ሰለሞን ሙጬ
ዓርብ፣ ጥር 30 2017ማስታወቂያ
ኒው ዚላንድ ዓለም ላይ ከፍተኛ የሚባል የኑሮ ደረጃ ካላቸው ሀገራት አንዷ ስትሆን ለጎብኝዎች የሚስማሙ መልክዓ ምድሮችን ያቀፉ፣ በበረዷማ ተራሮች ያጌጡ ደሴቶች፣ ጥብቅ ደኖችና አረንጓዴ ስፍራዎች እንዲሁም ውኃ ያረፈባቸው የመሬት ክፍሎች የተዋበች ሀገር ናት።
ሀገሪቱ አፍሪካ ውስጥ በጣት የሚቆጠሩ ኤምባሲዎች ያሏት ሲሆን አንዱ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ይገኛል። ትናንት ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ደግሞ የነፃነት ቀናቸውን ቦሌ ላይ በሚገኘው የኤምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ አክብረዋል።
ይህች የደሴቶች ሀገር የሆነችው ኒው ዚላንድ በነባር ሕዝቦቿ በተለይም በማዖሪዎች ሀካ የተባለው ሀገረሰባዊ ነባር የጭፈራ ትውፊት ትታወቃለች።
የቪዲዮ ዘገባ፤ ሰለሞን ሙጬ