የትራምፕ ርምጃና የአዉሮጶች ዛቻ
ማክሰኞ፣ የካቲት 4 2017ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕወደ አሜሪካ በሚገቡ የብረትና የአልሙኑየም ማዕዳናት ላይ የቀረጥ ጭማሪ አድርገዋል።
ትራምፕ ትናንት እንዳስታወቁት ከየትኛዉም ሐገር ወደ አሜሪካ የሚገባ ብረትና አልሙኒየም 25 በመቶ ቀረጥ ይከፍላል።
የትራምፕ እርምጃ የዩናይትድ ስቴትስ የቅርብ ወዳጅና ተሻራኪ የሆኑትን የአዉሮጳ መንግሥታትን አስደንግጧል።
የአዉሮጳ ሕብረት፣የአባል ሐገራትና የብሪታንያ መሪዎች የትራምፕን እርምጃ ተቃዉሞዉ ድርድር እንዲደረግ ጠይቀዋል።ድርድሩ ካልተሳካ በአሜሪካ ሸቀጦች ላይ አፀፋ እርምጃ እንደሚወስዱ አስታዉቀዋል።
ሥለ ትራምፕ ርምጃ-የአዉሮጶች ዛቻ የብራስልስ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴን በሥልክ አነጋግሬዋለሁ።
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ