የነዳጅ እጥረት በአማራ ክልል
ሰኞ፣ ሚያዝያ 6 2017ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ነዳጅ ለመቅዳት በታላላቅ ከተሞች ርጃጅም ሰክፎች መመልከት የተለመደ ሆኗል፡፡ የነዳጅ እጠረቱ የሚፈጥረው ችግር ሠዎች ከቦታ ቦታ በጊዜ ተንቀሳቅሰው ሥራቸውን ማከናወን እንዳልቻሉ ይገልፃሉ፡፡ አሽክረካሪዎች በተለይ የሥራ ጊዜያቸው በከፍተኛ ሁኔታ በነዳጅ እጥረት ምክንያት ይባክናል፡፡
በባሕር ዳር ከተማ የናፍጣ ዘይት ለመቅዳት ተሰልፎ ያገኘነው መልካሙ አቢች ነዳጅ ለመቅዳት ያለውን ፈተና እንደገለጸው በሰልፍ ቅናትን ያሳልፋል፣ ወረፋ ሲደርሰውም ነዳጅ አልቋል ይባላል፡፡
ማስረሻ ሞላ የተባለ አሽከርካሪ በበኩሉ በማደያዎች ተሰልፎ ነዳጅ ለመቅዳት እስከ 4 ቅናት እንደሚወስድበት አመልክቶ እንደዛም ሆኖ ሳይቀዳ የሚመለስበት ጊዜ እንዳለ ተናግሯል፡፡
በመንግሥት እና በፋኖ መካከል የሚካሄደዉ ጦርነት የአማራ ክልል ንግድን ማቀዛቀዙ
ማደያዎች ከታሪፍ በላይ እንደሚያስከፍሉም የሚገልፀው አስተያየት ሰጪው የቁጥጥር አሰራር መላላት የፈጠረው ችግር እንደሆነም ያምናል፡፡ ህብረተሰቡም በወቅቱ የትራንስፖርት አገልግሎት እያገኘ ባለመሆኑ ለገንዘብ ብዝበዛ ተጋልጧል ሲል ገልጧል፡፡
ማደያዎች ተጨማሪ ክፍያ ስለሚጠይቁና በህገወጥ መንገድ ነዳጅ ሰለሽጡ በህጋዊ መንገድ ነዳጅ መቅዳት የሚፈልጉ ሰዎች ተጎጂ ናቸው ያለው ደግሞ ቡቃያው ለጃለም የተባለ አሽከርካሪ ነው፡፡ ህገወጥነቱ ድብደባንም እንደሚጭምር ቡቃያው ነግሮናል፡፡
የአማራ ክልል ንግግድና ገበያ ለማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኢብራሒም ሙሐመድ ነዳጅ ከወደብ በሚመጣበት ወቅት በፀጥታ ችግር ምክንያት ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች በየከተሞቹ ስለሚያድሩ በፍጥነት ወደ ማዳያዎች መድረስ ባለመቻላቸው በየከተሞቹ ለሚታዩ የተሽከርካሪ ሰልፎች ምክንያት ነው ብለዋል፡፡
የነዳጅ ዘይት እጥረትና የዋጋ ንረት በአማራ ክልል
ሰልፎቹ ሁልት መልክ እንዳላቸው የገለፁት ቢሮ ኃላፊው አንደኛው በሀጋዊ መንገድ የሚቀዳ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በሀገወጥ መንገድ እየቀዱ የሚሸጡና ተመልሰው ተሰልፈው የሚቀዱ ናቸው ነው ያሉት፡፡
ለነዳጅ እጠረቱ ምክንያቶች ባለተሽከርካሪዎች፣ ባለማደያዎችና አንዳንድ ብበኢሮወው መዋቅር ውስጥ ያሉ ሠራተኞች መሆናቸውን ዶ/ር ኢብራሂም ጠቅሰው ከሥራ ማገድን ጨምሮ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሠራተኞችና የነዳጅ ማደያዎች አሉ ብለዋል፡፡
በነዳጅ አቅርቦት ረገድ ያለው ህገውጥነት ዘርፈ ብዙ መሆኑን ያብራሩት ዶ/ር ኢብራሒም ያለውን ህገውጥነትና የነዳጅ እጠረት ለማሻሻል የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በትኩረት እንደሚሰራ ቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡
ዓለምነው መኮንን
እሸቴ በቀለ
ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር