የአዉሮጳ ኅብረት የወደፊት እጣ ፈንታ
ሐሙስ፣ ሰኔ 26 2017የአዉሮጳ ኅብረት የወደፊት እጣ ፈንታ
የሁለተኛ የዓለም ጦርነትን ማብቃት ተክትሎ እንደጎርጎረሳዉያኑ በ1949 ዓ.ም በአሜሪካ ፊታውራሪነት በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት አንጻር የተቋቋመው ግዙፉ የጦር ኃይል፤ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለመጀመሪያ ግዜ ወደ ስልጣን እስከመጡበት ግዜ ድረስ ቢያንስ ከአባላቱ ጥያቄ የሚነሳበት አልነበረም። ፕሬዝዳንት ትራምፕ እንደ ጎርጎረሳዉያኑ በ2016 ተመርጠው ወደ ስልጣን እንደመጡ ግን የኔቶ አስፈላጌትና ቀጣይነት ላይ ያነሷቸውን ጥያዎችዎች ዳግም ወድ ስልጣን ሲመጡም አጉልተው በማንሳታቸው ምክንያት የዘንድሮው ጉባኤ ስኬት አሳሳቢ ሆኖ ነበር። የአውሮጳ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተቃራኒ አቋም
አሚሪካ ከአውሮጳ የኔቶ አባል አገራት በተለየ ሁኔታ ለዩክሬን የምትሰጠውን እርዳታ ላትቀጥል እንደምትችል መገለጹ፣ አባል አገራት የሚጠበቅብቅባቸውን መዋጮ እስካላሟሉ ድረስ በድርጅቱ ደንብ አንቀጽ አምስት መሰረት ከሚደርስባቸው ጥቃት ሊከላክልላቸው የሚችል ኃይል ሊኖር እንደማይችልና ከእንግዲህም አባል አገራት ከገቢያቸው አምስት ከመቶ ለመከላከያ እንዲመድቡ መጠየቁ አባል አገራቱን እንዳይከፋፍልና ድርጅቱንም አደጋ ላይ እንዳይጥለው አስግቶ ነበር። የአዉሮጳ ህብረት የእስራኤል በጋዛ ጦርነት፤ ያለዉ አቋም ልዩነት የታየበትም ነዉ። ዩናይትድ ስቴትስ በህብረቱ ላይ የምትጥለዉ የቀሪጥ ችማሪ ሌላዉ ከዩናትድ ስቴትስ ጋር በነበረዉን ጥብቅ ግንኙነት ላይ ጥያቄ ያስነሳ ነዉ። ይህ ሁሉ ተግዳሮት በአዉሮጳ ህብረት ላይ ምን ተጽኖ ያሳድር ይሆን ። በሃገራቱ መካከልስ ምን ያህል መተማመን ይታያል? ከብረስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ በቦን በሚገኘዉ የዶቼ ቬሌ ራድዮ ጣብያ ዋና መስርያ ቤት ብቅ ብሎ ሳለ ስለ አዉሮጳ ህብረት ወቅታዊ ሁኔታ ፤ ስለወደፊት እጣ ፈንታ ቃለምልልስ አድርገናል።
ገበያዉ ንጉሴ / አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ