የመጋቢት 22 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
ሰኞ፣ መጋቢት 22 2017ሐዋሳ ከተማ ውስጥ በተከናወነው የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ግጥሚያ የግማሽ ፍጻሜ አላፊዎች ተለይተዋል ። በእንግሊዝ ኤፍ ኤካፕም እንደዛው ። ናይጄሪያዊው ቡጢኛ ጋና ውስጥ የቡጢ መፋለሚያ መድረክ ላይ በአሳዛኝ ሁኔታ ሕይወቱ አልፋለች ።
እግር ኳስ
ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሞሮኮ ውስጥ ባለፈው ሳምንት ከጅቡቲ ጋር የተጋጠመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በሰፋ የግብ ልዩነት 6 ለ1 ማሸነፉ በቡድኑ መነቃቃትን ፈጥሯል ። ብሔራዊ ቡድኑ ከጅቡቲ ቀደም ብሎ እዚያው ሞርኮ ውስጥ ከግብጽ ጋር ተጋጥሞ የተሸነፈው 2 ለ0 ነበር ። የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ኢትዮ ስፖርት አዘጋጅ እና አቅራቢ ምሥጋናው ታደሰ ጨዋታውንም ከጨዋታው በኋላ የተሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫ ተከታትሏል ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ዓለም አቀፍ መስፈርትን የሚያሟላ ስታዲየም አሁንም ድረስ ባለመኖሩ ቡድኑ በአገር ቤት በሜዳው እና በደጋፊዎቹ ፊት መጫወት የነበረበት ሁለቱንም ጨዋታዎች ከአገር ውጪ ለማድረግ ተገድዷል ። ይህ በቡድኑ ውጤት ላይ የሚፈጥረው ተጽእኖው ቀላል እንዳልሆነ ይገመታል ።
የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች በጅቡቲው ጨዋታ ወቅት መለያቸውን ከፍ አድርገው የሆድ ቅርጻቸውን ሲያሳዩ ነበር ። ለአድማጮች ግልጽ እንዲሆን ተጨዋቾቹ ይህን ያደረጉበት ምክንያቱ ምንድን ነው? በእርግጥ በማኅበራዊ መገናኛዎች የተጨዋቾችን ተክለ ሰውነት በመቀየር የተዘዋወረ ፎቶ ነበር ። ከዚያ ጋር እንደሚገናኝ ምሥጋናው ገልጧል ።
ከጅቡቲው ጨዋታ በኋላ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ባሕሩ ጥላሁን በጋራ መግለጫ ሰጥተው ነበር ። ስለ ተጨዋቾች ስነምግባር እና የቡድኑ የተማከለ መረጃ የመስጠት ፍሰት ላይ ትችት ቀርቦ መልስ ተሰጥቷል ። የተሰጠው መልስ አጥጋቢ ነው? በእርግጥ የተጨዋቾችን ስነምግባር በማስጠበቅ ረገድ ምን መደረግ አለበት ለሚለውም ማብራሪያ ሰጥቷል ።
ግብፅ በ16 ነጥብ ምድቡን ትመራለች ። ቡርኪና ፋሶ በ11 ትከተላለች ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በሴራሊዮን በሁለት ነጥብ ተበልጦ በስድስት ነጥቡ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ። ተመሳሳይ ስድስት ነጥብ ሰብስቦ በግብ ክፍያ ልዩነት የጊኒ-ቢሳው ቡድን ደረጃው አምስተኛ ነው ። የግብ ጎተራ የሆነችው ጅቡቲ በ16 የግብ እዳ እና በአንድ ነጥብ ብቻ የመጨረሻ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ሰፍራለች ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ማጣሪያውን የማለፍ ተስፋው «በመርፌ ቀዳዳ የማለፍ ያህል ነው» ብሏል ምሥጋናው ።የመጋቢት 15 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
የኢትዮጵያ ዋንጫ
ሐዋሳ ከተማ ውስጥ በተከናወነው የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ግጥሚያ፦ ትናንት መቻል ኢትዮጵያ መድንን 3 ለ1፤ ወላይታ ድቻ ሐዋሳን 3 ለ2 አሸንፈዋል ። ቅዳሜ ዕለት ደግሞ፦ ሸገር ከተማ ባህር ዳር ከተማን 4 ለ3 እንዲሁም ሲዳማ ቡና ሀዲያ ሆሳዕናን 3 ለ0 ድል አድርገዋል ። በዚህም መሠረት ሚያዚያ 18 እና 19 በግማሽ ፍጻሜው፦ ወላይታ ድቻ ከሸገር ከተማ፤ እንዲሁም መቻል ከሲዳማ ይጋጠማሉ ። የውድድር ቦታ እና ሰአት ወደፊት እንደሚገለጥ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዐሳውቋል ።
ኤፍ ኤ ካፕ
ትናንት በተከናወነው የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ እግር ኳስ ግጥሚያ፦ ማንቸስተር ሲቲ እና አስቶን ቪላ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፋቸውን አረጋገጡ ። ቅዳሜ ዕለት ክሪስታል ፓላስ ፉልሀምን 3 ለ0 በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜው አልፏል ። በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜው ከብራይተን ጋር ያለምንም ግብ የተለያየው ኖቲንግሀም ፎረስትም በመለያ ምት 4 ለ3 ድል አድርጎ የግማሽ ፍጻሜው ተሳታፊ ሁኗል ።
ማንቸስተር ሲቲ ትናንት በርመስን ድል ያደረገው 63ኛ ደቂቃ ላይ በቀተቆጠረው የዖማር ማርሙሽ ሁለተኛ ግብ ነው ። በ21ኛው ደቂቃ ላይ በርመስ ባስቆጠራት ቀዳሚ ግብ ማንቸስተር ሲቲ እየተመራ ነበር የመጀመሪያው አጋማሽ የተጠናቀቀው ። ከእረፍት መልስ ብዙም ሳይቆይ በ49ኛው ደቂቃ ላይ የማንቸስተተር ሲቲ ደጋፊዎችን ትንፋሽ ጋብ ያደረገው ግብ በኧርሊንግ ኦላንድ ተቆጥሯል ። በሜዳቸው ቪታሊቲ ስታዲየም ውስጥ የተጋጠሙት በርመሶች ሲቲን አሸንፈው ወደ ዌምብሌይ ስታዲየም የማቅናት ሕልማቸውም መክኗል ። ሆኖም በርመሶች ማንቸስተር ሲቲ ላይ ጫና በመፍጠር ማስጨነቁ ተሳክቶላቸዋል ። በሌላኛው የትናንት ግጥሚያ፦ ለአስቶን ቪላ ማርኩስ ራሽፎርድ በ58 እና 63 ደቂቃ ላይ ሁለት ግቦችን፤ ጄኮብ ራምሴይ ደግሞ 71ኛው ደቂቃ ላይ ሦስተኛዋን ግብ አስቆጥረዋል ። በጨዋታው አስቶን ቪላ ፍጹም የበላይነት ዐሳይቶበታል ። የመጋቢት 8 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
ሚያዝያ 18 ቀን፣ 2017 ዓ.ም በሚኖረው የኤፍ ኤ ካፕ ግማሽ ፍጻሜ ግጥሚያ፦ ኖቲንግሀም ፎረስት ከማንቸስተር ሲቲ እንዲሁም ክሪስታል ፓላስ ከአስቶን ቪላ ጋር ዌምብሌይ ስታዲየም ውስጥ ይጋጠማሉ ። በተለይ ከፕሬሚየር ሊግ የዋንጫ ሽሚያ ግስጋሴው የተገታ ለመሰለው ማንቸስተር ሲቲ ዋንጫ ለማንሳት ይህ መልካም አጋጣሚ ይመስላል ።
በፕሬሚየር ሊጉ 48 ነጥብ ሰብስቦ አምስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማንቸስተር ሲቲ ረቡዕ ዕለት ከላይስተር ሲቲ ጋር ይጋጠማል ። ኖቶንግሀም ፎረስት በፕሬሚየር ሊጉ 54 ነጥብ ሰብስቦ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ። በ37 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ከሰፈረው ማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ነገ ይጋጠማል ። ረቡዕ ከብራይተን ጋር የሚጫወተው አስቶን ቪላ በ45 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ሰፍሯል ። ክሪስታል ፓላስ 39 ነጥብ ሰብስቦ በፕሬሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 12ኛ ላይ ይገኛል፤ በ9 ነጥቡ የደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ 20ኛ ላይ ከተዘረጋው ሳውዝሐምፕተን ጋር ረቡዕ ይጋጠማል ። ላይስተር ሲቲ እና ኢፕስዊች ታወን በ17 ነጥብ ወራጅ ቀጣና ውስጥ ይገኛሉ ። ፕሬሚየር ሊጉን በ70 ነጥብ የሚመራው ሊቨርፑል ረቡዕ ዕለት ኤቨርተንን ይጋጠማል ። በ58 ነጥብ ሊቨርፑልን የሚከተለው አርሰናል ነገ ፉልሀምን ያስተናግዳል ። በ49 በጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ቸልሲ ቶትንሀም ሐሙስ ይገጥማል ።
ቡንደስሊጋ
በጀርመን ቡንደስሊጋ፦ ትናንት ቦሩስያ ዶርትሙንድ ማይንትስን 3 ለ1 አሸንፏል ። በ38 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ይዋትታል ። በ48 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አይንትራኅት ፍራንክፉርት ሽቱትጋርትን 1 ለ0 ድል አድርጓል ። ፍራይቡርግ በሜዳው ኤውሮጳ ፓርክ ስታዲየም ተጋጥሞ በዑኒዮን ቤርሊን የ2 ለ1 ሽንፈት ገጥሞታል ። በ59 ነጥቡ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ባዬር ሌቨርኩሰን ቦሁምን 3 ለ1 ድል ማድረግ ችሏል ። በ65 ነጥብ የደረጃ ሰንጠረዡ መሪው ባዬርን ሙይንሽን ሳንክት ፓውሊን 3 ለ2 አሸንፏል ።
በቦሩስያ ሞይንሽንግላድባኅ 1 ለ0 ተሸንፎ በ42 ነጥቡ ስድስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ላይፕትሲሽ የ48 ዓመቱ አሰልጣኝ ማርኮ ሮይስን አሰናብቷል ። አሰልጣኙ የተሰናበቱት ቡድኑ በቡንደስሊጋው ባለው ዝቅተኛ ደረጃ እና ከአውሮጳ ሻምፒዮንስ ሊግም በጊዜ በመሰናበቱ ነው ። ማርኮ ሮይስ በላይፕትሲሽ የሁለት ዓመት ከመንፈቅ አሰልጣኝነታቸው ወርቃማ ዘመን ቡድኑን ለጀርመን ካፕ እና ሱፐር ካፕ ዋንጫዎች ድል አብቅተው ነበር ። ላይፕትሲሽ በኤፍ ኤካፕ ክርሲስታል ፓላስን ለግማሽ ፍጻሜ ያደረሱት አሰልጣኝ ዖሊቨር ግላስነር ላይ ዐይኑን ጥሏል ።
አሳዛኙ የቡጢ ፍልሚያ ፍጻሜ በጋና
በጋና ፕሮ መለስተኛ ከባድ ሚዛን ቡጢ የቅዳሜ ዕለት የቡጢ ፍልሚያ ውድድር ናይጄሪያዊው ተፋላሚ የቡጢ መድረክ ላይ ሕይወቱ አለፈ ። ናይጄሪያዊው ቡጢኛ ጋብሪየል ዖሉዋሴጉን ዖላንሬዋጁ በአሳዛኝ ሁኔታ ሕይወቱ የቡጢ መድረክ ላይ ያለፈው ጋና ዋና ከተማ አክራ ውስጥ ነው ። የመጋቢት 01 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
የ40 ዓመቱ ናይጄሪያዊው ዝነኛ ቡጢኛ ከጋናው ቡጢኛ ጆን ምባንጉ ጋር ስምንት ዙር ፍልሚያ ሊያደርግ ነበር መድረክ ላይ የወጣው ። ሆኖም በአሳዛኝ ሁኔታ ሦስተኛው ዙር ግጥሚያ ላይ ይህ ነው የማይባል ቀለል ያሉ ቡጢ ተሰንዝሮበት የመድረኩ መወጠሪያ ላይ ተዝለፍልፎ በመደገፍ ይወድቃል ። ናይጄሪያዊ ሕክምና እንዲያገኝ ዳኛው አስቸኳይ ጥሪ ቢያደርጉም ሐኪሞች ሕይወቱን ሊታደጉ አልቻሉም ። ቡጢው ለሕይወት የሚያሰጋ አልነበረም ሲሉ የጋና መገናኛ አውታሮች ቢዘግቡም ናይጄሪያዊው የቡጢ መድረክ ላይ ሕይወቱ ማለፉ በቡጢው ስፖርት ዘንድ ብርቱ ሐዘን ፈጥሯል ።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሠ