የናይሮቢ የአየር ንብረት ፍትህ የበጋ ትምህርት በአዲስ አበባ እየተካሔደ ነው
ረቡዕ፣ ነሐሴ 21 2017የ5ኛው የናይሮቢ የአየር ንብረት ፍትህ የበጋ ትምህርት ወጣት መሪዎችን፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮችን፣ ፖሊሲ አውጪዎችን እና ምሁራንን ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአለም ሀገራት በማገናኘት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው። የናይሮቢ የአየር ንብረት ፍትህ የበጋ ትምህርት ስልጠና የተዘጋጀ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና
የኮምፒውቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ከፓን አፍሪካ የአየር ንብረት ፍተህ ህብረት እና አለምአቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር ነው። የአየር ንብረት ፍትህ ለአፍሪካ እና ለአለም ዘላቂነት ያለው የጋራ መፈትሄ አስፈላጊ ነው የተባለው የበጋ ትምሀርት በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተስተናገደ ሲሆን ስልጠናው በአየር ንብረት ፍትሕ ዙሪያ እውቀትን፣ ቅስቀሳን እና የተጀመሩተን ተግባርት ለማጠናከር የተነደፈ ነው ተብሎዋል።
የናይሮቢ የአየር ንብረት ፍትህ የበጋ ትምህርት ለ ሁለት ሳምንት የሚቆይ ሲሆን ተገቢውን የአቅም ግንባታ በመፍጠር ለአፍሪካ እና ለተቀረው አለም የአየር ንብረት ቀውስ ምላሽ ለመስጠት ከተያዪ የአፈሪካ እና የአለም ክፍል የተውጣጡ ወጣት የፖሊሲ አወጨ ዎች እና መሪዎች እና ማህበረሰብ አንቂዎቸ በካል እንደዚሁም በበይነመረብ ጭምር ተካፍለውበታል ።
የአየር ንብረት ፍትሕ የአካባቢ ጉዳይ ብቻ አይደለም በአየር ንብረት መዛባት ምክንያት ያልሆኑ ነገር ግን ለችግሩ ገፈት ቀማሽ ለሆኑ ማህበረሰቦች ድምጽ መሆን እና ፍትህ መፈልግ ነው።’’ ይህንን ፕሮግራም የአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ በትብብር ማዘጋጀቱ ወጣት ምሁራን በአለም አቀፍ የአየር ንብረት ዙሪያ የራሳቸው ድርሻ እንዲኖራቸው ከማስቻሉም በላይ በዚህ ዙሪያ የአፍሪካ የሳይንስ እና የምርመር ተቁዋማት መካከል ያለውን ትስስር ያጠናክራ ‘’ሲሉ ዾ/ር አዲስ ሀይሉ ከአዲስ አብባ ዪንቨርስቲ ተፈጥሮኦ ሳይንስ ስነ-ምድር ትምህረት ከፍል ተናግረዋል
የአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ አሁን በጀመረው ሪፎርም መሰርት የአየር ንብረት ለውጥን ታሳቢ ያደረገ የጥናት እና ምርመር ክፍል እንዳልው ሁሉ በሌሎችም የጥናት እና የምረመር ዘርፎች ይህንኑ ታሳቢ ያደርጉ ኮርሶችን በጣምራ እየሰጠ እንደሆነ ተነግረዋል
የአየር ንብረት ፍትህ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ስልጠናው የአፍሪካ ወጣቶችን እና የሲቪል ማህበረሰቡን በአየር ንብረት ፍትሃዊ ነት ጥበቃ ላይ ያላቸውን አህጉራዊ እና አካባቢያዊ አግባብነት እንደሚያጠናክር ይናገራሉ ስልጠናው ለአፍሪካ እና ለአለም ጠንካራ የአየር ንብረት መፍትሄዎችን ለመቅረጽ እንዲሁም የፖሊሲ፣ የተግባር እና የጋራ አስተሳሰብ ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር ወሳኝ እንቅሰቃሴ እንደሆነ ተናግረው እንዲህ ያለው ስልጠና ከታች ጅምሮ ለተማሪዎች መስጠት እና ማሳውቅ እንድሚገባ ገልጸዋል።
ሐና ደምሴ
እሸቴ በቀለ
ኂሩት መለሠ