ማስታወቂያ
አርዕስተ ዜና
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፦ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት)ን ከፖለቲካ ፓርቲነት መሠረዙን ዛሬ ይፋ አደረገ ። ሕወሓት ከፓርቲነት የተሰረዘው በሦስት ወራት ጊዜ የዕርምት ርምጃ እንዲወስድ በቦርዱ የቀረበለትን ጥያቄ ባለመፈጸሙ መሆኑ ተገልጧል ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በተከሰተ ግጭት አንድ የፀጥታ አባልን ጨምሮ የአራት ሰዎች ሕወት ማለፉን የአካባቢዎው ነዋሪዎች ገለጹ ። በግጭቱ በርካቶች መቁሰላቸውንና ቁጥራቸው ያልታወቁ የመኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸው ተጠቅሷል ።
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከካታር ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን ሐማድ ኧል-ታህኒ ጋር ዛሬ ዶሐ ውስጥ በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ ። በውይይቱ ስለ ሩስያ እና ዩክሬን ጉዳይም ማንሳታቸው ተዘግቧል ። ካታር ከዩናይትድ ስቴትስ አውሮፕላን አምራች የቦይንግ ኩባንያ የ400 ቢሊዮን ዶላር አውሮፕላኖችን ለመግዛት ስምምነት መፈረሟም ተገልጧል ።
ሙሉ ዜናውን ከድምፅ ማእቀፉ ማድመጥ ይቻላል