የአለማቀፍ ወንጀሎች መዳኛ ፍርድ ቤት በእስራኤልና ሀማስ መሪዎች ላይ ያቀረበው ክስ ጭብጥ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 13 2016የአለማቀፍ ወንጀሎች መዳኛ ፍርድ ቤት በእስራኤልና ሀማስ መሪዎች ላይ ያቀረበው ክስ ጭብጥ
የአለማቀፍ ወንጀል መዳኛ ፍርድ ቤት አይ ሲሲ ጠቅላይ አቃቢ ህግ፤ በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስተር ቤንጃሚን ናታኒያሁና የመከላከያ ሚኒስትራቸው ዮቭ ጋላንት እንዲሁም በህማስ መሪ ሚስተር ያህያ ሲኖዋር፣ የወታደራዊ ክንፉ መሪ ሞሃምድ ዲአብ ኢብራሂምና የፖለቲካ ቢሮ ሀላፊው ኢስማኤል ሃኔህ ላይ ፍርድ ቤቱ የእስር ማዘዣ ዋራንት እንዲቆርጥላቸው የጠየቁ መሆኑን ትናንት ሰኞ አስታውቀዋል። ጠቅላይ አቅቢ ህግ ካሪም ከሀን ይህንን የእስር ማዛዣ ዋራንት የጠየቁት ባለፈው መስከሩም 26 በእስራኤል በደረሰው ጥቃትና በጋዛ ደግሞ ከመስክረም 27 ጀምሮ እስካሁንም በዘለቀው ጦርነት ሁለቱ ወገኖች በየበኩላቸው የሰባዊና የጦር ወንጀሎችን ለመፈጸማቸው በቂና አስተማማኝ መረጃ በማግኘታቸው መሆኑን አስታውቀዋል “ ያሰባሰብናቸው መረጃዎች ጠቅላይ ሚኒስተር ቤንጃሚን ናታኒያሁና የመክላከያ ሚኒስትራቸው ዮቭ ጋላንት ከመስከረም 27 ጀምሮ በጋዛ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ለተፈጸሙ የሰባዊነትና የጦር ወንጀሎች ተጠያቂዎች ስለመሆቻው ከበቂ በላይ መርጃዎች ያሉን በመሆኑ ነው በማለት ወንጀሎቹ እርሀብን እንደጦር መሳሪያ መጠቀምን፣ ሰላማዊ ሰዎችን ኢላአማ አድርጎ መግደልንና ሌሎች ኢሰባዊ ድርጊቶችን የሚያጠቃሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተመሳሳይ ዋና አቃቢ ህግ ክሃን በሀማስ መሪዎችም የጦር ወንጀል ስለመፈጸማቸው መረጃዎች እንደደረሷቸውና በነሱ ላይም የእስር ማዣ ዋራንት እንዲቆጥረጥብቸውየጠየቁ መሆኑን አስታውቀዋል፤ “የህማስ መሪ ሚስተር ያህያ ሲንዋር፣ ወታደራዊ አዛዡ ሞሃመድ ዲአብ ኢብራሂም፤ እንዲሁም የፖለቲካ ሃላፊው ኢስማኤል ሃንየህም በሰላማዊ ሰዎች ላይ ግድያዎችን በመፈጸም፣ ሰዎችን በማገት፤ በማሰቃየትና በመግደል የጦርና የሰባዊነት ወንጀሎችን የፈጸሙ ስለመሆናቸው ቢሯቸው ከበቂ በላይ ማስረጃ ያለው መሆኑን አስታውቀዋል። ፍርድ ቤቱ በአንድ ወር ግዜ ውስጥ በአቃቢ ህግ የቀረበውን መረጃና ማስረጃ አይቶና መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
የክሱ አወዛጋቢነትና ያልተጠበቀ መሆን
የአቃቢ ህጉ በተለይ በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስተር ናትኒያሁና መከላከያ ሚኒስራቸው ላይ ያቀረበው ክስና የጠየቀው የእስር ማዘዣ አውዛጋቢና በብዙዎች ዘንድም ያልተጠበቀ ሁኗል። ፍርድቤቱ በ20 አመት ቆይታው ከቀዶሞዋ ዩጎዝላቪያና በቅርቡ ደግሞ ከሩሲያው መሪ ፕሬዝዳንት ፑቲን ውጭ በአፍሪካ መሪዎችና ግለሰቦች ላይ ያተኮር ስለነበር ነው፤ የምራባውያኑ ዴሞክራሲ ቤተሰብ አባል ናት በምትባለው እስራኢል ላይ ይህ ክስ መመስረቱ አይን ከፋች የሆነው ።
በክሱ ላይ የተሰሙ ተቃውሞና ድጋፍ ድምጾች
ጠቅላይ ሚስትስተር ናታኒያሁ ግን ገና አቃቢ ህጉ ክስ ለመመስረት እያሰበ መሆኑ ሲገለጽ፤ “ ይህ ከሆነ ትልቅ ታሪክዊ ስህተት ነው የሚሆነው፤ በመሰረቱ እንደ አይሲሲ ያሉ ፍርድቤቶች የተመሰረቱት በ2ኛው የዓለም ጦርነት በአይሁዶች ላይ የተፈጸመውን እልቂት መሰረት አድርገው ዳጋም ተመሳሳይ ወንጀሎች እንዳይፈጽሙ ለመካልከል እንጂ እንደ እስራኤል ያሉ እራሳቸውን የሚከላከሉ አገሮችን ለመክሰሰ አይደለም” ሲሉ አሳስበው የንበር ሲሆን ያሁኑን ክስም በተመሳስይ ሁኔታ ውድቅ አርገውታል ።
የፍርድቤቱ አባል ያልሆነችው አሜሪካምየቀረበውን ክስ ተገቢ እንዳልህነና የተኩስ አቁም እንዲደረግና ታጋቾች እንዲለቀቁ የሚደረገውን ጥረት ሊይደናቅፍ እንዴሚችል ነው የገለጸችው{።ሌሎች እንድብርታኒያ፣ ኦስትሪያ፤ ቼክ ሪፑብሊክ የመሳሰሉት ደግሞ በተለይ የእራኤል መሪዎች ከሀማስ መሪዎች ጋር ተጠያቂ መደረጋቸው ትክክል ኣለመሆኑን በልዩ ልዩ መንገድ ባውጡዋቸው መግለጫዎች አስታውቀዋል።ቤልጀየም ስሎቬኒያና ፈረንሳይ የመሠሉት ግን ተጠያቂነት ሊሰፍን ይገባል በማለት ካለማቀፉ ፍርቤት ጎን እንደሚቆሚቆሙ አስታውቀዋል።ሀማስ በበኩሉ የመሪዎቹ ከእስራኤል መሪዎች ጋር እኩል መከሰሰሳቸው ወንጀልኛንና ሰለባዎችን ያለየ ነው በማለት ሶስቱ የሃማስ መሪዎች ከክሱ ነጻ እንንዲሆኑ መጠየቁ ተዘግቧል።
ቀጣዩ የክስ ሂደት
በተክሳሾች ላይ በአለማቀፍ ፍርድቤት የእስር ማዘዣ ሲጠየቅ ምን ማለት እንደሆነ የተጠየቁት ቀድሞ የፍርድቤቱ ዋና አቃቢ ህግ የነበሩት ሰር ጂኦፍሬር ኒስ ሲመልሱ፤ “አቃቢ ህግ ለእስር ማዛዣ መቆረጥ ያሳምኑልኛል ያላቸውን መረጃዎች ለፍርድቤቱ ያቀርብና ፍርድቤቱ ካመነባቸው በተክሳሾቾቹ ላይ የእስር ማዛዥ ሊቆረጥና ተላልፈው እንዲሰጡ ሊደረግ ይችላል ብለዋል። ሆኖም ግን አገራቱ ፈራሚዎች ካልሆኑ ሊሎች ፈራሚ አገሮች ግለሰቦቹን ወደ አገራቸው ሲገቡ ይዘው እንዲያስረክቡ እንደሚገደዱም፡ ገልጸዋል ሰር ጂኦፍሪ ኒስ። ከ123 የፍርድቤቱ ፈራሚ አገራት መከከል አሜርካ፣ ሩሲያ ቻይናና እራኤል ጭምር የሉበትም።
የክሱ አንደምታ በጠቅላይ ሚኒስተር ናታኒያሁ ስልጣን ላይ
በሌላ በኩል ግን ይህ ክስ በተለይም የስራኤል መሪዎች ከሀማስ መሪዎች ጋር እኩል መወንጀላቸው የህዝብ ድጋፍ ተሸርሺሮባቸው ለነበሩት ናታኒያሁ የተቃዋሚዎቻቸውን ድጋፍ ሳይቀር እያስገኘላቸው ነው እየተባለ ነው። በመሆኑም ክሱ ለፍልስጤም ህዝብ ሊያመጣ ከሚችለው ሰላም ይልቅ ለሚስተር ናኒያሁ በስልጣን መቆየት ሊረዳ እንደሚችል ነው ታዛቢዎች የሚናገሩት
ገበያው ንጉሴ