የአዉሮጳ ሕብረትና የብሪታንያ ባለሥልጣናት የመከላከያና የንግድ ሥምምነት
ማክሰኞ፣ ግንቦት 12 2017ማስታወቂያ
የአዉሮጳ ሕብረትና ብሪታንያ «ፍቅር እንደገና» እያሉ ነዉ።የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኡርዙላ ፎንዴር ላይንና የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ኪር ስታርመር ትናንት የሁለቱን ወገኖች የመከላከያና የንግድ ግንኙነትን ለማጠናከር ተስማምተዋል።ብሪታንያ ከአዉሮጳ ሕብረት አባልነት ከወጣች ወዲሕ በሁለቱ ወገኖች መካከል ከፍተኛ ቁጥጥር ይደረግበት የነበረዉ ከአንዱ ወደሌላዉ የመግቢያ ፈቃድ (ቪዛ)ና የተማሪዎችና የሠራተኞች ዝዉዉርም እንዲላላተስማምተዋል።ሥምምነቱን ስታርመር «ታሪካዊና ወቅቱን የጠበቀ» ሲሉት፣ ወይዘሮ ፎን ዴር ላይን በበኩላቸዉ «አዲስ ምዕራፍ» ብለዉታል።የሥምምነቱን ይዘትና ጥቅሙን በተመለከተ የለንደን ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕን በሥልክ አነጋግሬዋለሁ።
ድልነሳ ጌታነሕ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ