የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አጠቃቀምና ተጠያቂነት
ዓርብ፣ ሐምሌ 10 2012ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን የሰከነ የውይይት ባህል ማዳበር እንደሚገባ የጋዜጠኝነት መምህር እና የማህበራዊ ስነ ልቦና ሳይንስ ምሁር አሳሰቡ።ምሁራኑ ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አጠቃቀም ዴሞክራሲን ከማሳደግ ይልቅ ክብርና ማንነት የሚናድበት መድረክ ሆኗል በማለት ልምዱን ኮንነዋል። የማህኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በበኩላቸው የችግሩ ምንጭ የአጠቃቀሙ የሕግ ማዕቀፍና ተጠያቂነት አለመኖር ነው ይላሉ።በነርሱ አስተያየት መፍትሄው ሚዲያውን መዝጋት ሳይሆን ተጠያቂነት ያለው የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አጠቃቀም ሕጋዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ነው።
ዓለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ