የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በሁለት ዓመቱ የስልጣን ጊዜ ምን አሳካ?
ሰኞ፣ መጋቢት 15 2017ከፕሪቶርያ ስምምነት በኃላ በትግራይ የተቋቋመው ግዚያዊ አስተዳደር ከተመሰረተ ትላንት ሁለት ዓመት ሆኖታል። በህወሓት ከፍተኛ ድርሻ የተቋቋመው ግዚያዊ አስተዳደር የፓርቲው ክፍፍል ተከትሎ ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ገብቶ ይገኛል። የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር እስከ ቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ድረስ እንደሚቀጥልና 'ለውጦች' ግን ሊደረጉ እንደሚችሉ በቅርቡ አስታውቋል። ግዚያዊ አስተዳደሩ በእስካሁን ቆይታው ምን አሳካ ? የሁለት ዓመቱ ጉዞ ምን ይመስላል ? ከትግራይ ፖለቲከኛ እና ሌሎች አነጋግረናል።“መፈንቅለ-መንግሥት” ወይስ “ሕግ ማስከበር” የትግራይ ቅርቃር
ከሁለት ዓመቱ ጦርነት በኃላ የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተከትሎ መጋቢት ወር አጋማሽ 2015 ዓመተምህረት የተቋቋመው የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ወደ ስራ ከገባ ሁለት ዓመት ሆኖታል። በፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ የሚመራው የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር፥ ህወሓት አብላጫ ድርሻን ይዞ ያለበት ሲሆን፥ የትግራይ ሐይሎች፣ የአንድ ተቃዋሚ ፓርቲ፣ የሲቪክ ማሕበራት እና የምሁራን ውሱን ተሳትፎ እና ውክልና የሚያካትት አወቃቀር አለው። የህወሓት ክፍፍልን ተከትሎ በከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ገብቶ የሚገኘው ግዚያዊ አስተዳደሩ ለውጦች ተደርገውበት እስከ ቀጣይ ሀገራዊ ምርጫ ድረስ እንደሚቀጥልም በቅርቡ በፌደራሉ መንግስት ተነግሯል። የግዚያዊ አስተዳደሩ የሁለት ዓመት ጉዞ ምን ይመስላል በሚል አስተያየታቸውን ያጋሩን በክልሉ የሚገኙ ፖለቲከኞች እና ሌሎች አካላት በአወንታ እና አሉታ የሚነሱ ነጥቦች ያስቀምጣሉ።
የተቃዋሚው ፓርቲ ትንሳኤ ስርዓት ቃንጪ ሓቂ መሪ አቶ ደጋፊ ጎደፋይ በግዚያዊ አስተዳደሩ የሁለት ዓመት ግዜ በተለይም የፖለቲካ ምህዳር በማስፋት ረገድ በአወንታ የሚነሱ የተወሰኑ ለውጦች መታየታቸው ያነሳሉ።እንወያይ፤ ማኅበረሰቡን ያስጨነቀዉ የትግራይ ፖለቲከኞች ሽኩቻ
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግዚያዊ አስተዳደሩ የህዝብ የለውጥ ፍላጎት በሚገባ አለመምራቱ ደግሞ ፖለቲከኛው ይነቅፋሉ። ሌላው ያነጋገርናቸው በተለይም በምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮች ጉዳይ በስፋት የሚሰራው የወልቃይት ሲቪል ማሕበረሰብ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ነጋሽ ግደይ በበኩላቸው፥ በተለይም ተፈናቃዮች ወደቀዬአቸው ከመመለስ አንፃር በፕሪቶርያው ስምምነት መሰረት የተመሰረተው ግዚያዊ አስተዳደር የሚጠበቅበት አለመፈፀሙ ያነሳሉ።
የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር እስከ ቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ድረስ እንደሚቀጥልና 'ለውጦች' ግን ሊደረጉ እንደሚችሉ በቅርቡ አስታውቋል። ፖለቲከኛው አቶ ደጋፊ ጎደፋይ ግዚያዊ አስተዳደሩ አካታች ሊሆን ይገባል ሲሉ ሀሳባቸው ያቀርባሉ።
ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
አዜብ ታደሰ
ፀሐይ ጫኔ