እንወያይ፤ ለኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት ዋና ዋና ፈተናዎች እና መፍትሔዎች
እሑድ፣ ነሐሴ 18 2017የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር በአሁኑ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚገኙ፣ ከሁሉም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የክረምት ልዩ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።
በዘንድሮው ዓመት 84 ሺ የሚሆኑ ሰልጣኞች ተሳታፊ እንደሆኑም ተገልጿል። የማህበራዊ ሳይንስ ስልጠና የሚወስዱት ዛሬ ነሀሴ 16 ቀን ስልጠናውን ያጠናቀቁ ሲሆን ፤ የተፈጥሮ ሳይንስ ስልጠና ደግሞ የሚቀጥለው ዕሮቡ ነሀሴ 21 ቀን ይጠናቀቃል።
በመጪው እሁድ የሚተላለፈው የእንወያይ መሰናዶ ይህንን የክረምት ልዩ ስልጠና ተንተርሶ ከ ኢትዮጵያ ትምህርት ጥራት እስከ መምህራን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል፤ የመማር ማስተማር ሂደቱን የሚያስተጓጉሉ ችግሮች እና መፍትሔዎች ድረስ ይቃኛል።
በውይይቱ የተሳተፉት፦
1. የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት: ዶክተር ዮሀንስ በንቲ፣
2. በአሁን ሰዓት ለመምህራን የሚሰጠውን የክረምት ልዩ ስልጠና በመከታተል ላይ የሚገኙት : መምህር አማኑኤል በላቸው እና
3. እስካለፈው ዓመት ድረስ በኦሮሚያ ክልል ደምቢ ዶሎ ዩንቨርስቲ በመምህርነት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ካሳሁን ተሬቻ ናቸው።
በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራን እና ትምህርት አመራር ልማት ክፍል ኃላፊ፤ ወይዘሮ አሰገድ ምሬሳ በቀጥታ በውይይቱ ባይሳተፉም ከውይይቱ አስቀድሞ ከስልጠናው ጋር በተያያዘ ሊነሱ በሚችሉ ጥያቄዎች ላይ ምላሽ ሰጥተውናል።